የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክክር አደረገ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክክር አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር እያደረገ እንደሚገኝ ታወቀ::

ዛሬ በተጀመረው ውይይት የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የምርጫ እና ስነ ምግባር አዋጅ አጠቃላይ ገጽታ ላይ ውይይት እያካሄደ መሆኑን ካነጋገርናቸው የዜና ምንጮች መረዳት ችለናል፡፡

አዲሱን የምርጫ እና የስነ ምግባር አዋጅን በመቃወም ከሳምንታት በፊት ሰላሳ ሁለት ድርጅቶች በሕብረት አቋማቸውን ማሳየታቸው ይታወቃል:: መኢአድ ትዴት እና በመርሻ ዮሴፍ የሚመራው ኢሕአፓ ረቂቅ ከዋጁ አፋኝ ነው ማለታቸው አይዘነጋም::

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሚያደርጉት የስልጣን ፉክክር ባሻገር ለዜጎች መብት መከበር እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ በዛሬው ውይይት ላይ የተነሳ ሲሆን ፓርቲዎቹ በጋራ ምክር ቤቱ ውይይት ማጠናቀቂያ ላይ የአቋም መግለጫም ይሰጣሉ ተብሎ ተገምቷል::

LEAVE A REPLY