የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጳጉሜን 3 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጳጉሜን 3 ቀን 2011 ዓ.ም

በነዋሪው አየተተቸው የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ለ350 አባላቱ ማዕረጎችን አደለ

ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የከተማ መስተዳደር ድሬዳዋ ለ350 የፖሊስ ሠ ራዊት አባላት የተለያዮ ሹመቶችን ማንበሽበሿ ተሰምቷል::

የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ነው ዕድገቱ ይገባቸዋል ያላቸውን የፖሊስ አባላት የሾመው:: የሹመት ዕርከኑም ከረዳት ሳጂን እስከ ኮማንደር ድረስ የማእረግ እድገት እንዳካተተ ታውቋል::

 ከሁለት ወር በፊት የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ቀደም ሲል በሥነ ምግባር ጉድለት የተባረሩ በርካታ የሠራዊቱን አባላት ወደሥራ መመለሱን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ ማቅረባቸውን ኢትዮጵያ ነገ መዘገቧ አይዘነጋም:: የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የ2011 በጀት አመት የአፈፃፀምና የሪፎርም ሥራ የማጠቃለያ መድረኩን ዛሬ ሲያካሂድበመድረኩ ላይ በጡረታ ለሚሰናበቱ 23 አባላቱ የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀትን ጨምሮ ሙሉ ልብስና የአመት በአል ስጦታ አበርክቷል።

የድሬ ዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አህመድ ቡህና የንግድ ኢንዱስትሪና ንቨስትመንት ቢሮ ሓላፊ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ነተገኙ ሲሆን፤ የድሬ ዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አህመድ ቡህ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ በዓመቱ የገጠሙትን ፈተናዎች ተቋቁሞ ራሱን ለመለወጥና የተሸረሸረውን የህዝብ አመኔታ ለመመለስ ያደረገውን ጥረት አበረታተዋል:: ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ መሰዋእትነት በመክፈል ጭምር ለተጫወተው በጎ ሚና ምክትል ከንቲባው በከተማ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በክብር በጡረታ ለሚሰናበቱ የፖሊስ አባላት እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ በማለት ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ አህመድ ቡህ፥ የማእረግ እድገት ላገኙ አባላትም እንኳን ደስ በማለት በተቀበሉት ማእረግ በተሟላ ፖሊሳዊ ዲስፕሊን ህዝብንና ሀገርን ለማገልገል የተሰጠ መሆኑን በመገንዘብ ፤ በሓላፊነት ስሜት ሕዝባዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ መክረዋል:: ተቋሙ ራሱን በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀት ለሚያደረገው ጥረት አስተዳደሩ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነም አረጋግጠዋል:

የኦሮሚያን ከችግር ለማውጣት መንግሥታቸው እንደሚሠራ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ

ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ::

ርዕሰ መስተዳደሩ አዲሱን አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በ2012 ዓ.ም ለተሻለ ተጠቃሚነት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል :: በያዝነው ዓመት የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርም ለ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ከመናገራቸው ባሻገር በቀጣዩ በጀት አመትም መንግስት ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ማድረግ የክልላቸው መስተዳደር ዋነኛ ዓላማ እንደሆነ አስታውቀዋል::

መጪው ዓመት ስኬታማ ስራዎች የሚሰሩበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚሰራበት፣ ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የምናስቀጥልበት እና ስራ አጥ ዜጎችንየተሻለ ስራ የሚያገኙበት ነዉ ብለዋል::

በፖለቲካው ዘርፍም በ2011 ዓ.ም የታዩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ስኬታማ ስራዎች እንደሚከናወኑ በመግለጫቸው ያወሱት ሽመልስ አብዲሳ፤ የህብረተሰቡ ኑሮ እንዲሻሻልም በኢኮኖሚው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥልና በየደረጃው ያለ የመንግስት አመራር የተያዙ እቅዶችን ለማስፈጸም በተጠያቂነት እንዲሰራም አሳስበዋል።

ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት በዜግነት አገልግሎት የችግኝ ተከላን ሳይጨምር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ስራ መሰራቱንም አስረድተዋል። በዚህም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡ ላደረገው ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአራት ሄክታር ላይ ለሚገነባው የሠላም ማዕከል ሞፈሪያት ካሚል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ

ለአመታት ያዳበርናቸውን ኢትዮጵያዊ ባህሎች ይበልጥ በማጠናከር ለሰላም መስፈን የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ:: የበዓሉ አካል የሆነው የእግር ዛሬ ሰላምን እተክላለሁ ለሀገሬ በሚል መሪ ሃሳብ ከወሎ ሰፈር አደባባይ እስከ ደንበል ድረስ  ተካሂዷል::

ለሃገሪቱ ሰላም መስፈን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የታመነበት የሰላም ማዕከል ግንባታ መሰረት ድንጋይም ተቀምጧል። የመሰረት ድንጋዩንተናግረዋል። ያስቀመጡት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ማዕከሉ የኢትዮጵያውያንን ባህልና ማንነት ይበልጥ በሚያንጸባርቅ መልኩ የሚገነባ መሆኑን ያመላከቱት ሚኒስትሯ ሁሉም ዜጋ ለአመታት ያዳበርናቸውን ኢትዮጵያዊ ባህሎች ይበልጥ በማጠናከር ለሰላም መስፈን የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስታውቀዋል::

ግንባታው አራት ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የሰላም ማዕከል ለሰላም የሚደረጉ የኪነ ጥበብ ስራዎችና መሰል ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል ሆኖ እንደሚሰራም መስክረዋል::

በዓሉን አስመልክቶም በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርና የፓናል ውይይት ተካሂዷል። የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በበኩላቸው፥ የሰላም ቀን የህዝቡን ሰላምና አብሮነት ከፍ ለማድረግ እንደሚከበር ጠቁመው ፤ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በማስወገድ አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ መነቃቃት እንዲሁም ቂም፣ ጥላቻንና ዘረኝነትን ጥለን ለመሻገር በማሰብ የሰላም ቀን እንደሚዘከር አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያዊው አሜሪካዊ በአሜሪካ ምርጫ እየተወዳደረ ነው 

ዜግነታቸውን ካገኙ 1 ወር የሆናቸው ዶ/ር ደራራ ጢሞቲዎስ በአሜሪካ ምርጫ እየተወዳዳሩ ነው ላለፉት 13 ዓመታት በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑት   ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ደራራ ጢሞቲዎስ በጆርጂያ ግዛት አትላንታ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው የክላርክስተን ከተማ የምክር ቤት አባል ለመሆን እየተወዳደሩ መሆናቸው ታወቀ: :

በአሜሪካን ለአስራ ሦስት ዓመታት የኖሩት ዶ/ር ደራራ የአሜሪካን ዜግነት ከተሠጣቸው ሠላሳ ቀናትን ብቻ ቢያስቆጥሩም ለምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር ተጨማሪ ጊዜያትን ለመጠበቅ አልፈለጉም:: ” ቀደም ባሉት ጊዜያትም ለምክር ቤት ለመወዳደር ፍለጎት እንደነበራቸው የሚገልጹት ኢትዮጵያዊ፤ የአገሪቱን ዜግነት ሳያገኙ በመቆየታቸውና ያለ ዜግነት መወዳደር ባለመቻሉ ምክንያት እስካሁን ለመቆየት መገደዳቸውን ጠቁመዋል ::

ክላርክስተን 13 ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ትንሽ ከተማ ብትሆንም አብዛኞቹ ነዋሪዎች ስደተኞች ስለሆኑከተማውም የሚታወቀውም መጥፍ ገጽታ ሆኖ ቆይቷል:: “ይህ ከተማ በጣም ትንሽ ነው፤ ነገር ግን ከ40 አገራት በላይ የመጡ ዜጎች ይኖሩበታል፤ ለምሳሌ ከእኔ መኖሪያ ቤት በቀኝ በኩል ከኔፓል የመጡ ሰዎች ይኖራሉ፤ በግራ በኩል የሚኖሩት ደግሞ ከበርማ የመጡ ናቸው፤ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንዲሁም የሌላ አገር ዜጎችም በአካባቢያችን ይኖራሉ” በማለት ከተማው የተለያዩ አገራት ስደተኞችን ያቀፈ እንደሆነ መራራ ጢሞቲዎስ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ገልጸዋል::

ያለፉበት የልጅነትና የዕውቀት ዘመናቸውን ያለፋበት የገዳ ሥርዓት ለውድድሩ ፍላጎት እንዳሳደረባቸው ያልሸሸጉት ግለሰብ፤ ከአንድ ወር በፊት የአሜሪካ ዜግነት በማግኘታቸው ለውድድር የመቅረብ ፍላጎታቸውን እንዳናረው ጠቁመውበዚህም የአሜሪካ የዲሞክራሲን ሥርዓት “እውነት ለመናገር፤ አንድ ሰው ከሌላ ቦታ መጥቶ የሚኖርበትን ከተማ ለማስተዳደር መወዳዳር ማለት ትልቅ ነገር ነው” ሲሉ ምስጋናቸውንም አቅርበዋል::

“ይህ ሰው ጎሳው ምንድን ነው? ከየት መጣ? ሳይሆን፤ ይህ ሰው ሃሳቡ ምንድን ነው? ምን መሥራት ይችላል? የሚለውን ነው የሚያዩት፤ በመሆኑም አገራችን ከዚህ ብዙ ነገር መማር ትችላለች” በማለት የፖለቲካ ተሳትፏቸው ለኢትዮጵያ ዜጎችም ሆነ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውድድሮች ውስጥ ላሉ አካላት መልዕክት ሊያስተላልፍ እንደሚችል በመግለጽ እግረ መንገዳቸውን የኢትዮጵያን የማይሻሻል ፖለቲካ በነገር ሸንቆጥ ያደረጉት ዶ/ር ደራራ፤ ከአገር ውጭ በእንደዚህ ዓይነት ውድድር ላይ ሲሳተፉ የገጠማቸውን ተግዳሮት በተመለከተ ሲናገሩ “ሰው ዓላማ ላደረገው ነገር መጣር፣ መፍጨርጭር አለበት። አንዳንድ ሰዎች ቋንቋውን አንችልም የሚሉት ነገር አለ፤ እውነት ነው፤ ነገር ግን ሃሳብ ካላቸው ሃሳባቸውን ዳር ለማድረስ ወደ ኋላ ማለት የለባቸውም፤ ማንኛውም ሰው የተወለደበት ዓለማ አለው ፤ከአላማው ወደኋላ የሚመልሰውን ፍርሃት ጥሶ ማለፍ ይናኖርበታል ” ሲሉ ተደምጠዋል።

በሚኖሩበት ከተማ እምብዛም ስለማይታወቁ የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ ቤት ለቤት ለመዞር የተገደዱት የም/ቤት ተወዳዳሪ ፤ “ሰው አያውቀኝም ብዬ፤ ወደ ኋላ አልመለስም” በማለት በጎ ሃሳብ በመያዛቸው እመረጣለሁ የሚል ተስፋን ሰንቀዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለስደተኞች ጥሩ አይደሉም የሚሉት ዶ/ር ደራራ፤ የሚቀጥለውን ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ላይ ትኩረት አድርገው ለመሥራት ዕቅድ ይዘዋል። ምክንያታቸው ደግሞ በአሜሪካ ስደተኞችን በተመለከተ እየወጡ ያሉ ሕጎች እየጎዷቸው ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው። ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ዜጎች እንግሊዘኛ ስለማይችሉ መንግሥት የሚሰጠውን አገልግሎት እያገኙ አይደሉም የሚሉት ዶ/ር ደራራ፤ እሳቸው ከተመረጡ ይህንን ችግር ሊያቃልሉ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል::በከተማው ፖሊስ ውስጥና ከተማ አስተዳደር ውስጥ የኢትዮጵያዊያን ሥራ ላይ አይታዩም፤ በመሆኑም በእነዚህ መስኮች ላይ ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉም እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

 

LEAVE A REPLY