በስሜን ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት አልተቻለም 

በስሜን ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት አልተቻለም 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ  ቃጠሎ በፓርኩ ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም ምሽት  ሦስት ሰዓት ጀምሮ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱንና ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ የደረሰን ዜና ያስረዳል። 

በጣም ከፍተኛ ሥፍራ በመኾኑ ጠፋ ሲባል መልሶ በመቀጣጠል እንደሚሰፋም ገልጸዋልና ቃጠሎው እየሰፋ ሲሄድ  በሰው ኃይል መቋቋም የሚቻለውን ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ሰው በማይደርስባቸው ገደላማ አካባቢዎች ያለውን እሳት ግን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ነው ተብሏል።

ቃጠሎውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት ከፍተኛ የሕዝብ ንቅናቄ እንደሚጠይቅም አንስተዋል። ከዞኑ አቅም በላይ የሚሆንበት እድል ከተፈጠረ እገዛ እንፈልጋለን ነው ያሉት የአካባቢው ማኅበረሰብ የዓለም ሀብት የኾነውን ታላቅ ስፍራ ከቃጠሎ ለመታደግ ቃጠሎውን በአጭሩ ለማስቆም የክልል እና የፌዴራል ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY