በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን ታብሌት ሊሰጥ ነው

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን ታብሌት ሊሰጥ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢንጂነር ታከለ ኡማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን የትምህርት ዝግጅትና ቁጥጥር የሚያደርጉበት በተጨማሪም የትምህርት እቅድ ለማውጣት የሚያስችላውን ታብሌት እሰጣለሁ እያለ ነው::

በአዲስ አበባ ያለውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ሰጥቼ እየሠራ እንደሆነ የሚናገረው መሰተዳድር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በከተማዋ ለሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤት መምህራን የትምህርት ዝግጅት እና የትምህርት እቅድ የሚያወጡበት ታብሌት ለመስጠት ዝግጅቴን አጠናቅቂያለሁ ብሏል::

ዕቅዱን እውን ለማድረግ የሚያግዙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን ታብሌቶቹ በሳተላይት የሚገናኙና መረጃዎችን ወደ ማዕከል የሚልኩበት መተግበሪያዎችም ተካተዋል:: ከታብሌቶቹ በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ዓርማ ያረፈበት ቦርሳ እና ደረጃውን የጠበቀ ጋዎን ለአዲስ አበባ መምህራን ያቀርባል::

በመምህራን የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለመመለስም የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆመው የከንቲባው ጽ/ቤት መግለጫ በ2012 ዓ.ም ለመምህራን ቁሳቁሶች የማሟላቱ ተግባር የከተማ አስተዳደሩ በአዲሱ አመት በከተማዋ ለሚገኙ 600 ሺህ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደንብ ልብስና የመማሪያ ቁሳቁሶች የማቅረብ ፕሮጀክት አካል ነው ሲል ተያያዥነቱን ይፋ አድርጓል::

ከመምህራን የዲስፕሊን ጉድለት እና የሙያ ብቃት የተያያዙ ከህዝብና መንግሥት ያልተሰወሩ በርካታ ችግሮችን መፍታት ያልቻለው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ታብሌቱ ብቻውን የትምህርት ጥራቱን የሚቀርፍ ይመስል መጣደፉ ከወዲሁ ትዝብት ላይ እየጣለው ነው::

ከኢህአዴግ ባለሥልጣናትም ሆነ ከአዲስ አበባ የ27 ዓመት ከንቲባዎች ሁሉ ለነዋሪው የሚጠቅም ነገር በመሥራት አድናቆት ካገኙት አርከበ ዕቁባይ ጋር ለመመሳሰል እና እግረ መንገድም ” ከፊንፊኔ ኬኛ” ፖለቲካ ገለል ባለ መልኩ ራሳቸውን በማሣየት ትርፋማ መሆን ይፈልጋሉ ተብለው የሚታሙት ም/ ከንቲባ ታከለ ኡማ ለመንግሥት ት/ቤት ተማሪዎች በጠቅላላ የደንብ ልብስ ለማልበስ የወሰዱት ዕርምጃ ብዙዎች ተደንቆላቸዋል::

LEAVE A REPLY