እንደ አዲስ ሙሽራ- እንደ በኩር እናት፣
ደሞ አብረከረካት – ሀገሬን ደም መታት፣
ከአንጀት የማይወጣ – ከልብ የማይፋቅ -መራር ሀዘን ገባት።
ዘመናዊ ሃኪም – የሚገላግላት፣
የባህል አዋቂ አዋላጅ ቸግሯት፣
በሆዷ ሸክፋ፣
የያዘችው ተስፋ፣
በደም ተበላሽ፣
መልኳ ጠቀረሸ ፤
ከ”አብዮት” በኋላ – የሚያስጨነግፋት; – በሽታዋ ጎሸ፤
የእንሽርቱ ውሃ – የእንግዴ ልጅ መምጫ፣
የቋጠረችው ፅነስ- የተስፋዋ ርግጫ፣
አዛላት በብርቱ – ፅልመት አለበሳት፣
ወይ አለመታደል – ሀገሬን ደም ፈታት፤
ይኼን “ውርዴ” ህማም – የሚፈውስ ነገር – እስቲ ሀሳብ አዋጡ፣
ነቅሎ የሚፈውሳት – ወይም ዋግምት አምጡ!