በፕሮቴስታንትነቱ የታሠረው ኤርትራዊ በዓዲ አቤቶ ማጓሪያ ሕይወቱ አለፈ
የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆኑ ብቻ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊው ተኪኤ ተስፋ ዮሃንስ በእስር ቤት ህይወቱ ማለፉ ታወቀ::
የእምነት ነፃነት እንደሌለባት በሚነገረው የኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ በፕሮቴስንታንት ተከታዮች ላይ የሚደርሰው ግፍ ጨምሯል ነው የተባለው:: የእስረኞች የእምነት መብት ተሟጋች ድርጅት ‘ሪሊዝ ኤርትራ’ ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሃነ አስመላሽ እንደሚናገሩት ከሆነበአስመራ በአንድ የግል መኖሪያ ቤት መቶ አርባ አንድ የሚጠጉ የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ ስብስባ ሊያካሂዱ ሲሉ የተያዙት ከአራት ወራት ገደማ በፊት ነበር።
አሁን ሕይወቱ ያለፈው ተኪኤ በወቅቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንዱ በዕምነታቸው ብቻ የተያዙት ግለሰቦች በሙሉ ዓዲ ዓቤቶ ወደተሰኘው እስር ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም የተወሰኑት ከቀናት በኋላ ሊፈቱ ችለዋል።
ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት የሆነው ሟች ተኪኤ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆኑ በአካል ጉዳኝነቱ ሳይበገር ሁለት አይነት ስራ እየሰራ ልጆቹንም እያሳደገ እንደነበር የቅርብ ጓደኛው ሃኒባል ዳንኤል ለቢቢሲ ገልጿል::ስክርነቱን ሰጥቷል።
በጉዳዮ ላይ ከኤርትራ ባለስልጣናት መረጃ ማግኘት ከባድ እንደሆነ የሚገልፀው አቶ ሃኒባል መሞቱ እንጂ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ህክምና እርዳታ ይደረግለት አይደረግለት፤ እንዲሁም መቼ እንደሞተ የሚታወቅ ነገር የለም በማለት እውነታውን አረጋግጧል:: በተጨማሪም ከጥቂት ወራት በፊትም ፍፁም የተባለ ሌላ ወንጌላውያን እምነት ተከታይ በዳህላክ እስር ቤት ህይወቱን እንዳጣም አስታውቋል።
እንግሊዘኛ፣ ሒሳብና ጆግራፊ ፈተና ውጤቶች ብቻ የዮንቨርስቲ መግቢያ እንዲሆኑ ተወሰነ
በውዝግብ እና በቅሬታ የከረመውን የ12ኛ ክፍል ፈተና እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ የሠጠው ሚኒስቴር መ/ቤቱ፤ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ እስካሁን ድረስ ሳይገለጽ ቢቆይም አሁን ላይ ግን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተሰጡ ፈተናዎች ብቻ የሚወሰን እንዲሆን አቋም ወስደናል ሲል ገልጿል::
ይህን መነሻ ባደረገ መልኩ እንግሊዝኛ፣ አፕቲቲውድ፣ ሂሳብ፣ ጂኦግራፊ እና ፊዚክስ ውጤቶች የተማሪዎቹን የዮንቨርስቲ መግቢያ ይወስናሉ ተብሏል። ከዛ በኋላ በተከታታይ ሁለት ቀናት የተሰጡት ፈተናዎች የውጤት መጋሸብ የታየባቸው ናቸው ሲልም ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው ከእነመልሱ መሰረቁን በተዘዋዋሪ ያመላከተ መግለጫ አሰምቷል::
መበቀጣዮ ምርጫ በማጭበርበር የሚታሙት ቀበሌና ወረዳዎች ከአሠራር ወጪ ሊደረጉ ነው
የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ያቀረቡበት የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች ህግ አስፈላጊው ውይይት እንደተካሄደበት ምርጫ ቦርድ አረጋገጠ::
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ቡርቱካን ሜዴቅሳ ጉዳዩን አስመልክተው ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ፤ በቅርቡ የፓለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ያቀረቡበት ፣ የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች ህግ ኢሕአዴግን ጨምሮ በሀገሪቱ ሕጋዊ ምዝገባ አካሂደው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎች በተገኙበት በተለያዮሦስት ጊዜያት አስፈላጊው ውይይት እንደተካሄደበትገልፀዋል።
ይህ እውነት ባለበት ሁኔታ ፓርቲዎቹ በኋላ ላይ “ህጉን አናውቀውም ፣ አልተሳተፍንበትም ” በማለት ያነሱት ቅሬታ ተገቢ አይደለም ያሉት ወይዘሪት ብርቱካን ፤ ከዚህን መሰሉ ወቀሳ ይልቅ ምን አልባት በቂ ውይይት አልተደረገም የሚል ቅሬታ ቢቀርብ እንደሚሻል ጠቁመው ፣ በሀገሪቱ ከሚገኙ ፓርቲዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በምርጫ ቦርድ እውቅና ባይሰጣቸውም በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ እና ከእስር ቤት የወጡ በመሆናቸው በሚዘጋጁ መድረኮች እንዲሳተፉ የተደረገ መሆኑንም አስታውሰዋል::
የቦርድ አመራረጥ፣ በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጫና ሳይደረግበት ገለልተኛ ሆነ እየሰራ ስለሚገኘው ተቋማቸው ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡት የምርጫ ቦርድ ፤ የህዝብ ቆጠራ ሳይካሄድ ሀገራዊ ምርጫ መካሄዱ ፣ በምርጫ ውጤት ላይ ለውጥ የሚያመጣው አሁን ያለው የህዝብ ቁጥር መረጃ ሳይሆን በምርጫው ለመሳተፍ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር ሊሆን እንደሚችል እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የህዝብ ቁጥር መረጃን፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ለማዘጋጀት እና የምርጫ አስፈፃሚዎችን ለማስተካከል ከስታቲስቲክስ እና ከሌሎች ተቋማት መረጃዎችን እንደሚሰበሰቡ ያሳወቁት ታሪካዊዋ የነፃነት ታጋይ የምርጫ ምዝገባ ሂደቱም ለጋዜጠኞች እና ፓርቲዎች ክፍት እንደሚሆን ፣ፓርቲዎች በዚህ ቅሬታ ካላቸውም ማቅረብ እንደደሚችሉጠቁመዋል:/
የሲዳማ ዞንን ህዝበ ውሳኔ በተመለከተ አስፈላጊውን በጀት የሚሸፍነው የክልሉ መንግስት ወይንም ምክር ቤት እንደሆነ ያሳወቁት ፤ የህዝበ ውሳኔው ጥያቄ ከክልሉ የመጣ እና ምርጫ ቦርድ በጀት ያልያዘለት በመሆኑ በጀቱ በክልሉ መንግስት ወይንም በምክር ቤቱ መሸፈኑ ግድ መሆኑ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ሲገልጹ አድምጠናል::
የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ሕይወት ከቀጠፈውና በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት ካወደመው ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ የሀብት ክፍፍልን በተመለከተ ፣ የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ከመስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም በፊት እንዲቀርብ ስምምነት ላይ መደረሱን ያሳወቁት የቀድሞ የቅንጅትና የአንድነት ፓርቲዎች ከፍተኛ ፤በሀገሪቱ ለሚካሄደው ምርጫ 250 ሺህ የምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚመለመሉ ፣ ይህንን ገለልተኛ ለማድረግ በርካታስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ይፋ አድርገዋል::
ቀደም ባሉት ጊዜያት በታችኛው እርከን የምርጫ ቦርድ ስራን በተለይ ቀበሌዎች እና ወረዳዎች ሲሰሩ እንደነበረ እና ይህም ገለልተኝነቱ ላይ ጥያቄ ሲያስነሳ በመቆየቱ፤ አሁን ላይ ግን ይህአሠራር እንዲቀር መወሰኑን ከጋዜጣዊ መግለጫው መረዳት ተችሏል::
ከነሃሴ 30 ቀን 2011 ጀምሮ የሲዳማን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መካሄድ የተጀመረ ሲሆን መስከረም 7 2012 ዓ.ም ደግሞ ፣ ህዝበ ውሳኔው ከመካሄዱ በፊት እና ከተካሄደም በኋላ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልጸዋል፡፡
በተቋሙ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ውጤቱ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን ፥ ምንም የሚያመጣው ተጽዕኖ አለመኖሩንና ትክክለኛ አካሄድና ፍትሃዊ ውሳኔ መሆኑም ተነግሯል :: ይህ የትምህርት ሚኒስቴር ያልተለመደ አሠራር ከወዲሁ በርካታ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በስፋት እያነጋገረ ነው።
መንግሥት ከጥንቃቄ ጉድለት ፈተናውን ለአደጋ ፣ እንዲሁም የቀጣይ ዘመን የትምህርት ወቅት መቃረቡ ይሄንን አማራጭ ለመጠቀም እንዳስገደደው አሰተያየታቸውን ያደረሱን የትምህርት ኤክስፐርቶች ለሁለት ጊዜያት ፈተናዎች መሰረቃቸው በቀጣይ የአገሪቱ የማትሪክ ፈተና እና የከፍተኛ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከባድ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ከወዲሁ አስታውቀዋል:: ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብም ይፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከአዲሱ ዓመት በፊት እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።
በቀጣዮ ምርጫ በማጭበርበር የሚታሙት ቀበሌና ወረዳዎች ከአሠራር ወጪ ሊደረጉ ነው