ኢትዮጵያ የኑሮ ደህንነት ከሌላቸው ሀገራት 130ኛ ደረጃ ያዘች

ኢትዮጵያ የኑሮ ደህንነት ከሌላቸው ሀገራት 130ኛ ደረጃ ያዘች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በ2024  ዓመተ ምህረት የዓለም አቀፍ ደረጃ የ 143 ሀገራት  ላይ በተካሄደ ጥናት በአለም ዙሪያ ካሉ ሀገራት የደስታ እና  የህዝብ የኑሮ ደህንነት ላይ በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ ደስታ ከራቃቸው ሀገራት ተርታ መሰለፍዋ ተገለፀ።

ሪፖርቱ ሀገሪቱ ደስተኛ ማህበረሰብን ለማፍራት ያጋጠሟትን ተግዳሮቶች በዘርዝር  አብራርቷል።

እንደ ድህነት፣ ስራ አጥነት፣ መፈናቀል ግጭት እንዲሁም ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እና የትምህርት ተደራሽነት ውስንነት፣ እንዲሁም የፖለቲካ አለመረጋጋት ያሉ ጉዳዮች የኢትዮጵያውያንን አጠቃላይ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጿል በሪፖርቱ።

እነዚህን ተግዳሮቶች መፍታት እና የዜጎችን ደስታና ደህንነት ለመመለስ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY