ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር  ሚኒስትራቸውን ከስልጣናቸው አባረሩ

ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር  ሚኒስትራቸውን ከስልጣናቸው አባረሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የገንዘብና ፕላን ሚንስትራቸውን ባክ ባርናባ ቾልን በሁለት መስመር ደብዳቤ ከስልጣናቸው በማባረር በዳንኤል ዳንኤል ቹንግ ኢንጅነር ተክተዋል።

በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ  አርብ መጋቢት ፮ ቀን ፪ሺ ፩፮ በተሰጠው ፕሬዚዳንታዊ መግለጫ ሳልቫ ኪር የፋይናንስ ሚኒስትሩን ከስልጣን ለማባረር ምንም ምክንያት አልሰጡም። ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ፕሬዚዳንት ከሆኑ  ይሄኛው ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ ነው የገንዘብ ሚንስትራቸውን ሲሾሙና ሲሽሩ።

አዲሱ የገንዘብ ሚኒስትር ቀደም ሲል የፔትሮሊየም ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ በፔትሮሊየም ሚኒስቴር የቴክኒክ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። en

LEAVE A REPLY