ዶ/ር አብይን አንግሶ ጃዋርን መወንጅል ሕጋዊነት የለዉም ||

ዶ/ር አብይን አንግሶ ጃዋርን መወንጅል ሕጋዊነት የለዉም ||

የአገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ ስለሚያስጨንቃችሁና መልካሙን ለምትመኙ በዉስጥና በዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ኢትዮጵያዉያን፤ በመጀመሪያ ከዘመናት በፊት ስለ አገራችን ኢትዮጵያ በነቢያት የተነገረዉ የሰላምና የብልጽግና ዓመት ተካፋዮች እንድንሆን ያለኝን መልካም ምኞት በቅድሚያ አስታዉቃለሁ፡፡ አሁን በምድራችን እየተካሄደ ያለዉ እንዲያዉ በድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በእምነት መጻሕፍት የተጻፈ በመሆኑ ነው፡፡ ከተጻፈዉ ደግሞ አንዱም ተግባራዊ ሳይሆን መጨረሻዉ እንደማይመጣ ተነግሮናልና፡፡

አይሁድን ለአራት መቶ ዓመታት በባርነት የገዛዉ ፈርዖን፣ ዘመኑ ሲጠናቀቅ አላስወጣም እንዲል ያደረገዉ አይሁድን ለባርነት አሳልፎ የሰጠዉ አምላክ ማንነቱን ለፈርዖን ያሳይ ዘንድ ነበር፡፡ ዛሬም ኢትዮጵያን ከተጫናት መንፈሳዊ ባርነት እንዳትላቀቅ ከሚታገሉት መካከል ቲም ለማ በመባል አገር አጥፊ የተካተተዉ ጃዋር መሀመድ መሆኑ እየታወቀ፣ ዶር አቢይ አህመድን አንግሶ ጃዋርን መወንጀል አግባብነት የለዉም፡፡ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን እንደሚባለዉ መሆኑ ነው፡፡

ዉድ አንባቢ የመልክቱ ርዕስ ባትቀበለዉም፣ እስከ መጨረሻዉ ማንበብ ጠቀሜታዉ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለአንተ ነውና፡፡ በሰዎች መካከል ለሚከናወኑ ተግባራት በአጋጣሚ የሚከናወኑ አይደሉም፡፡ ከኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን መዉረድ፣ ዶር አቢይም የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ሆኖ መሾሙ ያለምክንያት አይደለም፣ ለሁሉም ነገር ምክንያት አለዉና፡፡ ኢየሱስን ለመስቀል ሞት አሳልፎ እንደተሰጠዉ፣ የዶ/ር አብይን አህመድ አሊ ወደ ሥልጣን መምጣትና የአክቲቪስት ጃዋር እና መሰሎቹ ከዚሁ ጋር የተቆራኘ ነዉ፡፡ ጃዋር መሀመድ አሊ አና ዶር አቢይ አህመድ አሊን ያገናኛቸው ጥቂቱን ብንመለከት ሁለቱም ከኦሮሞ ጎሳ፣ ከእስላም አባቶች እና ከኦርቶዶክስ እናቶች የተወለዱና ሚስቶቻቸዉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መሆናቸዉ የአጋጣሚ አይደለም፤ ዓለም በአጋጣሚ የምትንቀሳቀስ አይደለችምና፡፡፡፡ የግላቸዉን እምነት በተመለከተ አክቲቪስት ጃዋር የኢስልምና ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ ተናገሮአል፤ ዶ/ር አቢይ አህመድ ግን ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ማንነቱ አይታወቅም ነበር፣ ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ የፕሮቴስታንት አማኝ መሆኑ በተናገረ ማግሥት እሰላም መሆኑንም በአንደበቱ ተሰምቶአል፡፡

እምነትን በተመለከተ የፕሮቴስታንት አምላክ ኢየሱስ፣ ሙስሊሙ አላህ እንደሆነ የሚታወቁ ሲሆን ዶር አቢይ አምላክ ግን ፈጠሪ መሆኑ የመጀመሪያዉ በፓርላማ ንግግሩ ነው፡፡

ዶ/ር አቢይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ለእስትራተጂስቱ ጃዋር መሀመድን በቲም ለማ ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ከናሆም ቲቪ (Naom tv) ጋር ባደረገዉ ጥያቄና መልስ “አሁን ወደ ኢትዮጵያ እንድትመጣ ከቲም ለማ ጋር እንዲሁም ከዶ/ር አብይ ጋር ግንኙነት ነበረህ ወይ?” ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉ መልስ በተመለከተ የተናገረዉ፡-

“ብዙ ናቸዉ፣ እነርሱ ብቻ አይደሉም፡፡ እነርሱ (ዶር አቢይና ለማ መገርሳ) ወደ ፊት እንዲመጡ ከእነርሱ ጀርባ ለአስር ዓመት በፖለቲካዉ፣ በወታደራዊ ክፍል፣ በደህንነት ውስጥም ነበሩ፤ አሁን የተገኘዉ ድል አምስት ሺህ የኦርሞ ወጣቶች በእሳት መስዋዕት ሆነው ነው፡፡” ማለቱን መሠረት ያደረገ ብቻ ሳይሆን፣ አክቲስት ጃዋር መሀመድ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት በሰሜን አሜሪካ እያለ በተለያዩ መድረኮች ያስተጋባ የነበረዉ “ኦሮሞና እስልምና የማይለያዩ”፣ “ኦሮሞ ሲነካ፣ እስላም ይነካል”፣ “የኦሮሞ ድል፣ የእስላም ድል ነው”፣ “ እኔ በተወለድኩበት ቦታ 99 % ኦሮሞ፣ 99 % ኢስላም በመሆኑ ማን አባቱ ነው የሚናገረኝ አንገቱን ነው የምቀላዉ“ ማለቱ ያለ ምክንያት አልነበረም፣ በጥቅምት 13 እና 14 2012 ዓ. ም በጃዋር ቀጥታ ትዕዛዝ 67 ኢትዮጵያዉያን በቄሮች መታረዳቸዉ፣ በድንጋይ ተወግረዉ መሞታቸዉ፣ በመቶዎች መቁሰላቸዉ፣ ቤተ አምልኮ መቃጠላቸዉ በተግባር ታይቶአል፡፡ ይህ ድርጊት እንግዳ አይደለም ካለፉት እልቂቶች ቀጣይ መሆኑና ወደ ፊትስ ስንቶች ይገደላሉ ብሎ መጠየቅና መፍትሄዉ መፈለግ ዛሬ ነው፡፡

ጃዋር መሐመድ እስላም ነኝ ይበል እንጂ ቅዱስ ቁርኣንን ጠንቅቆ የሚያዉቅ አይደለም፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ዶር አቢይ አህመድ እና ደጋፊዎችም ቢሆኑ እንዲያዉ በቃላቸዉ ይደግሙታለ እንጂ እውነቱ ገብቶአቸዉ አይደለም፡፡ ለዚህም አባባሌ ሙስሊሙ እምነቱ በቁርኣን አስተመምሮ ላይ በመሆኑ፣ ቁርኣን አታድርጉ ያለዉን ማድረግ ገነት እንደማያስገባ ያዉቁታል፡፡ ይህም መልዕክት፣ የዶር አቢይ ደጋፊ ከጃዋር ደጋፊዎች በአንድ መንፈስ የተያያዙ በመሆናቸዉ፣ ተጸጽተዉ ከጥፋት ይታቀቡ ዘንድ እና ከእሳትም ባህር እንዳይጣል ለመምከርና ለማስጠንቀቅ ነዉ

ቁርኣን መጥቀስ ያስፈለገዉ፡፡ ሱራህ አል-ማኢዳን 5፡32 …ነፍስን የገደለ ሰዉ (ያስገደልም)፣ ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነዉ፤ ወንጌልን መስክሮ ሕያዉ ያደረጋትም ሰዉ ሰዎችን ሁሉ ሕያዉ እንዳደረገ ነዉ …::

ኢብሊስ፣ በአላህ አምሳያ ጠየተፈጠረዉን ሰዉ አስገድሎ ገነት ትገባላችሁ ቢልም፣ በሲዖል ሽልማት እንደማይሰጣቸዉ ልቦናቸዉ ያዉቀዋል ግን አዳምንና ሔዋንን እንዳሳታቸዉ ዛሬም በጃዋር አንደበት እየሸነገላቸዉ፣ የዶር አቢይንም አንደበት ከመጠቀም አልተቆጠበም፡፡ በሰዉ ምክንያ ሰማያዊ ክብሩን ስላጣ፣ ዛሬ ክርስቲያኖችን ለይቶ ማጥቃጡ የበቀል እርምጃ ነዉ፡፡ ለጊዜዉ ሙስሊሙ የተጠቃ ባይመስልም፣ ዉሎ አድሮ አይቀርለትም፤ ሰዉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ተቀርጾና እስትንፋስ ተቸሮት የሚንቀሳቀሱ ፍጡር ነዉና፡፡

