ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ኦሲስ የታሽገ ውሃ ፋብሪካ ማናጀር ኢንጂነር ወልደፂዮን ግደይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ አስከሬኑ ተጥሎ መገኝቱን አይ ሬዲዬ ዘገበ።
ኢንጂነር ወልደፂዮን ግዳይ በ 1980 ዓ.ም በኩባ ሳንቲያጎ ዩኒቨርስቲ የኢንጂነሪንግ ፋኩልቲ ከተመረቀ በኋላ በመጀመሪያ በአሥመራ ሳባ መሥታወት ፋብሪካ በኋላ በአዲስ አበባ ጠርሙስና ብርጭቆ ፋብሪካ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ያገለገለ ሲሆን በኢትዮ-ኤርትራ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ወደ ኤርትራ በማቅናት ከዛም ወደ ደቡብ ሱዳን በማምራት የ ታሽገ ውሀ ፋብሪካ በመክፈት የተሳካ የንግድ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደነበር ወዳጆቹ ይናገራሉ።

የጁባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንጂነር ወልደፅዬን ግዳይ አስከሬን ምርመራ ማድረጉንና የገዳዩን ማንነት በማጣራት ላይ መሆኑን የአይ ሬዲዮ ዘግቧል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)