ካለንበት ችግር ለመውጣት የምንነጋገርበት ጊዜው አሁን ነው
ሁሉም ሰው ለአሁኗ እና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ድርሻ አለው
በኤልያና ሆቴል
ቸርችል ጎዳና ፒያሳ
አዲስ አበባ
ቅዳሜ ሕዳር 27 ቀን 2012ዓ.ም
ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ አናሳ እና አጋር ተብለው ይጠሩ ለነበሩ ህዝቦች ዕድል በመስጠት “ሌሎችስ ?” ወይም ሌላውን ህዝብ የሚወክሉ የመንግስት አካላት አለያም ተቋማትን የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል፡፡
ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ኢህአዴግ አራቱን ክልሎች ብቻ ማለትም ኦሮሚያ ፣ትግራይ፣ አማራ እና የደብብ ብ/ብ /ህ ክልል አጠቃላይ የአገሪቱን ህዝብ በመወከል ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ከእነዚህ ብሔር ተኮር የክልል አወቃቀርን የተመለከቱ ድርጅቶች ሦስቱ ግንባር ቀደም ሲሆኑ የደብብ ብ/ብ /ህ ክልል በአካባቢያዊ ሁኔታ እና በያዛቸው የተለያዩ ብሔረሰቦች የተለየ አደረጃጀትን ይዟል፡፡
በሌላ በኩል አምስቱ ሶማሌ፣አፋር፣ ቤኒሻንጉልጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ሁለቱ ከተሞች አገራችን ባጋጠማት ቀውስ ላይ የመፍትሔ ሀሳብ ለማምጣት የሚያደርጉት ውይይት ጎልቶ አይታይም፡፡
አሁን ባለው የፖለቲካ ውጥረት እያጋጠሙ ያሉት ብሔር ተኮር እና ሃይማኖት ላይ የሚቃጡ ግድያ፣ አመፅ እና ግጭቶችን በተመለከተ አምስቱ ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚያቀርቡት የመፍትሔ ሀሳብ መደመጥ አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ኮንፍረንስም ይህን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
አናሳ ወይም አጋር ተብለው ሲጠሩ የቆዩት ክልሎች በኢትዮጵያዊነታቸው እንደሌሎቹ ሁሉ በሚፈጠሩ ችግሮች ተጎጂ ሆነው ሳለ ባለፉትም ሆነ በአሁናዊ ችግሮች ሀሳባቸው ሲደመጥ ባለመታየቱ አሁን ያለንበትን ችግር እነዚህ ህዝብን የወከሉ ክልሎች እንዴት ያዩታል? በችግሩ ላይ ምን አመለካከት አላቸው? ከዚህ ችግር ለመውጣት ምን ያስፈልጋል? ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ያላቸው የመፍትሔ ሀሳብ ምንድነው? ያለን ነገር ምንድነው? ያጣናውስ? ምንስ መስራት እንችላለን? ለሚሉት ጥያቄዎች የየራሳቸውን ሀሳብ የሚገልፁበት መድረክ አዘጋጅተናል፡፡
ግጭቶች ሲፈጠሩ ብዙ ህዝብን በወከሉት ብሔሮች መካከል የተፈጠረ የመምሰል መልክ ሲኖራቸው ሌሎችም ችግሩን መፍታት እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ ምንም አይነት ምክንያት ቢቀመጥም እነዚህን ህዝቦች በአገራቸው ጉዳይ እንዳለፉት ዘመናት ከማግለል ይልቅ አንዳችን ለሌላችን በሰላም የምንኖርበትን መንገድ መፍጠር ትልቅ ዋጋ አለው፡፡
በለውጡ 18 ወራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እነዚህን ህዝቦች የደገፉባቸው ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡በኢትዮጵያ የጋራ ራዕይ እንዲኖርም ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ እንደ ብዙሀኑ ህዝብ ሁሉ በነዚህ ክልሎችም ለሚኖሩትም ኑሯቸውን የሚያሻሽሉ የተቋማዊ አሰራር ለውጥ መደረግ እንዳለበት ይታመናል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ብሔር ተኮር በሆነው የፌደራሊዝም ስርዓት ምክንያት እየተፈጠረ ያለው ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል፡፡ ከዋና ማሳያዎቹ አንዱም ችግሩ ከፈጠረበት አካባቢ አኳያ የቅርቡ 86 ሰዎች የተገደሉበት እና አብያተ ክርስቲናት እና መሰጊዶች የተቃጠሉበት ጥቃት ብሔርን እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያመለክታል፡፡
በዚህ የፍትህ ጥያቄ ጎልቶ በተጠየቀበት ወቅት ንፁሀን ተገድለዋል፤ በፀጥታ አስከባሪዎች አካባቢም ወንጀልን እንደመከላከል ለራስ የመወገን አዝማሚያዎች መታየታቸው ችግሩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም የማያዳግሙ ርምጃዎች አለመወሰዳቸውም ችግሩ እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለም ስራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ለከፋ ድህነት እየዳረገ መሆኑም ይታወቃል፡፡
