የወልቃይት ጠገዴ እና ሲቲት ሁመራ ውዝግብ  ቀጥለዋል 

የወልቃይት ጠገዴ እና ሲቲት ሁመራ ውዝግብ  ቀጥለዋል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን  ዘላቂ ማንነቱ አማራነቱ እንደሆነ እንዲረጋገጥ የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የአማራ ክልል በመግለጫው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጠብ ጫሪ የሆኑ ተግባራት እየተፈፀመብኝ ነው ሲል የክልሉ መንግስትን አስጠንቅቋል። 

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን  ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የዞኑ አመራሮች እና የመንግሥት ሠራተኞች በተገኙበት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች የዞኑ ሕዝብ ባለፈው የአገዛዝ ሥርዓት የደረሰበት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በርካታ መኾኑን አንስተው  መንግሥት በደል የደረሰበትን ሕዝብ ችግሮች በመመልከት መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ሰላምን በማስጠበቅ በጦርነት ወቅት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን በማይነጥፈው የሕዝብ ድጋፍ  በመገንባት ለጠንካራ የሀገረ መንግሥት ግንባታ በትብብር እንደሚሠራም ተናግረዋል።

በመድረኩም የአማራ ክልል ምክትል አፈጉባኤ አማረ ሰጤ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ደሴ ጥላሁን (ዶ.ር) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው ተገኝተዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ የጎንደር በጌምድር አማራ ለመኾኑ ብዙ ታሪካዊ ማስረጃዎች አሉ ያሉት የዞኑ አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው እውነተኛ የሆነ የማንነት ጥያቄ ትግል መቸም አይሸነፍም ብለዋል።

ዘመኑን በዋጀ ሁኔታ ሰላምን እና ኅብረ ብሔራዊነትን በማስቀጠል የዘመናት ጥያቄያቄዎች እውን እንዲኾኑ ሁሉም በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል። 

የአማራ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ አማራ ለመኾኑ ከሰዎች ምስክርነት ባለፈ እንደ ጎንደር ቤተ መንግሥት የታነፀው የአያና እዝጊ ቤተ መንግሥት ምስክር ነው ብለዋል። ወጉ፣ ባሕሉ እና ማንነቱም አማራ ነው ያሉት አፈ ጉባኤው መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልላዊ መንግስት አስተዳደር በመማሪያ መጽሐፍት ላይ  የትግራይ ክልል አካል የሆኑ አካባቢዎችን በካርታው ውስጥ አካቶ አውጥቷል ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ድርጊቱን «ጠብ አጫሪነት» ሲል  ከሰሰ። 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ የአማራ ክልል መንግስት የትግራይ ክልል አካል የሆነ መሬት በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ማካተቱን እንደተገነዘበ  አስታውቋል። የአማራ ክልል መንግስት በሐይል በተቆጣጠራቸው ባላቸው አካባቢዎች “እየፈፀመ በመጣው ግፍ እና መከራ ከመቆጨት ይልቅ፥ ወደ ሌላ ታሪካዊ ስህተት መግባቱ በቀጣይነት ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን በመገንዘብ በፍጥነት ሊያርመው ይገባል” ሲልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቃውሞውን ማሰማቱ ተዘግቦል።

LEAVE A REPLY