በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን ግጭት ተቀስቀሰ! 

በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን ግጭት ተቀስቀሰ! 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከማርች 9 ቀን2024 ጀምሮ  በአማራ ክልል በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዞን ጂሌ ጥሙጋ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች እና በክልሉ ፖሊስ እና የአካባቢ ሚሊሻዎች እያካሄዱት ባለው  ጥቃት 27 ሰዎች ሲገደሉ ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተዘገበ።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቆላሺ መንደር ነዋሪ  እንደተናገሩት በመንደሩ ማርች 9 ቀን 2024 በደረሰው የመጀመሪያው ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን ሌሎች ሁለት ቆስለዋል።

ጥቃቱ በወረዳው በሚገኙ በርካታ መንደሮች ተዛምቶ ለበለጠ የሰው ህይወት፣ ለቤት መቃጠልና ውድመት እንዲሁም ለንብረት ዝርፊያ መዳረጉን ነዋሪው አክለው ገልጸዋል።

እንደ ነዋሪው ገለጻ፣ ከመጋቢት 09 ቀን ጀምሮ በተከታታይ  10 ቀናት ውስጥ 27 ሰዎች በተለያዩ መንደሮች ተገድለዋል፣ ሌሎች 40 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ተርፈዋል።  ከተጎጂዎቹ መካከል ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋውያን እንደሚገኙበት ተነግሯል።

በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል 20 የሚሆኑ ግለሰቦች በአዳማ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን  ነዋሪዎች ተናግረዋል። የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖችን ለመደገፍ አንዳንድ በጎፉ ቃደኞች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቆል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY