አቶ ሙስጠፌ አምስት አዲስ ሹመት ሰጡ፤ ሁለት የምክር ቤቱ አባላት ያለመከሰስ...

አቶ ሙስጠፌ አምስት አዲስ ሹመት ሰጡ፤ ሁለት የምክር ቤቱ አባላት ያለመከሰስ መብት ተነስቷል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አራተኛው አስቸኳይ ጉባዔ የቢሮ ሓላፊዎችን ሹመትና ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል:: በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ  ሙስጠፌ መሐመድ የቀረቡለት ሓላፊዎችን ሹመት ያፀደቀው የክልሉ ምክር ቤት፤ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች እንደገና ለማደራጀት ሥልጣንና ሓላፊነት ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ ዓዋጅ ካፀደቀ በኋላ ነው::

የለውጡ ትክክለኛ አስቀጣይ መሆናችው የሚነገርላቸው ሙስጠፌ መሐመድ ተሿሚዎቹ ን ባላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና የፖለቲካ ብቃት መሠረት በማድረግ ለሓላፊነት እንዳጯቸው ገልጸዋል::

በመመዘኛው መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ አግኝተው የተሾሙት

አቶ አብዲቃድር ሐሺ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ

አቶ ሱቤር ሁሴን – የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሓላፊ

አቶ ጠይብ አህመድ ኑር – የእንስሳት ልማት ቢሮ ሓላፊ

አቶ አብዲሰላም ዩሱፍ – የኢንቨስትመንትና ዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ

አቶ ሩብሌ አዋሌ– የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሓላፊሆነው የተሾሙ ሲሆን፣

ዶክተር ዩሱፍ መሐመድ የጤና ቢሮ ሓላፊ፣ ዶክተር አብዲቃድር ኢማን  የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ፣ ወይዘሮ ዘይነብ ሐጂ አደን የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሓላፊ፣ አቶ ሙበሽር ዱበድየፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሓላፊ፣ አቶ ኤልያስ አቢብ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊ፣ አቶ ሐሰን መሐመድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሓላፊ በነበሩበት የተጠቀሱት ቀደምት ሓላፊነቶቻቸው ላይ እንዲቆዮ ተደርጓል:: በተጨማሪም ስምንት የቢሮ ሓላፊዎች ሽግሽግ ተካሂዷል::

በተያያምዘም ምክር ቤቱ በሰብኣዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ኹለት የምክር ቤቱ አባላትን  ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል:: የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ ዓዋጅንም ጉዳዮ ለሚመለከተው የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስተላልፏል::

LEAVE A REPLY