ደግሞም ሱራህ አል-በቀራህ 2፡256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም … እያለ፣ አንድን ክርስቲያን ካልሰለም እንገድልሃለን ብሎ ማስፈራራት፣ አሻፈረኝ ያለዉን ክርስቲያን ለሰይጣን መስዋዕት ማቅረብ ሃራም መሆኑን እያወቅህ ገነት እገባለሁ ማለትህ ምን ያህል እንዳደነቆረህ ያለማወቅህ አያስደንቅም፤ አስቀድሞ ነቢዩ ሙሐመድ ሰይጣን አባትና እናታችሁን አታልሎ ከገነት እንዳስወጣቸዉ እናንተን አይሞክር ንቁበት ማለታቸዉ በአል-አዕራፍ 7፡ 27 የተጻፈልህን አንብበህ ንስሃ ግባ ዳግመኛ ከቲም ለማ ጋር ላለመተባበር፡፡ አሻፈረኝ ካልክ የሚጠብቅህ ኢብሊስ ልብህን አጠንክሮ በእሳት ባህር መጣል ነዉ፡፡ የሰዉ ልብ ቁርኣንን ወይም ወንጌልን በማንበብ የሚለወጥ ሳይሆን የልብ ቅንነት ነዉ፡፡

በሰሞኑ በኬንያ አንድ ኢስላም መኪና ነጂ፣ ስምንት ክርስቲያኖችን ከአልሸባብ እንዳስመለጠ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡ ለምስክርም እንዲሆን ድረ መረቡን ማንበብ ነዉ፡፡ Faithwire.com
ታዲያ ቅዱስ ቁርኣን እውነቱ እንደዚያ ተጸፎላችሁ እያለ ሰዉን፣ ክርስቲያኑን ማረድ እምነቱን በአላህ ላይ ባደረገ ሰዉ አይጠበቅም፡፡ የሟች በድን ቢቀበርም ባይቀበርም፣ ነፍሱ ግን በአላህ ዘንድ ታለቅ ክብር አላት፡፡ ገዳዩ ደግሞ በኢብሊስ ዘንድ መከራን ይጨምራል፡፡ ገዳይም ሆነ አስገዳይ፣ ሹመኛም ቢሆን ዛሬ ላይ የማይሞት ቢመስለዉም መሞቱ አይቀርም፣ ፕሮቴስታንትም መሆን ከፍርድ አያስመልጥም፣ ፍርዱም አይዘገይም፡፡ ወየሁ ለዚያች ክርስቲያኑን ለገደለችና ላስገደለች ነፍስ ምነዉ አርፌ በተቀመጥሁ ይሻል ነበር ማስባሉ የሚቀር አይደለም፡፡ ክቡራን ሼኾችና ኢማሞች ሃላፊነታችሁን ዘንግታችኋል ወይም ተታላችኋል? አላህ እኮ አባቶቻችሁንና እናቶቻችሁን ወደ ቅድስቲቱ ምድር ኢትዮጵያ ያስገባችሁ አረሕማን (አማኑኤል) ሆኖ ሳለ በእናንተ ልጆች ምድሪቱን በሰዉ ደም ማርከሳቸዉ በአላህ ዘንድ የማትጠየቁ መሰላችሁችሁ? ዶር አቢይ አህመድም ቢሆን ነገ ከስልጣኑ ይነሳል፣ ጃዋርም ቢሆን ይባረራል፣ አላህ እናንተን ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ለመሆኑ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ቁርኣን ግልጽ ካልሆነላችሁ አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ጠይቁ ማለታቸዉ ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ግደሏቸዉ፣ ክርስቲያኖችን እረዷቸዉ ማለታቸዉ ነዉን? እውነትን ብታዉቁ ኖሮ እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ይመሠረታል ያላችሁን ሹመኞችን ማመን ባልነበረባችሁም? በመካ የሚገኘዉ ካባ በኢትዮጵያዉያን እንደሚፈርስ በመጽሐፋችሁ አልተጻፈምን? ታዲየ ቀድመን ኢትዮጵያን እናፈራርስ ከሆነ ሴራዉ፣ አላህ ለአባቶቻችሁ ያደረገዉን ዉለታ መዘንጋት ብቻ ሳይሆን፣ በእርሱ ላይ ማመጽም ነዉ፡፡

ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) መንፈሳዊ መሪያችሁ፣ “ወንድሞቼ ሆይ! አላህ ያቺን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችዉን መሬት ግቡ፣ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ ከሳሪዎች ሆናችሁ ትመለሳላችሁ” የተባለዉ በሱራህ አል- ማኢዳን 5፡21 ተጽፎ እንዲነበብ የተደረገዉ ለእናንተ መኖሪያችሁ በቅድስቲቱ ምድር እንዲሆን አላህ ካስመጣቸዉ ለተገኛችሁ አይደለምን? ደግሞስ እነዚያ ከአላህ አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን ከከሳሪዎች ትሆናለህና የተባለዉስ አይመለከታችሁምን? በዶር አቢይ ዘመነ መንግሥት ክርስቲያኑን ያረዱና ቤተ ክርስቲያን ያቃጠሉ ቄሬዎች እውነት ሲገባቸዉ ካባን ለማፍረስ የሚሄዱ አይደሉምን? ለእናንተንስ ለመበቀል ትግስት ይኖራቸዋልን? የዶር አቢይ ዘመን “ጊዜ የሰጠዉ ቅል ድንጋይ ይንዳል” እንደሚባል ሆኖ ነዉ እንጂ እንኳን ለማረድ ክፉ ቃል መናገር ባልነበረባቸዉም ነበር፡፡ ለእኛም ኦርሞና እስላም ላልሆነዉ ኢትዮጵያዉያን ጊዜ አለን፡፡ እንበቀላለን ማለት ሳይሆን በቀል የአላህ ነው፡፡

በሰሜን አሜሪካ 18ኛዉ የበድር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በኢስላማዊ ዳዋ ሴንተር July 26, 2018 ከአቶ ለማ መገርሳ፣ ከዶር ወርቅነህ ገበየዉ እና ከሌሎች ልዑካን ጋር ተገኝቶ በንግግሩ መክፈቻ “አልሰሰላም አል ራመት ወበረከቱም” በማለት የጀመረዉ “ኢስላም ሰላምን፣ ምህረትን፣ በረከትን ይሰጣል” ማለት እንደሆነም አሰምቶአል፡፡ ቀደም ብሎ ከተባበሩት ዐረብ ኤሚሬት ሼኺ መንፈሳዊ መሪ ጋር ተገናኝቶ በኢትዮጵያ ኢስላሚክ ኢንስቲቱዩት ለመክፈት

ማቀዱን አሳዉቆ በአዳራሹ ለተገኙ ሙስሊሞችም፣ “እኛ አረብኛን ቶሎ ቶሎ ተምረን፣ ትናንት ሁለቱን ኦርቶዶክስ አንድ እንዳደረግን፣ እናንተ የኢትዮጵያ ሙስሊም ኢማሞች አንድ ከሆናችሁ ዓለም ሁሉ በእጃችን ይገባል” ማለቱን

በተመለከተ አዳራሹ የተገኙ ልዑካንም ዶር አቢይ አህመድ ሙስሊም ነው ብሎታል፡፡ እናንተስ? አንቺስ?
በቲም ለማ የታቀፋችሁ ኢስላሞችና ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስን በተመለከተ በቁርኣን አሊ-ዒምራን 3፡45 “ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ ልጅ ያበስርሻል” እንደ ተባለ በወንጌልም ሉቃስ 1፡31 “እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ እርሱ ታላቅ ነዉ፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሣል፣ መንግሥቱም መጨረሻ የለዉም፡፡” መባሉና እስራእል ለሁለት ሺህ ሰባት መቶ ዓመታት አገር አልባ ሆነዉ ሳለ፤ኢትዮጵያ ግን በወራሪዎች ሳትደፈር የቆየችዉ ሕዝቡ ቅዱስ ሆኖ ሳይሆን፣ ምድሪቱ የኢየሱስ በመሆኗ ነው፡፡ ሰይጣን ዓለምን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ የቀረዉ ቢኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ አሁንም አገሪቱን እስላም አገር ለማድረግ ከሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞች ራሳችሁን ካላገለላችሁ ቅጣቱ እንደማያልፋችሁ ከአሁኑ እወቁት ነዉ መልዕክቴ፡፡

