ከቻይና ወደ ኬንያ የሚገቡ ሳልቫጅ ልብሶች ፈላጊያቸው መጨመሩ ተዘገበ

ከቻይና ወደ ኬንያ የሚገቡ ሳልቫጅ ልብሶች ፈላጊያቸው መጨመሩ ተዘገበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኬንያ  የአልባሳት ፍላጎትዋና ምንጭ የሆነውየሳልቫጅ  እልባሳት የግብይት ፍላጎትበ 86.2 በመቶ ጨምሯል በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፍላጎት ጭማሪ ባሳየው የሳልቫጅ አልባሳት አቅርቦትን ቻይና በአንድኝነት መቆጣጠርዋን ተገለፀ።

ከቻይና ባለስልጣናት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሀገሪቱ በ22.732 ሚሊዮን ዶላር  ወይንም(3.03 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ) ዋጋ ያለው 31,594 ቶን ሳልቫጅ ልብስ እና ጫማዎችን  በጃንዋሪ እና መጋቢት 2024 ባሉ ሶስት ወራት ወደኬንያ ልካለች።

እ.ኤ.አ. በ2023 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከቻይና የገቡ የሳልቫጅ  ልብሶች ዋጋ 20.651 ሚሊዮን ዶላር (2.768 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ) በ16,962 ቶን የሚደርስ የሳልቫጅ አልባሳትና ጫማዎች ከቻይና ወደ ኬኒያ መግባቱን ከቻይና መንግስት የተገኝው መረጃ ያሳያል ።

በተለምዶ ሚቱምባ በመባል የሚታወቁት ስልቫጅ  ልብሶች በተለይ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ተመራጭ ሆነዋል ምክንያቱም ከአዳዲስ ልብሶች ጋር ሲነፃፀሩ ዋጋው ዝቅተኛ ነው.

በኬንያ   የሳልቫጅ አልባሳት ንግዱ ብዙ ቢሊዮን ሽልንግ የሚያንቀሳቅስ የንግድ ዘርፍ ሲሆን በ ኬኒያ መንግስት ግምት ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን በዚሁ የሥራ ዘርፍ መስማራታቸውን የሚያሳዩ የዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ ።ሳልቫጅ ልብሶች ንግድ የሚካሄድባቸው  ከ በመላ ሀገሪቱ ባሉዋና ዋና የገበያ ቦታዎች እና እንደ ጊኮምባ፣ ኢስትሊግ፣ ሙቱርዋ እና ቶይ ካሉ የገበያ ማዕከሎች እንዲሁም በናይሮቢና በሌሎች ከተሞች  በመንገድ ዳር እና በመኖሪያ አካባቢዎች ይካሄዳል።

  እ.ኤ.አ. በ2022 177,664.4 ቶን ሳልቫጅ ልብሶችን ወደ 19.9 ቢሊዮን የኬኒያሽልንግ የሚያወጣ 

  ግብይት ኬንያውያን ነጋዴዎች ማካሄዳቸው ሲታወቅ ወደ ኬንያ የሚገቡ ልባሽ ሳልቫጅ  ልብሶችን ወደ ኬንያ በመላክ ቻይና የመሪነቱን ቦታ የምትይዝ ስትሆን አሜሪካ፣ ካናዳ እና የአውሮፓ ህብረት  ሀገራት  በቅደም ተከተል ዝቅተኛ ዋጋ ያለው  የሳልቫጅ አልብሳትን ለኬንያ ገበያ በአቅራቢነት እንደሚሳተፉ በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ ።

የሳልቫጅ አልባሳት ግብይቱ  እየጨመረ በሄደ ቁጥር በኬንያ የሚገኙ  የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ህልውናቸው ለአደጋ እንዲጋለጡ አድርግዋል ፣ ይህም ማለት የኬንያ ህዝብ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እየጨመረ ያለውን የአልባሳት ፍላጎት ለማሟላት  የሚያስችለው አቅምና አትራፊነት እያሳጣቸው   ማምረት እንዳይችሉም.አድርጎ ቸዋል።

ኬንያ ፋይበርን ወደ ክር የሚቀይሩ 52 የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች አሏት ነገርግን 15ቱ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን 37ቱ ፋብሪካዎች ምርት ማምረት ማቆማቸውንየኬንያ የህዝብ ፖሊሲ ​​ጥናትና ትንተና ተቁዋም ይፋ አድርጎል።

በተጨማሪም በዝቅተኛ የሰው ኃይል ምርታማነት እና ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ ምክንያት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የሚሠሩት ካላቸው የማምረት አቅም 45 በመቶውን ብቻ ነው. እየተጠቀሙ ያሉት የኬኒያ”የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው እንደ ከፍተኛ የኤሌክትሪክፍጆታ  ወጪዎች ያእና የጥሬእቃ ግብይቱ ዋጋ መናር እንዲሁም የሀገሪቱን ብሎም ደቡብ ኢትዬጵያ ድረስ የዘለቀው የሳልቫጅ አልባሳት ግብይት የኬኒያ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ህልውናን እየተፈታተነው እንደሚገኝ የኬንያየህዝብ ፖሊሲ ​​ጥናትና ትንተና ተቁዋም   ኪፕራ  ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን ይፈ እድርጎል። 

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኬንያውያን ዜጎች መተዳደሪያ የሥራ ዘርፍ  የሆነው የሳልቫጅ አልባሳት ንግድ፣ የአፍሪካን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪን  ህልውና የሚፈታተን አህጉር አቀፍ ችግር ወደመሆን የተሸጋገረ ፈተና  ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY