የኢትዮጵያንግድ ባንክ አገልግሎት መስጠት አቆርጦ ነበር 

የኢትዮጵያንግድ ባንክ አገልግሎት መስጠት አቆርጦ ነበር 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሃገሪቱ ለግማሽ ቀን በአጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ሳብያ አገልግሎት መስጠት አቆርጦ  ነበር ። 

    ቅዳሜ መጋቢት ፯ እስከ ቀኑ ሰባት ሰአት ድረስ የሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም ከቅርንጫፍ ወደ ቅርንጫፍ ገንዘብ ማዘዋወርም ሆነ ሂስብ ማንቀሳቀስ አይቻልም ነበር።

 አንዳንድ የባንኩ ደንበኞች እንደተናገሩት የኤቲኤም እና የምባይል ገንዘብ ዝውውር በተመለከተ ከሌሊቱ ስድስት ሰአት እስከ ዘጠኝ ሰአት ድረስ ባጋጠማቸው ብልሽት ደንበኞች የሌላቸውን ገንዘብ ሁሉ ያወጡ ነበር የሚል መረጃ ከጅማ ስምተው እንደነበር ተናግረዋል

 የባንኩ ተገልጋዬች የሆኑ የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ይህንን መረጃ ከሰሙ በኃላ ኤቲኤም ማሽን እየፈለጉ ገንዘብ ሲያወጡ ማንጋታቸው መሰማቱን ተከትሎ ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ያሉት ቅርንጫፎች ስራ አቁመው ችግሩን ለመፍታት ሲረባረቡ ማርፈዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

   የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለስድስት ሰአት በላይ ሲስተሙን ለማስተካከል ሰራተኞቹና ባለሙያዎች ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ርብርብ ሲስተሙ ተስተካክሎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ለተፈጠረው መስተጉዋጎል ደንበኞቹን እና ተጠቃሚዎችን ይቅርታ በመጠየቅ እገልግሎትን እስከ ምሽት ሁለት ሰአት እንዲቆይ ለደንበኞቹ ከማሳውቅ በቀር በጅማና በሌሎች ክልሎች ከተሞች ያሉ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች የቴክኒክ ስህተቱን ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተወሰደበት ምንም አይነት መረጃ አልሰጠም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባወጣው መግለጫ 

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ባንኩ አስታውቋል፡፡ 

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልጿል፡፡ 

ባንኩ በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን ለደምበኞቹ አስታውቋል፡፡ 

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ 

ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ባንኩ ይቅርታ ጠይቋል፡፡en

LEAVE A REPLY