አንባቢ እዚህ ላይ የእስልምና ተከታዮች በኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባቸዉም ማለት ሳይሆን እዉነትን ለማሳወቅ እና የሚያስከትለዉን ቅጣት ክርስቲያን በመሆኑ የማያመልጥ መሆኑንም እንድታዉቁት ጭምር ነዉ፡፡ ቅዠት ተፈርቶ መተኛት አይቀርምና አገራችን ኢትዮጵያ የጠላት ዒለማ የሆነችዉ፣ አባቶቻችሁንና እናቶቻችሁን ከጣዖት አምላኪ ዐረቦች ጥቃት እንዳይደረስባቸዉ በነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ የመካ መዲና መንግሥት ስደተኞችን ለማስመለስ ብዙ ሥጦታዎች በወቅቱ ንጉሥ ለነበረዉ ነጃሲ ቀርቦለት አባቶቻችሁንና እናቶቻችሁን አሳልፌ አልሰጠም ካለ ቀን ጀምሮ ነዉ ዐረቦች የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑት፡፡ ዛሬም እናንተ ሙስሊሞችን በመተማመን እንደ ጃዋር ያሉትን አሰልፎ ኢትዮጵያዉያንን እያስገደለ ባለበት ወቅት ዶር አቢይ እንደ አገር መሪነቱ ግድያዉን ከጅምሩ ማስቆም ሲገባዉ እንዳላየና እንዳልሰማ ሆኖ አልፎታል፡፡ በዶር አቢይ የሚመራዉ የቲም ለማ ስብሰባ ላይ ጃዋርን ማሰር ለአንድነታችን አደጋ ይፈጥራል መባሉ ተሰምቶአል፤ ይህም በተግባርህ ግፋበት ከማለት የተለየ አይደለም፡፡ታዲያ አሁን ምን ታይቶና ተሰምቶ ነዉ ጃዋር አህመድ ከዶር አባይ አህመድ ጋር ጸብ እንዳቸዉ ተደርጎ መነገሩ? አሳፋሪ ከመሆኑም ባለፈ ጃዋርን ወንጅሎ ዶር አቢይን መተዉ በራሱ ሕጋዊነት የለዉም፡፡ እንዲያም ሆኖ የአገሪቱ መከላከያዉ ሠራዊት እና የፀጥታዉ ኃይል ነገም ቢሆን ከመጠየቅ አያመልጡም፡፡ ምነዉ ዶር አቢይ ከአትዮጵያ በወጣ ጊዜ በኢትዮጵያ ጥፋት ይከሰታል?
በአገሪቱ አስተዋይ ሰዉ ጠፋ እንጂ ዶር አቢይ ከእኔ የተሸለ ሃሳብ ያለዉ ከመጣ ሥልጣኔን እለቃለሁ ማለቱ ተደጋግሞ ተናግሮአል፡፡ በሃሳቡ ምን መደረግ እንዳለበት ወደ ሥልጣን ከመምጠሩ በፊት “እርካብና መንበር” በሚል መጽሐፉ ውስጥ በዝርዝር ያሰፈረዉን አገር አፍረሽ ሤራ በተግባር እያሳየን ነዉ፡፡ ከይሁዳ አንበሳ ጋር ቁርኝት ያላቸዉን መንግሥታዊ ድርጅቶች እየሸጠ፣ ሃዉልቶችና ሕንጻዎች አፈራርሶና ከምድሪቱም አጥፍቶ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት እንደሆነ፣ ተናግሮአል፤ እየታየም በመሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአስላም ማዕከልም ሆኖአል፡፡ አየር መንገዱምና ቴሌም ለሽያጭ አቅርቦአል፡፡ እንግዲህ አሻሻጮችና ገዥዎች የምናያቸዉ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በውጭ አገር ያላችሁን ጨምሮ ክርስቲያን ወይም ኢስላም በመሆን ማምለጥ የማይቻልበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ዛሬ በጃዋር ትዕዛዝ፣ በዶር አቢይ አዉቆና የኢትዮጵያዊ ደም ወደ ሰማያት እየጮኽ ነዉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ማቃጠል ማለት አላህን መዳፈር ነዉ፡፡ ይኽም በፀረ ክርስቶስ መንፈስ የተናወጠ ሰዉ ካልሆነ ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠልና የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ቀሳዉስቱን አርዶ ለአባቱ ለሰይጣን መስዋዕት ማቅረቡ ካልሆነ ለምንድነዉ? እንደ እኛ በዓለም ላይ ተጽኖ ማምጣት የሚችል አገር የለም ከተባበርን፡፡

