ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ቴኒ የአሜሪካ የእንግሊዝ እና የኖርዌይ መንግስታት በደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ምርጫ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተከትሎ ማክሰኞ ዕለት በጁባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሻሻለው የሰላም ስምምነት ፓርቲዎች በምርጫ የጊዜ ሰሌዳ እና የሰላም ፍኖተ ካርታ ማሻሻያ ላይ ለመስማማት ድርድር እንዲደረግ ጠይቀዋል።
በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ የተካፈሉ ወገኖች በሙሉ እንዲወያዩበት ከአጋር መንግስታት ያቀረቡትን ሃሳብ በደስታ መቀበላችንን እና ድጋፋችንን መግለጽ እፈልጋለሁ” ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንት ሬሪክ ማቻር ቴኒ ለኢስት አፍሪካ ስታንዳርድ።