*ተፈናቃዮችንወደቀያቸው መመለስ ቅድሚያተሰጥቶል!!
ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚገኙና የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን አካባቢዎች በህገ መንግስቱ እና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረት በዘላቂነት እልባት ለመስጠት በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ አፈጻጸም የገመገመ ስብሰባ መጋቢት ፯ቀን ፪ሺ፩፮ ተካሄደ።
በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚገኙና ህወሓት ምዕራብ ትግራይ በሚል የሚጠራቸው ቦታዎች አሁን ላይ በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ዞን አካል ናቸው።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተሳታፊዎች የተሳተፉበት ብሔራዊ ኮሚቴ በግምገማው መሰረት በአፈፃፀም ሂደቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች የተለዩ ሲሆን የማንነትና የይገባኛል ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በአፋጣኝና በዘላቂነት ሊፈታ እንደሚገባም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ከዚህ አኳያ ተፈናቃዮችን በአጭር ጊዜ ወደቀያቸው የመመለስ ጉዳይ ቅድሚያ ተሰጥቶት በሚፈፀምበት አግባብ ላይ መተማመን ላይ መደረሱም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በብሔራዊ ደረጃ ይህን እንዲያስፈፅም የተቋቋመው ኮሚቴ በቋሚ የጊዜ ሰሌዳ እየተገናኘ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለጉዳዩ እልባት እንዲሰጥ በዛሬው ዕለት በተደረገው ስብሰባ መወሰኑን ከብሔራዊ ኮሚቴው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ብሄራዊ ኮሚቴው የትግራይ መንግስት እና ህወሀት እያንዳንዱን ኢንች የትግራይን ግዛት በሚቻለው መንገድ ሁሉ በሰላማዊም ሆነ በሌላ አካሄድ ለማስመለስ ሁሉንም እናደርጋለን” ማለታቸውን ትተው ነው ወይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከአማራ ክልል መስተዳድር ጋር ተፈናቃዬችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የተስማማው ሲሉ የሚጠይቁ በርካቶች ናቸው። en