ይህ ኢትዮጵያ ሌሎች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የገቡ አገራት ዕጣ ፈንታ እንዳይገጥማት የማንቂያ ደወል ነው፡፡ በብሔር አክራሪነት ከሚመጣ ችግር አገራችንን የምንታደግበት ጊዜው አሁን ነው፡፡
ይህንን በማሰብ አናሳ ወይማ አጋር ተብለው የቆዩ ክልሎች እና ቡድኖች በአገር ጉዳይ ላይ ጠንካራ ውይይት ሊያደርጉ በሰላም ግንባታ ላይ በጋራ ሊሰሩ ይገባል፡፡
ይህ ወቅት ኢህአዴግ እነዚህን ህዝቦች አጋር ሲል የቆየበት ጊዜ አብቅቶ በአገራቸው ጉዳይ እኩል የመሳተፍ እና የመወሰን አቅም እንዲኖራቸው በአዲስ መልክ ፓርቲውን የተቀላቀሉበት ወቅት ነው፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም፡፡በቀዳሚነት በፓርቲው ውስጥ ቀደም ሲል የነበሩ አሰራሮች ስለመወገዳቸው ርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም አብሮ መስራት ይገባል፡፡ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስቶ በመወያየት እና በመደማመጥ የተሸለው ላይ መተማማን ያስፈልጋል፡፡በዚህ ጊዜ አናሳ ወይም አጋር ተብለው የቆዩት ክልሎች የሚሰሩበት የጋራ ስለሆነችው አገር የተሸለ ዕድል የሚናገሩበት ወቅት ነው፡፡
ለሁሉም ነገር መሰረታዊ ለሆነው ሰላም ሁሉም ዜጋ እና ሁሉም ቡድን ሌላው ሊደረግለት የሚፈልገውን ይፈልጋል፡፡ ለኛ ጥሩ የምንለውም ለሌሎች ያስፈልጋቸዋል፡፡ እውነታውን መቀበል ግድ ነው፡፡ ሁላችንም የመልካሙም ነገር የችግሩም ተጋሪ እንደመሆናችን ያለፈው ጊዜ ችግር መረሳት የለበትም፡፡የወደፊቷን ኢትዮጵያ መልካም ነገር እንዲበላሽ የሚያደርጉትን ልንፈቅድላቸው አይገባም፡፡ እንደሰው በአገራችን ጉዳይ ላይ አንድ ሊያደርጉን በሚገቡ ጉዳዮች ላይ እንዴት አንድ መሆን እንዳለብን ማወቅ አለብን፡፡እኛ የሰው ልጆች በዘርና በጎጥ መከፋፈልም የለብንም ከዚህም በላይ ስለሆንን፡፡
እኛ ሰዎች ነን፡፡ በፈጣሪ ዘንድ እኩል የተፈጠርን፡፡ሰው በመሆናችንም ለራሳችን ና የኛ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የመቆም ኃላፊነት አለብን፡፡ እኛ ሰዎች ፈጣሪ ለትልቅ ዓላማ እና ዋጋ እንደፈጠረን ሁሌም መገንዘብ አለብን፡፡ ጥሩና መጥፎን እንድንለይ ማመዛዘኛ ህሊና ያለን፤ ሌሎችን መጉዳት ፣ መግደል ፣ ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ሰው በመሆናችን ብቻ የምናውቅ ነን፡፡ ሰው በመሆናችን ብቻ መልካም ነገሮችን መከተል እና ሌሎችን የመጠበቅ ሀላፊነት አለብን፡፡ ለምን? ብለን ብንጠይቅ ለራሳችን ለማህበረሰባችን እና ለአገራችን ምቹ ሁኔታን እንፈጥራለን፡፡
ህግ እና አስገዳጅ ሁኔታዎች ለሰው ልጆች እጅግ በጣም ያስፈልጋሉ፡፡ስናጠፋ ራሳችንነ ማረም እና ከስህተታችን መማር፤ ከተሳሳተው አመለካከታችንም መመለስ አለብን፡፡ይቅርታን መጠየቅ እና ይቅር ማለት የሰው ልጅ የትም ቦታና መቼም የሚጋራው ባህሪ እንደመሆኑ ልናደርገው ይገባል፡፡ ይህ ከፈጣሪ የጠሰጠን ኃላፊነት ነው፡፡
አናሳ ወይም አጋር ሲባሉ ለቆዩት ክልሎች የ “ሰው ነኝ “እንቅስቃሴ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡ ይህም ለዘላቂ ፍትህ፣ ሰላም እና ነፃነት ጥሩ መደላድል ለመፍጠር ይረዳል፡፡ ሰው በመሆናችን ብቻ የታደልነው ነገር ቢኖር ለአገራችን ሰላም እኛ ሊደረግልን የሚገባውን ለሌሎችም በማድረግ ነው፡፡
እነዚህ ክልሎች በአገር ጉዳይ ያላቸውን ሀሳብ እና አመለካከት ለማጋራት የፊታችን ቅዳሜ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅተዋል፡፡ በአገሪቱ ያሉ በአገራቸው ሰላም እና አንድነት ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችና ድርጅቶችም ይገኛሉ፡፡
ሰውነት ከዘር እንዲቀድም ከማንኛውም የከፋ ልዩነት ተላቀን ሌሎችን እንደራሳችን እንድንወድ ፈጣሪ ይርዳን፡፡ይህም መብት ብቻ ስለሆነ ሳይሆን ሁላችንም ነፃ ካልወጣን የአንዳችን ነፃ መውጣት ነፃነታችንን ዘላቂ ስለማያደርገው ነው፡፡
እንነጋገር እንደማመጥ
ለተጨማሪ መረጃ
Mr. Obang Metho,
Executive Director
E-mail: obang@solidaritymovement.org;