የአሁኑ እንጃ እንጂ፣ በመለስ ዜናዊ ጊዜ በመላው የዓለም ዙርያ ባሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የደህንነት ዘርፉ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በአድዋ ተወላጅ የህወሃት ካድሬዎች የተያዘ ነበር።
ይህ የውጪው ጉዳይ ሲሆን፣ ትግራይም እግርና እጅዋን አስረው እያሰቃይዋት የሚገኙት የስብሃት ነጋ የአድዋ ተወላጅ ሹመኞች ናቸው።
ታድያ አንድ ጊዜ ስብሃት ነጋ የተባሉት የህወሃት ባለቤት የአድዋ ሰዎችን ስብስበው፣ “በእናንተ ስንፍና ህወሓት ስልጣንዋን ብትለቅ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ተወላጆችን፣ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ እናንተ የአድዋ ተወላጆችን አሳደው እንደሚያጠፏችሁ እወቃችሁ ድርጅታችሁን ጠብቁ” ብለው አስጠንቅቀው ነበር።
የአድዋ ካድሬ አገዛዝ ለጠላትህም የማትመኘው እጅግ ኋላ ቀር፣ “ከየት አምጠተህ በላህ፣ ከየት አምጥተህ ጠጣህ የሚል” አጅግ ዘግናኝ የሆነ ውዳቂ ሥርዓት ነው።
“Injustice anywhere is a threat to justice everywhere,” ብሎ ነበር ማርቲን ሉተር ኪንግ። ትግራይ ከትህነግ የባርነት ቀንበር እስካልተላቀቀች በስተቀር፣ ኢትዮጵያ ሰላም እና ፍትህ ይነግሳል ማለት ትልቅ ስላቅ ይሆናል።
ማስረጃ
ለአብነት ያክል ነብዩ ስሑል ሚካኤል የተባለው እጅግ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ምሁር የተንቤን ህዝብ በአድዋ ካድሬዎች መገዛት አቅለሽልሾት የኛ ሰው የት ሂዶ ነው በስብሃት ነጋ ካድሬዎች የምንገዛው በማለት የሚከተለውን በማስረጃነት ለቋል።