በእስራኤል የናታናዩ መንግሥት እንዳይጸና ያደረጉት ኢትዮጵያዉያን በአንድነት በመጽናታቸዉ ነዉ፡፡ የአሜሪካና የእግሊዝ የበላይነት ዘመን አክትሞአል፣ እኛ የቀመስነዉን መራራ ጽዋ ሊጎነጩት በእጃቸዉ ላይ ነዉ፡፡ ዘመኑ ወደ እኛ አዘንብሎአል፡፡ ለዚህ ነዉ ዓለም የመጨረሻዉን ምጥ በማማጥ ላይ ያለችዉ፡፡
ጃዋር፣ ዶር አቢይን ወደ ሥልጣን ለማምጣት አምስት ሺህ የኦሮሞ ወጣቶችን በእሳት መስዋዕት እንዲሆኑ አድርጌ ነዉ ማለቱ ተደምጠአል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ግን ችላ የሉት ጉዳይ ቢሆንም፣ ዉሎ አድሮ ፖለቲከኞችን ከማሳረድ አይመለስም፣ ዶር አቢይ በሥልጣን እስካለ ድረስ፡፡ “ፖለቲካና ሃይማኖት አይገኛንም” የሚል አባባል

የተዘወተረ ቢሆንም፣ እንደ አዉነት ከሆነ፣ ሃይማኖት ያለ ፖለቲካ፣ ፖለቲካም ያለ ሃይማኖት መኖር አይቻልም፡፡ ይህም የኢየሱስ እና ሳጥናኤል የሌሉበት ምድር እንደመፈለግ ነዉ፡፡ ሁለቱም ኃያላን በመሆናቸዉ ሰዉ ወዶ ወደ አንዱ ካልተጠጋ በኃይለኛዉ መጥፋቱ አይቀርምና፡፡ ይኽም ጨለማ በብርሃን ውስጥ እንደማይኖር ጨለማን የመረጠም በኢትዮጵያም እንደማይኖር አመላካች ነዉ፡፡ በቁርኣንም እርሱ ዒሳ ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣችኋል እንደተባለም ነው፡፡

ኢትዮጵያና ሕዝቧ ደግሞ ለዚያ ለወሳኝ ጦርነት ከዘመናት በፊት የተመረጡ ናቸዉ፡፡ ነገ የተባለዉ ዛሬ እንደሚሆን ወደፊት ተብሎ የተጻፈዉ ዘንድሮ ሆኖአልና፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋትም ሆነ ለመከፋፈል ከተግባር አልፎ በሃሳብ የተባበሩ፣ የተደመሩ መጥፋታቸዉ በጣም ቅርብ ነዉ፡፡ መለሰ ዜናዊ እድለኛ ነዉ ይህን በእኛ በህዋት አመራሮች ላይ የደረሰብንን በሰዉ አዕምሮ የማይታሰብ ስቃይ ሳያይ መሞቱ ያስብላል፤ ኢሳያስም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ገንጥዬ መሪ ከመሆኔ ምነዉ ኢትዮጵያዊነቴን ይዤ በተቀመጥሁ ይሻለኝ ነበር ማለቱ የማይቀር ነዉ፡፡ የዉጭ አገር መሪዎች በኢትዮጵያ ባለሥልጣን ላይ የደረሰዉን ጥፋት በማየት ድንጋጤ ውስጥ በመግባታቸዉ ምክንያት ለትንሽ ጊዜም ቢሆን በሕዝቦች መካከል ሰላም ይሰፍናል፡፡ እንዲህ ስል ትንቢት መናገሬ ሳይሆን የተጻፈዉን መድገሜ ነዉ፡፡ “በአሕዛብ ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም፦‘ በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይፈጫቸዋል፤ ይህም ልክ እኔ ከአባቴ ዘንድ ሥልጣንን እንደ ተቀበልሁ ነው፤ እኔም የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።

መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።” ራዕይ 2፡25-29
ዶር አቢይም መጽሐፉን ያነበበ በመሆኑ፣ እኔ ነኝ በሚል እስረኞችን ፈትቶ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም ሰላም እናመጣለን ማለቱ ተደምጦአል ነበር፡፡ በአገዛዝ ዘመኑ ከተፈቱት እስረኞች የበለጡት መገደላቸዉ፣ መፈናቀላቸዉ፣ ቤተ አምልኮም መቃጠላቸዉ አምኖ፣ እርሱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ያለመሆኑን ማመን ይኖርበታል፡፡ ተጸጽቶም ከዐረቦች ጋር የገባዉን ቃልኪዳን ካላፈረሰ፣ ትርፉ በሲዖል መጣል ነው፡፡

