ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ ከአራዳ ጊዬርጊስ ቤተክርስቲያንን ይዞታ በላይ ቤተልሔም የህዝብ ትምህርት ቤትን ይዞ ግዳም ሰፈር እንዲሁም ዳትስን ሰፈር እና የተለያዩ አካባቢዎች «ለልማት» በሚል በወራት ውስጥ ቤቶችን የማፍረሱና ነዋሪዎችንም የማንሳት ሥራ እንደሚጀመር ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአዲስአበባ መስተዳድር በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ባለግል ይዞታዎች ምትክ ቦታ እና ግምት ለመክፈል እንዲሁም የቀበሌ ቤት ነዋሪዎች ምትክ ቤት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል።
ፒያሳ አከባቢ የተነሱ ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ በመኖሪያ እጦትና ተማሪወች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ እንደተገደዱ ይታወቃል። መንግስት አካባቢውን ለማልማት ሲያቅድ ቅድመ ሁኔታ ሲያመቻች በዘፈቀደና ሀላፊነት በጎደለው ግዴለሽነት መተግበሩ ብዙ ትችት ሲቀርብበት እንደነበር አይዘነጋም።
በተመሳሳይ በሰሜን ማዘጋጃና በሰሜን ሆቴልን አካባቢ ህይውት ሆቴል እና ወይዘሮ ቀለምወርቅ ትምህርት ቤት ድረስ ያለው ሰፈር ነዋሪዎች እንደሚነሱ ነዋሪዎች እንደተነገራቸው ለኢትዮጵያ ነገ ተናግረዋል።( enኢትዮጵያ ነገ)