ቦሌ አካባቢ የፋኖ ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጥ ተሰውተዋል

ቦሌ አካባቢ የፋኖ ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጥ ተሰውተዋል

4 ሰው ሞትዋል 3 ስው ቆስሎል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ  ረፋድ ላይ ድብልቅልቅ ያለ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተነገረ። የተኩስ  ልውውጡ የተካሄደው በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ሀይላት መካከል መሆኑ ታውቋል።

የፋኖ ታጣቂዎች የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ  ባለመሆናቸውና ተኩስ በመክፈታቸው ፖሊስ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ሻለቃ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት የፋኖ አባላት በአዲስ አበባ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ ዲዛዬር መኪና በመጠቀም ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል መሞቱን እንዲሁም አቤኔዘር ጋሻው አባተ የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ፖሊስ  ያስታወቀው፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በፋኖ በኩል በቀጥታ የተገለጸ ነገር ባይኖርም በአንዳንድ የፋኖ ድጋፍ አስተባባሪዎች በኩል የሚሰጡ መግለጫወች ፋኖ በአዲስ አበባ ኦፕሬሽን ላይ የነበሩና በሻለቃ ናሁሰናይ የሚመራ ቡድን የተሰጠውን ኦፐሬሽን መፈፀሙንና በጀግንነት የተሰው መሆኑን አመላክተዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የመንግስት የፀጥታ የጋራ ግብረኃይል በአዲስ አበባ የተደራጁ አካላትን በቁጥጥር ስ ማዋሉን ገልፆ በአዲስ አበባ የሚያሠጋ ምንም አይነት የፀጥታ መደፍረስ አንደሌለ ከመገለፁም በላይ ቀለል ያለ ችግር መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ ሰዎች ፖሊስ በዛሬ መግለጫው በእርግጥም የፋኖ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ እንደተጀመረ ያመነበት መግለጫ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY