የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ.ም

አዲስ አበባ አትክልት ተራ አካባቢ የ20 ዓመት በፖሊስ ጥይት ተገደለ

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ አንድ የ20 ዓመት ወጣት ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መሞቱ ተሰማ::

በፖሊስ የተገደለው የ20 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት ጅብሪል አህመድ፤ በአትክልት ተራ አካባቢ የተለያዩ አትክሎትችን በመቸርቸር በዝቅተኛ ሥራ ህይወቱን ይመራ እንደነበርበአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች ተገልጿል:: እናቱን በቅርቡ በሞት በማጣቱ ምክንያት ታናናሾቹን አንድ ወንድምና እህቱን ከዚሁ ስራ በሚያገኘው ገቢም ያስተዳደርም ነበር።

ትናንትናው ጧት ላይ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት በአካባቢው የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች እንደመጡ ፤ ምንም ሁኔታውን ሳያጣሩ በወጣት ጅብሪል አህመድ ላይ ሦስት ጥይት ተኩሰው እንደገደሉት የአካባቢው ነዋሪዎች መስክረዋል::

በጥይት የተመታው ወጣት ጅብሪል ወዲያውኑ ወደ አቤት ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ ግንአልተቻለም።የሟች አስከሬን ዛሬ ለአካባቢው ነዋሪዎች በመሰጠቱ ስርዓተ ቀብሩ በኮልፌ ሙስሊም መቃብር አካባቢ ተፈጽሟል።

ፖሊስ ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ ጥይት መተኮሱም በተለይም በስፍራው የነበሩ ሰዎችን አስቆጥቷል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉትም ፖሊስ ጉዳዩን ሳያጣራ ነው ልጁ ላይ የተኮሰበት በመሆኑ፣መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

ልማት ባንክ ለባለሀብቶች ያበደረውን 5 ቢሊዮን ብርእንደማያገኘው ተሰማ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአገሪቱ የተለያዩ ኢንቨስተሮች(ባለሀብቶች) ከሰጣቸው ብድሮች ውስጥ አምስት ቢሊየን ብርመመለሱ አጠራጣሪ መሆኑ ታወቀ፡፡

በአገሪቷ የሚገኙ ትላልቅ የግል ባንኮች በዓመትከሚያስመዘግቡት ትርፍ ሦስት እጥፍ ጋር ይስተካከላልየተባለውን ይህን ገንዘብ  ያጣው ባንኩ አጣብቂኝ ውስጥገብቷል፡፡ ከ16 ቢሊዮን ብር ብድር በላይ ተበላሽቶበታልየተባለው ልማት ባንክ 11 ቢሊዮን ብር ብድር መመለሱከአጠራጣሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ቀሪው አምስት ቢሊዮን ብርግን ሙሉ በሙሉ እንደማይመለስ ነው የተሰማው፡፡

የልማት ባንክ የተበላሹ ብድሮች መጠን 33 ነጥብ 9 በመቶበ2011 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ እንደደረሰ ያመላከተው ዜናከዲስትሪክቶች መካከል የጋምቤላ ክልል ቀዳሚውን ሥፍራይዟል፡፡ ከጋምቤላ ክልል በልማት ባንክ ከተሰጡ ብድሮች 80 በመቶ የሚሆኑት አልተመለሱም፡፡ ይህ መጠን በቁጥር ሲሰላወደ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡

ከነቀምት ዲስትሪክት 866 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ያልተመለሰሲሆን የቅርንጫፉ የተበላሸ ብድር መጠን ወደ 83 ነጥብ 8 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ ከባህርዳር ቅርንጫፍ በተሰጠ ብድር 739 ሚሊዮን ብር እንደተበላሸም ታውቋል፡፡ ለባንኩ የተበላሹብድሮች መጨመር እንደ ዋነኛ ምክንያት የቀረቡት አደጋ ላይለወደቁ ፕሮጀክቶች  የተሰጠው ትኩረት መቀነስና አንዳንድባለሀብቶችም ብድራቸውን ለመመለስ ፍቃደኛ አለመሆናቸውእንደሆነ ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኘው ልማት ባንክ 768 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ኪሳራ በያዝነው ዓመት ያስመዘገበ ሲሆንይህ ቁጥር ባንኩ ለማግኘት ካቀደው 878 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብርትርፍ በእጅጉ ያነሰ እንደሆነ ያሣያል፡፡

