ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን በጸጥታ ስጋት ሳቢያ የነዋሪዎች የዕለት’ተለት እንቅስቃሴ መገደቡንና ውጥረት መስፈኑ ተሰማ።
በክልሉ ዋና ከተማ ውጥረት የተፈጠረው፣ አንድ የከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ አባል ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ እንደኾነ ይነገራል። በከተማዋ ትናንት አንዳንድ የንግድ ተቋማት ተዘግተው እንደነበርም ምንጮች ይናገራሉ።
ሰሞኑን የጋምቤላ ክልል አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለመገምገም ወደ ክልሉ ያመራው የፌዴራል መንግስቱ ከፍተኛ ልዑክ የክልሉ ሰላም ወደ አስተማማኝ ደረጃ መሸጋገሩን አረጋግጫለሁ ማለቱ አይዘነጋም ።