ከሃያ የሚበልጡ የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት የጋራ የጦር ልምምዱ፥ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሽብርተኛ ቡድኖችን ለመዋጋት አስፈላጊውን ዝግጁነት እና ትብብር ለመገንባት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኀይል የአፍሪካ ዕዝ አፊሪኮም “ጀስቲፋይድ አኮርድ”(Justified Accord) የተሰኘ ስያሜ ይኸው ዓመታዊ ልምምድ፣ ዕዙ እስከ አሁን ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ካካሔዳቸው ሥልጠናዎች ሁሉ ትልቁ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ (EN – ኢትዮጵያ ነገ)