የተቃዋሚው መሪ ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ሆኑ!! 

የተቃዋሚው መሪ ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ሆኑ!! 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሴኔጋል በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ  የተቃዋሚ ፓርቲው እጩ ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ማሽነፋቸው ተገለፀ።  

ከእስር ከተፈቱ ከቀናት በኋላ በተካሄደው ምርጫ ያሽነፉት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የሴኔጋል ፕሬዚደንት ለመሆን ተዘጋጅተዋል።

በሴኔጋል  ታሪክ ውስጥ በእድሜ ትንሹ ፕሬዚደንት የሚሆኑት የተቃዋሚው እጩ አሸናፊነት ሀገሪቱን የምትመራባቸው በርካታ  ፖሊሲዎችን ላይ ስርነቀል ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች እንዲተገበሩ  ያደርጋሉ  ተብሎ ይገመታል።

ፌይ በአገር አቀፍ ደረጃ በምንም አይነት ኃላፊነት ላይ ተመድበው ስርተው  አያውቁም እና ለሶስት አመታት ብጥብጥ እና የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ ከተካሄደው የእሁዱ ምርጫ ግን አሽንፈዋል።

በስልጣን ላይ የሚገኝው የገዢው ፓርቲ ዋና ፕሬዚዳንታዊ እጩ አማዱ ባ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ፋዬን ማሸነፋቸውን አውቀው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አዲሱ የሴኔጋል ፕሬዚዳንት  ባሲሩ ዲዮማዬ ፌይ 44ኛ ልደቱን ባከበረበት ቀን ማርች 25 ቀን2024  ፕሬዝዳንት ሆነውመምረጣቸው ሴኔጋላውያንን እያነጋገረ ነው።

LEAVE A REPLY