“እምነት! እምነት! ተመሳሳይ እምነት!” ኦሪት ዘ-ህወሀት! || ታዬ ደንደአ

“እምነት! እምነት! ተመሳሳይ እምነት!” ኦሪት ዘ-ህወሀት! || ታዬ ደንደአ

መግለጫዉ ቀጥሏል። ጌታቸዉ እንደተለመደዉ ይናገራል። የሀገር ተቆርቋሪ ሆኖ ” ህወሀት ተመሳሳይ እምነት ካላቸዉ ፓርቲዎች እና ግለሰቦች ጋር ግንባር ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለማዳን ይሰራል። ህዝቡ ከኛ ጋር ይቁም” ይላል።

አሁን ከበፊቱ የተሻለ ይመስላል። መቸም ከማፍረስ ማዳን ይሻላል። ግን መሠረታዊ ጥያቄ ይኖራል። ኢትዮጵያን ወደ ገደል አፋፍ የወሰዳት ማነዉ? ዩንቬርሲቲዎችን ከዕዉቀት ገበያነት ወደ ጥላቻ ማምረቻ ፋብሪካነት የቀየረ ማነዉ? የሀይማኖት እና የብሔር ግጭት ተፀንሶ፣ ተወልዶና አድጎ ለሀገር አደጋ እስኪሆን ሲሰራ የነበረዉ ማነዉ? ባል ምስቱን፥ አባት ልጁን፥ ወንድም ወንድሙን እንዲጠራጠር እና እንዲጠላ ያደረገ ማነዉ? በተቻለዉ ቀዳዳ ሁሉ በኢትዮጵያዊያን መሀከል የጎራ ክፍፍል እንዲፈጠር ያለእረፍት የሰራ ማነዉ? በቅርቡ ከሆነ ሀገር አምባሳደር ጋር በኢትዮጵያ ላይ የዶለተ ማነዉ? የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም አሳምሮ ያዉቃል። ጌች በዝህ ላይ ምን ይላል?

ለመሆኑ ህወሀት የሚሰበከዉ እምነት ምንድ ነዉ? ኦሪት ዘ-ህወሀት ሊባል ይችላል። መዝረፍን፣ ማኮላሸትን፣ ማሰቃዬትን፣ መከፋፈልን፣ ማጋጨትን፣ ማስመሰልን፣ መግደልን፣ ማፈንን፣ ስግብግብነትን እና ሌሎች አስነዋሪ ተግባራትን ያጠቃልላል። በፌዴራሊዝም እና በብሔር ብሔረሰብ ስም የሞግዚት አስተዳደር መዘርጋትንም ይጨምራል።

ይህ ሀይማኖት ዳግም እንዲያንሰራራ የሚመኝ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ሊኖር ይችላል። እንደተለመደዉ ይህን ያመነ በዉስኪ የተጠመቀ ለጊዜዉ ይፅናናል። እምነቱን በግላጭ መቀበሉን ገልፆ የህወሀትን “የሀገር ማዳን” ጥሪ ተቀብሎ ለምርጫ የሚቀርብ ግለሰብንና ፓርቲን ለማዬት ግን ጓግተናል። መቸም እድሜ ብዙ ነገር ያሳያል! አፍራሹም ገንቢ ይባላል!

ኦሪት ዘ-ህወሀት!

LEAVE A REPLY