ጃዋርን ማሰር ዐረብ አገራት ኢትዮጵያን የማፈራረስ እቅድ ያዘገየዋል እንጂ አያስቆመዉም፤ አቢይ አህመድ በሥልጣን እስካለ ድረስ፣ የግብፅ ድንፋታ ያበዛዋል እንጂ አይገታም፡፡ ከግብፅ ጋር ለመደራደር ወደ ሰሜን አሜሪካ መጓዝ ወደ ካይሮ እንደ መሄድ ነዉ፡፡ አሜሪካ እና እንግሊዝ መሠረታቸዉ ግብጻዉያን በመሆናቸዉ ነዉ፣ በታሪክ ወዳጅ ተብለዉ ኢትዮጵያን ካጠቁት አገራት መካከልም ናቸዉ፡፡ ኢትዮጵያ ወዳጅ የሚባል አገር የላትም፡፡ ወንጌል ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በጦርነት ከመጡብን አገራት ጀርባ እስራኤሎች የሉም ማለት እውነትን እንደ መካድ ነዉ፡፡ የነቢዩ ሙሐመድ ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ የመጡትም እስላም ሆነዉ ሳይሆን ሳባዉያን በመሆናቸዉና ኢየሱስም እንደጠፉ በጎች ተመለክቶአቸዉ ሆኖ ሳለ፣ የልጆቻቸዉ ምርጫ እስልምና ሆኖ ኢትየጵያን ወጉ፡፡ ዶር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያን መከፋፈል ዋጋ እንደሚያስከፍለዉ ጠንቅቆ ያዉቀዋል፡፡ ማፈራረሱንም ሆነ ኢስላማዊ አገር ለማድረግ ቀስ በቀስ የማድረግ ዝንባል በማሳየቱ፣ የጃዋር ቡድን ግን ለምን ጊዜ ታባክናለህ ባይ በመሆኑ ተደማጭነት እንዳለዉ ለማሳየት ኢትዮጵያዉያን እንዲታረዱ፣ ቤተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ የተሰጠዉ፡፡

በቆይታም ጃዋርን ማሰር ለኦሮሞ ኢስላም አንድነት አደጋ ይሆንብናል ተብሎአል፡፡ በሌላ ጎኑ እውነት ለመናገር ከ1966 አብዮት ወዲህ በኢትዮጵያ ምድር እንደ ዶር አቢይ አህመድ ያለ መሪ በዓለም መንግሥታት ሥር ያለ አገራት ድጋፍ የተሰጠዉ መሪ የለም፡፡ መመረጡም የጥንት ዓላማቸዉ እንዲፈጽምላቻቸዉ ብቻ ነዉ፡፡ ደርግን በክብር ሸኝቶ ወያኔን ሥልጣን ያስጨበጠዉ ማን እንደሆነ ይረሳልን?

ዶር አቢይን ብታወርድ እነዚያ ደጋፊዎች በሙሉ አድማ ያደረጉብናል፡፡ እንዲያም ስል በሥልጣኑ ይቀጥላል ማለቴ አይደለም፡፡ አሁን ያለዉ ብቸኛዉ መንገድ በዶር አቢይም ሆነ በጃዋር ስር ያሉ ቆሬዎችን ነፍስ ለማዳን እውነትን መናገር ነው፤ ስለ እነሱ ነፍስ ተጠያቂ ላለመሆን፡፡ መለማመጥ አይደለም፤ ከእንግዲህ በሰዎች በኩል ለኢትዮጵያ ሰላም አይመጣምና፡፡ ትናንት ትራምፕ ከዩ ኤስ ኤ (USA) ጋር በመተባበር አይ ሲስን ISIS ይዋጉለት የነበሩ ክርስቲያን ኩርዶችን ጀርባ ሰጥቶ በሶሪያና በቱርክ እንዲወረሩ ያደረገ፣ ኢትዮጵያ ምኑ ናትና ነዉ ኢትየጵያን ጅቡቲና ባርባራ ወደቦች የሠፈሩ የዉጭ አገር የጦር ኃይሎች የሚታደገዉ? የሠፈሩት ለኢትዮጵያ ካልሆነ ለማነዉ? ኩርዶችም እኮ በእስላም አገራት የተከበቡ ባንዲራቸዉም ቀይ ነጭና አረንጓዴ ሆኖ ፀሐይ ነዉ አርማቸዉ፣ ፀሐይ ደግሞ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ያለዉን የሚወክል ሲሆን ኢትየጵያም በባንዲራዋ አንበሳ በማድረጓ ጠላቶቿ በዝተዉ ነዉ

ተበትነንም አልበቃ ብሎአቸዉ ምድሪቱን ሰሜን፣ደቡብ፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ብለዉ ለመከፋፈል የቋመጡት፡፡ ኢትዮጵያን ማፍረስ ማለት የመሬትን ዋልታ እንደማነቃነቅ ነዉ፣ በእሳትም እንደመጫወት ነዉ፡፡ እስላሞች በተመለከተ፣ እውነት ለመናገር የነቢዩ ሙሐመድ ተከታዮች እስላም ሆነዉ ወደ ኢትዮጵያ አልመጡም፣ በፈቀዳቸዉ አስተማሪ አጥተዉ ሰለሙ እንጂ፡፡ ኢስላም ማለት አል-ሷፍፋት 37፡174፤ አል-ዱኻን 44፡34፤ አል- ሑጁራት 49፡14 በቅንፍ ውስጥ ያለዉን የ1997 እትም መመልከት ነዉ፡፡

የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ሰዎች፣ ኢየሱስ “አላዉቃችሁም፣ እናንተ ማን እንደሆናችሁ?” የተባሉት የኦርቶዶክስ ቤተ እምነት ተከታዮችን እንዳልሆነ ልባችሁ ያዉቀዋል፡፡ ከእናንተ መካከል አራት መቶዎቹ ተመርጠዉ ዶር አቢይ በቤተ መንግሥት ሰብስቦ ማናገሩ ከአርያም የተመረጣችሁ የመሰላችሁ ሁሉ፣ 400ዎችን ቀሳዉስት ሰብስባ ያሳረደች ኤልሳቤጥን ማስታወስ ይኖርባችኋል፡፡ አስታዉሱ አስቴር በዳኔ የተባለችዉ እህት ከቤተ መንግሥት ከአርቲስቶች ተለይታ እንድትወጣ የተደረገዉ በእርሷ ዉስጥ ያለዉ መንፈስ የሚያዉካቸዉ መሆኑ እየታወቀ፣ በክርስቶስ ስም ከዶር አቢይ ጋር ያላችሁን የመደመር ሀሳቤ፣ ከመንፈስ አንድነት ወጥታችሁ በለቅሶ ወደ አዳኛችን ካልተመለሳችሁ እናንተም መታረዳችሁ የማይቀር ነው፡፡ ምነዉ 400 ቁጥር ተመሳሰለ ብላችሁ አስባችኋል? ደግሞም አይቀርላችሁም፡፡ የኖኽን መርከብ በር የዘጋዉ እጅ፣ ዛሬም የይቅርታ እና የምህረት በር ባልተጠበቀ ጊዜና ሰዓት ሊዘጋ ይችላልና፡፡ የእናንተ ቤተ እምነት ከመቃጠል የዳነዉ ሰይጣንን ስለምታስወጡ ሳይሆን ስሙን ከሌሎቹ አብዝታችሁ ስለምትጠሩት ነዉ እንጂ በተግባር የተለያችሁ በመሆናችሁ አይደለም፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳዉስት ሱባኤ በማወጇ የአቢይን መንግሥት እንዳስደነገጠዉ፣ የፐሮቴስታንት እምነት ሲጨመር መድረሻ እንዲያሳጣዉ በአንድ መንፈስ በመሆን ራሳችሁን አዋርዳችሁ፣ ሕዝቡንም ሰበስባችሁ ጸሎት ማወጅ ነዉ የሚጠበቀዉ፡፡ “መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፣ ኢትዮጵያ አጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለዉ የተስፋ ቃል ያፋጥነዋል፣ ነገ ከተባለም ነገ እስከሚመጣ መከራዉን የሚያስቆም ምህታት የለም፡፡

የተስፋዉ ቃል ቢዘገይም ለመልካም ነዉና በፀሎት ከጸናህ ታየዋለህ፤ ሌሎችም እንዲያነቡት ብታደርግ በረከቱን ታፋጥነዋለህም፡፡

ማራናታ! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና

LEAVE A REPLY