የቤተ መንግሥቱ መኪና ማቆሚያ በ1.5 ቢሊየን ብርይገነባል ተባለ

በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት ወደ ሙዚያምበመቀየር ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ቤተ መንግስት የመኪናማቆሚያው በ1.5 ቢሊየን ብር እንደሚገነባ ተነገረ፡፡ የቻይናውጂያንግኮንስትራክሽን በተጠቀሰው የገንዘብ መጠንሥራውን ለማወንም ውል ፈጽሟል፡፡

በቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ ግንባታው የተጀመረውንናሙዚየም ለመጎብኘት ለሚመጡ ጎብኚዎች እንዲሆን ታስቦየሚገነባው የመኪና ማቆሚያ ወጪን የአዲስ አበባኮንስትራክሽን ቢሮ ይሸፍናል፡፡

የዲዛይን ጥናት ሥራውን ጨምሮ በአንድ ዓመት ከ6 ወር ጊዜውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆንጂያንግሱ ኮንስትራክሽን ባለው ልምድና ባቀረበው የግንባታዋጋ ሊያሸንፍ እንደቻለ እንዲሁም ግንባታው ከ1600 በላይለሚሆኑ ሠራተኞች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርተገልጹዋል፡፡

የቤተ መንግሥቱ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ሥራ በአዲስ አበባኮንስትራክሽን ቢሮ ተቆጣጣሪነት የሚከናወን ሲሆን የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማማከርነት እየሰራይገኛል፡፡

ነሐሴ ወር በዓመቱ የኑሮ ውድነት የገነነበት እንደሆነ ታወቀ

ባለፉት አስር ወራት ከቀን ቀን እየባሰ የመጣው የኑሮ ውድነትኢትዮጵያ ውስጥ ከአስከፊ ደረጃ ላይ ቢደርስም ከሁሉም በላቀመልኩ ነሐሴ ወር የኑሮ ውድነቱ የከፋበት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በአገሪቱ የተንሠራፋውን የኑሮ ውድነት በተመለከተ ሠፊጥናት ሲያካሂድ የቆየው የማዕከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ የነሀሴወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 17.9 በመቶ መድረሱን ይፋአድርጓል፡፡

የተጠቀሰው ወር የዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅትጋር ሲነፃፀርም በ23 በመቶ አሻቅቧል ያለው ተቋሙ ጤፍገብስማሽላና በቆሎ በነሐሴ ያልተቋረጠ የዋጋ ጭማሪየታየባቸው እህሎች እንደሆኑበአንፃሩ ቀይ ሽንኩትና ነጭሽንኩርት የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው መሆኑንምአረጋግጧል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች 12 በመቶ የዋጋጭማሪ እንዳሳዩም ታውቋል፡፡

በ2011 ዓ.ም 4ሺ 597 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞተዋል

እያገባደድነው ያለነው ዓመት አስመልክቶ የትራንስፖትሚኒስቴር እንደገለፀው ከሆነ በ2011 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ4ሺህ 597 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የትራፊክ አደጋው አገሪቱ ካላት አነስተኛ የተሽከርካሪ ቁጥርአኳያ ሲታይ እጅግ የከፋ መሆኑን የገለፁት የትራንስፖርትሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔርበጉዳዩ ላይ አፋጣኝ ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል፡፡

በትራፊክ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ2010 ዓ.ም ሲነፃፀር በ4 በመቶ ብልጫ ያሣየ ሲሆን የመንገድ አጠቃቀም ህግና ሥርዓትባለመከበሩ እንዲሁም ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ ችግሩ ሊባባስእንደቻለ ተነግሯል፡፡

LEAVE A REPLY