በትልቁ ስዕል (Macro politics) እና በትናንሽ ፖለቲካዊ ክስቶች (Micro politics)፡፡ ትልቁ ፖለቲካዊ ሁኔታ (Macro politics) እለታዊ የፖለቲካ ሁኔታችንን (Micro politics) በእጅጉ ይወስናል፡፡ እኛ ሃገር ደግሞ Macro politics ማለት በገዥው ፓርቲ መንደር ያለው የፖለቲካ ዘይቤ ማለት ነው፡፡
ባለፈው ሃያ ሰባት አመት የገዥው ፓርቲ ህወሃት/ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ዘይቤ በሃገራችን የዘውግ ማንነትን አለቅጥ አስፍቶ ብቸኛው የሃገራችን ፖለቲካ ዩኒት አድርጎ፣ ያለ አቅሙ የፖለቲካችን ራስ አድርጎት ኖሯል፡፡ ይህ ዛሬ በየሰበቡ በዘር የሚያባላንን ፖለቲካዊ ስነ-ልቦና ተክሎብን አልፏል፡፡ የህወሃት መራሹ መንግስት ዘውግን አለቅጥ ለጥጦ ፖለቲካ ማለት ዘውግ ማለት ነው እስከ ማለት የደረሰበትን አካሄድ (Macro politics) ዛሬ በቀን ተቀን ህይወታችን፣ በየዩኒቨርሲቲው፣ በየሁሉ ቦታ በዘር የሚያጋድለንን፣ የጎሪጥ የሚያስተያየንን Micro politics ፈጥሯል፡፡
አሁን ፓርቲው ሲዋሃድ የዘውግ ማንነት ከተሰቀለበት የተጋነነ ሰገነት በጣም በጥቂቱ ወረድ ማለት መጀመሩ አይቀርም፡፡ ይህ ማለት ዘውግን አግንኖ የሚያናክሰን ትልቁ የፖለቲካችን ምስል (Macro politics) መቀየር ይጀምራል ማለት ነው፤ ትልቁ የፖለቲካችን ምስል በጣም በጥቂቱ እንኳን መቀየር ሲጀምር ደግሞ እለት እለት የሚያጋድለን (Micro politics) የዘውግ ፖለቲካዊ ቅኝታችንም መቀየሩ አይቀርም፡፡ ፓርቲው መዋሃዱ በአንድ ቀን የዘውግ ፖለቲካውን ያስቀራል እያልኩ አይደለም፡፡ እያልኩ ያለሁት የፓርቲው መዋሃድ በገዥው ፓርቲ ውስጥ በብቸኝነት ተለጥጦ የነበረውን የዘውግ ፖለቲካ በመጠኑ ይቀንሰዋል፤ ቀስ በቀስ ደግሞ እያከሰመው ይሄዳል ነው፡፡ ይህ እሳቤ ነው፤ ተግባሩን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፡፡ የሚሆነውን ለማየት ግን አይቶ ለመፍረድ የሚያስችል ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡
በበኩሌ በሃገሬ ፖለቲካ ኢህአዴግን በተመለከተ ተስፋ ለመቁረጥ የቀረኝ አንድ መንገድ ኢህአዴግ ተዋህዶ የሚያደርገውን ማየት ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም በአሁኑ ወቅት የሃገራችን ፖለቲካዊ እጣ ፋንታ የሚወሰነው በኢህአዴግ መንደር በሚሆን ሁነት ነው፡፡ ይህ ማለት ሃገር የምትኖረው ኢህአዴግ ሲኖር ወይ ሲሞት ነው ለማለት አይደለም፡፡በኢህአዴግ በኩል ሃገር የት ትደርሳለች የሚለውን ለማየት የመጨረሻው ዕድል ፓርቲው ከተዋሃደ በኋላ የሚያመጣውን መፍትሄ ማየት ነው ብየ አስባለሁ፡፡ኢህአዴግ ከተዋሃከ ከዛ በኋላም የማያጠግበን ከሆነ አድካሚ፣አታካች፣ምናልባትም የሚያመጣው ውጤት የማይገመት ቢሆንም ሃገር ከኢህአዴግ ሌላ የምትድንበትን መንገዶችን መፈለጉ ይመጣል ማለት ነው፡፡ለዚህ ሁሉ ግን ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡
የኢህአዴግን ውህደት የምፈልግባቸውን መንገዶች በአርቲክል የምመለስበት ይሆናል፡፡ለአሁኑ አጠር ባለው የፌስቡክ ፖስት መግለጽ የሚቻለው የፓርቲው ውህደት ማክሮ ፖለቲካውን በመጠኑም ቢሆን ይቀይረዋል የሚለውን ነው፡፡አሁን ሰው እየሞተ ስለውህደት አታውሩ የምትሉ ጓዶች ማክሮ ፖለቲካውን ትተን በማይክሮ ፖለቲካችን ላይ እንነጋገር እያላችሁ ነው፡፡ ማክሮ ፖለቲካው ሳይፈወስ ደግሞ ማይክሮ ፖለቲካው ሊፈወስ ከቶ አይቻለውም፡፡ ወገኖቻችን ስለመሞታቸው ስናወራ ማይክሮ ፖለቲካውን ብቻ እያነሳን ነው፡፡ ከላይ እንዳልኩት ይህ የመጋደል ማይክሮ ፖለቲካ እንዲቀየር ማክሮ ፖለቲካው መቀየር አለበት፡፡ ስለ ፓርቲው ውህደት የምናወራ ሰዎች ማይክሮ ፖለቲካውን ስለሚቀይረው፣የሁሉ ችግር ስር ስለሆነው ማክሮ ፖለቲካችን እያወራን ነው፡፡
ከላይ እንዳልኩት ማክሮ እና ማይክሮ ፖለቲካ ተለያይተው የሚመጡ ነገሮች አይደሉም፡፡ ስለ ማክሮ ፖለቲካው ስናወራ ማይክሮ ፖለቲካው የሚቀየርበትን (ዘውግ ተኮር ሞት የማናይበትን) መንገድ መናፈቃችን ነው እንጅ አንዳንዶቻችሁ እንደምትሉት ውህደቱን የምንፈልገው ህወሃትን ለማብሸቅ፣ ህወሃትን ከመጥላታችን የተነሳ አይደለም፡፡ ግራ በገባው ህወሃት ስሜት ላይ ተመርኩዞ አቋም መያዝ ከህወሃት መባስ ነው፡፡ሆኖም ህወሃት ውህደቱን ለምን አልፈለገውም የሚለውን ነገር መተንተኑ ደግሞ የውህደቱን አስፈላጊነት ይበልጥ ይነግረን ይሆናል እንጅ ከዛ ያለፈ ጥቅም የለውም፡፡