በኬኒያ የሀኪሞች የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል!!

በኬኒያ የሀኪሞች የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል!!

የኬንያ የህክምና ባለሙያዎች ፋርማሲስቶች እና የጥርስ ሀኪሞች ህብረት የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።

የኬኒያ የህክምና ባለሙያዎች የስራ ላይ የመድህን ዋስትና ሽፋን ለመጠየቅ እና መንግስት እስካሁን 1,200 የህክምና ባለሙያዎችን አልቀጠረም በሚል የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው።

የህብረቱ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ዴቪድ ቢሂጂ እንዳሉት 4,000 ዶክተሮች የስራ ማቆም አድማውን  ተካፍለዋል።  መንግስት ጥያቄያቸውን እስካልመለሰ የስራ ማቆም አድማው እንደሚቀጥል የተናገሩት የህብረቱ ተወካዬች  አንዳንድ ዶክተሮች ግን በፅኑ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ያሉ ታካሚዎች እንዳይሞቱ ለማድረግ ተረኛ ሆነው  በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

እ.ኤ.አ. በ2017፣ በኬንያ የህዝብ ሆስፒታሎች ዶክተሮች የተሻለ ደሞዝ ለመጠየቅ እና በሀገሪቱ የተበላሹ የህዝብ ጤና ተቋማትን ወደ ነበረበት ለመመለስ መንግስት ለ100 ቀናት የዘለቀ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። 

ከፍተኛ የሆነ የጤና ባለሙያዎችን እጥረት ለመቅረፍም ተከታታይነት ያለው ስልጠና እና የሀኪሞችን መቅጠር እንደሚያስፈልግ ጠይቀው ነበር። መንግስት ጥያቄያቸውን እንደሚመልስ ቃልገብቶ ቃሉን ባለማክበሩ የሥራ ማቆም አድማው እንደተጠራ የህብረቱ አመራሮች ተናግረዋል ። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY