ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በትላንት ምሽት አርሰናልን ቸልሲን 5-0 በማሸንፍ ባሳየው አስደናቂ ብቃት ፈነጠዙ።
ፖል ካጋሜ የአርሰናል እውቅደጋፊ ናቸው። ሩዋንዳን በተደጋጋሚ ከሚጎበኙ የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች አንዱ እና ግንባር ቀደሙ አርሴናል እግርኳስ ቡድን ነው።
“መአን….እኛ የምንወዳቸው # Gunners ናቸው…!!!” ካጋሜ በ X (የቀድሞው ትዊተር) መለያ ግጥሚያውን ተከትሎ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
ባለድሉ አርሰናል ከ34 ጨዋታዎች በኋላ በ77 ነጥብ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዡንበበላይነት እንዲይዝ አስችሎታል።
ሚኬል አርቴታ አርሰናልን ከ2003/04 ከማይበገር የነበረው አርሴናል ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ ከሃያ እመት በኋላ የመጀመሪያውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ እንዲያሸንፍ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክለቡን እያስተናገደ ያለው አካሄድ ካጋሜን ጨምሮ ለክለቡ ያለውን ፍቅር ከማሳየታቸውም በላይ የክለቡን ደጋፊዎች አስደምሟል።
ከሩዋንዳ ጋር ስትራቴጂካዊ የቱሪዝም አጋርነት ካላቸው የአውሮፓ ቡድኖች መካከል አንዱና ግንባርቀደሙ አርሴናል ነው ። ከቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እና የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን የእግርኳስ ቡድኖችም የሩዋንዳ ስትራቴጂካዊ የቱሪዝም አጋርነት ስምምነት አላቸው።
ከ 2018 ጀምሮ ከሩዋንዳ መንግስት ጋርባለው ስምምነት መሰረት ፣ የእንግሊዙ ክለብ አርሴናል በሁሉም የእግርኳስ ቡድን፣ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን እና የአርሴናል የሴቶች የእግርኳስ ቡድን ማሊያዎች በግራ እጅጌ ላይ “ሩዋንዳ ጎበኙ” የሚል ፅሁፍን አጥልቀው ይጫወታሉ።(EN – ኢትዮጵያ ነገ)