የትግራይ ጡረተኞች ጡረታ ሊከፈላቸው ነው

የትግራይ ጡረተኞች ጡረታ ሊከፈላቸው ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ጡረተኞች ጡረታ እንዲከፈላቸው የተወሰነ መሆኑን  የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታና የጡረታ ፈንድ የቦርድ አባል ዶክተር እዮብ ተካልኝ ገለፁ። 

ውሳኔው  ከፕሪቶሪያው የስላም ስምምነት በፊት ክፍያ ተቋረጦባቸው የነበሩ ጡረተኞች፤ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው እንደሚገኙ በመግለጽ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል ።

መጋቢት፮ቀን፪ሺ፩፮ ከትግራይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በተወያዩበት መድረክ ላይም ጉዳዩ ተነስቶ ነበር።

በሚቀጥሉት ሳምንታት ክፍያ ይፈፀምላቸዋል ተብሏል። ውሳኔው በመንግስት ተቋማት እና በግል ድርጅቶች ይሰሩ የነበሩ ጡረተኞችን ያጠቃልላል ተብሎል። (EN – ኢትዩጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY