ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ለማስማማት ጅቡቲና ኬኒያ እየጣሩ ነው!! 

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ለማስማማት ጅቡቲና ኬኒያ እየጣሩ ነው!! 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እንደተናገሩት ሶስተኛ ወሩን የያዘውን የሶማሊያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እልባት እንዲያገኝ የጅቡቲ እና የኬንያ መንግስታት መሪዎች እየጣሩ ነው ሲሉ ተናገሩ።

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የጅቡቲ እና የኬንያ መንግስታት በሁለቱ መንግስታት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተወግዶ ወደ ቀድሞ  ወደነበረበት ለመመለስ ጠንክረው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል ።  ግጭቱ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል። 

የጅቡቲው ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ እና የኬኒያው ዊልያም ሩቶ ቀደም ሲል በሁለቱ ሀገራት መካከል  የነበረው መልካም ግንኙነት እንዲመለስ ሁለቱን መንግስታት ለማስታረቅ በጋራ እየሰሩ ናቸው ።

ይህንን እንቅስቃሴ ተከትሎ  የኢትዮጵያን መንግስት እናየሶማሊያ የመንግስት በተናጥል ማወየየታቸው ሲታውስ በቅርቡ በጅቡቲ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የሚገናኙበት ሌላ ስብሰባ በጅቡቲ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY