ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጠላት የሆኑ ሐይሎች ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ ነው ሲሉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሱ።
የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል በተያዙ የትግራይ ግዛቶች፥ እየታየ ያለው ክስተት በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር አልያም በህወሓት፥ ወይም ደግሞ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው በይፋዊ ማሕበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ ክስተቱ ሁለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የሚፈልጉ “የስምምነቱ ጠላቶች” የፈጠሩት ነው ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ጨምረውም ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የጋራ መግባባት ለመገንባት ሁለቱ ወገኖች አሁን ላይ በአዲስ አበባ እየመከሩ መሆኑ ጠቁመዋል።
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በትግራይ ደቡባዊ ዞን በሚገኙ እና ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች በጦር መሳርያ የታገዘ ግጭት እየታየ መሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሩቅና ቅርብ ያሉ የሰላም ስምምነቱ ጠላቶች ያልዋቸው ሐይሎች ያለው ብቸኛ አማራጭ ሰላም መሆኑ መገንዘብ እንዳለባቸው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ጨምረው ገልፀዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)