የኦሮሞ ብሄረተኞች አጥበቀው ኦህዴድ ላይ ትልቅ ጫና እያሳደሩ ነው። በተለይም እነ ጃዋር ኃይላቸውን የሚያሳዩት ኦህዴድ ላይ ተንጠላጥለው ስለሆነ፣ በየቦታው የሚያሰማሯቸው ጽንፈኛ ቄሮዎች በኦህዴድ የተደራጁና የሚደገፉ፣ ከኦህዴድ ሃላፊዎች ጋር በቅንጀት የሚሰሩ እንደመሆናቸው፣ ኦህዴድ ከሰመ ማለት የነርሱን ነገር አበቃለት ማለት እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ።
ስለዚህ ዉህደቱ እንዳይፈጸም የሞትና የሕይወት ሽረት ትንቅንቅ እያደረጉ ነው። ዉህደቱ ተከናወነ ማለት ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ …ምናምን ብሎ ቢያንስ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ይቀራል ማለት ነው። በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ በስፋት የመመረጥ እድል ያገኛሉ ማለት ነው። “ኦሮሞነት” ፣ ወይም “አማራነት” …ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ይጎላል ማለት ነው። ይሄ ለነርሱ የመጨረሻ ሽንፈት ነው። መከፋፈልን፣ ጥላቻና ጠብን ካልሰበኩ ቢዝነሳቸው ዜሮ ይገባል።
በቅርቡ ባለ ሜንጫው ጃዋር ወደ ስምንት ገጽ የሚሆን ጹሁን በላቲን ጽፎ ለቋል። ጽሁፍን ያነበቡ እንደሚናገሩት እጅግ በጣም በጠነከረ መልኩ ነው ዉህደቱን እየተቃወመ ያለው። “ኢህአዴግ መዋሃድ የለበትም!!!!!!!!!!…” እያለ ነው።
ሆኖም፣ በነጃዋርና በኦሮሞ ጽንፈኞች ከፍተኛ ጫና ቢደረግም፣ የኦህዴድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 6 ለ 3 ዉህደቱን መጽደቁ ይታወሳል።
ጉዳዩን 55 አባላት ወዳሉት ወደ ማእከላዊ ኮሚቴ ይመለከተዋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፣ ማ’እከላዊ ኮሚቴው ላለፉት 2 ቀናት ስብሰባ አድርጎ ምን ውሳኔ እንዳሳለፈ እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም። ምንም አይነት መግለጫ ይፋ አልሆነም።
ዉህደቱን ኦህዴዶች አጸደቁ አላጸደቁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ይመጣል።
ዉህደቱን ካጸደቁ ኦህዴድ ይከስማል። ካላጸደቁ ደግሞ ኦህዴድ ለብቻው ተነጥሎ ከሕወሃት ጋር ይሆናል። ከፌዴራል መንግስቱም ይባረራል። ዶ/ር አብይን የተወሰኖ ኦህዴዶችን ይዞ ኦህዴድን ይለቃል። የኦህዴድ ሊቀመንበር መሆኑ ይቀራል ማለት ነው።
በኢሕአደግ ደንብ መሰረት ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለፓርላማ እጩ ሆኖ ለመቅረብ የአንዱ የኢሕአዴግ አባል ድርጅት ሊቀመነበር መሆን ያስፈልጋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕግ መንግስት፣ ጠቅላይ ሚኒስተር የፖለቲካ ድርጅት መሪ ወይንም አባል መሆን አለበት የሚል አንቀጽ የለውም። ከፓርላማ አባላት መካከል አብዛኛው የፓርላማ አባል የመረጠው ተወካይ ጠቅላይ ሚኒስተር መሆን ይችላል። በመሆኑም ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ሊቀመንበር ባይሆንም፣ የፓርላማ ተወካይ እንደመሆኑ የአብዛኞቹን የፓርላማ አባላትን ድምጽ ካገኘ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መቀጠል ይችላል። ብዙም የተወሳሰበ ነገር አይደለም።
ኦህዴድ 178 የፓርላማ መቀመጫ አለው። ከዚህ ውስጥ እንበል በጣም አሳንሰን ዶ/ር አብይን የሚደገፉ 18 አባላት ቢኖሩና የተቀሩት 160 የኦህዴድ ተመራጮች ለዶ/ር አብይ ድምጽ ቢነፍጉ፣ የትግራይ የሕወሃት 38 ተወካዮችም እንደዚሁ፣ ከ547 የፓርላማ መቀመጫ 196 ተወካዮች ይደርሳሉ። 19 የሲዳማ ተወካዮችም እንበል ያው ለኦነጎች ቅርብ ስለሆኑ፣ ዶ/ር አብይን አንፈልግም ቢሉ፣ የተቃዋሚው ቁጥር 215 ይደርሳል። የተቀሩት 332 የፓርላማ አባላት ከዶ/ር አብይ ጎን ከቆሙ ዶክተሩ አሁን ያለበትን ቦታ ይዞ ይቀጥላል። ይሄ እንግዲህ በጣም ወግ አጥባዊ ሆኜ ነው። እንጂ በኦህዴድ ውስጥ የዶ.ር አብይ ደጋፊ ከመቲ ሊበልጥ ይችላል። ህወሃት ውስጡ ብዙ ዶ/ር አብይ ሊደገፉ የሚችሉ ይኖራሉ።
ዶ/ር አብይ ከኦህዴድ አልለይም ብሎ፣ ዉህደት ሳይደረግ እንቀጥል የሚል አቋም ከያዘ ፣ ከተለሳለሰ፣ አዴፓ የራሱን መንገድ ይዞ ለመቀጠል ይገደዳል። እስከ አሁን ድረስ አዴፓዎች የኦህዴዶች ብልግናና ጥጋብ እያዩና እየሰሙ፣ ውስጣቸው እየደበነ ዝም ያሉት ዉህደቱን በሚል ነው። ዉህደቱ ከቀረትልቅ የኃይል አሰላለፍ ሽግሽግ ይኖራል።