በ1997 ሰኔ ላይ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ! ምርጫ መጭበርበሩን ተከትለዉ ተማሪዎች በአንድነት ተቃዉሞ አነሱ። በማግስቱ FBE ካምፓስ ወያኔ ቅዱስ ቁርአንን ቀዶ በማይሆን ቦታ አስቀመጠ። የተማሪዉ አንድነት ፈርሶ አንዱ ሌላዉን በጎሪጥ ማየት ጀመረ። ወያኔ ላይ የተጀመረዉ ተቃዉሞም ከሸፈ። ስለዝህ ከፋፋይ አጀንዳን በጥንቃቄ ማየት ነዉ!
ወያኔ የኖረዉ በብሔርና በሀይማኖት ክፍፍል እና ግጭት ነዉ። በክርስትና እና በእስልምና እጁን አስገብቶ ከፋፍሏል። በማገጨት አስታራቂ ሽማግሌ ሲሆን ከርሟል። የሀይማኖት መሪዎችንም አስሮ ገርፏል። አሁንም በብሔርና በሀይማኖት ግጭት ከተቀበረበት ሊነሳ ይፈልጋል። ከጀሌዎቹ ጋር በዩንቨርሲቲዎች የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ሞክሮ ህይወት እንዲጠፋ አድርጓል። በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሶማሌ ክልሎች በቤተ-እምነቶች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም አድርጓል። የሀይማኖት ግጭትን ለማፍጠርና ለማስፋፋትም ጥሯል።
ባለፈዉ ቅዳሜ ሞጣ ላይ መስኪዶች ተቃጥሏል። አለማዉ የሀይማኖት ጦርነት መለኮስ ነበር። ግቡ ደግሞ ለዉጡን መቀልበስ እና ኢትዮጵያን መበታተን ነዉ። ማንም ቢፈፅመዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን እኩይ ተግር ሊያወግዘዉ ይገባል። ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎችም ድርጊቱን ኮንኗል። በወንጀሉ የተጠረጠሩ ከ 30 በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ተይዟል።
በሞጣዉ ቃጠሎ ከሁሉም በላይ ወያኔ የሙስሊሙ ተቆርቋሪ ሆኖ ወጥቷል። በመደበኛና በማህበራዊ ሚዳያዎች ብዙ ይሰብካል። ግን በምን ሞራሉ ወያኔ ስለእስልምና ይናገራል? ሀይማኖቱን ስከፋፍል እና መሪዎቹን አስሮ ስገርፍ የነበረዉ ማን መስሎታል? በነገራችን ላይ ወያኔ ኢትዮጵያን ለመግዛትም ሆነ በትኖ ለመሄድ የብሔርና የሀይማኖት ግጭትን እንደ ቁልፍ መሳሪያ ለመጠቀም ከመነሻዉ አቅዶ ሰርቶበታል። አሁን ህብረተሰቡ መንቃት ያለበት ይመስለኛል። በዝህ ወቅት የተቃዉሞ ሰልፍ ሳይሆን የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። መንግስት ተጠርጣሪዎችን በመያዝ ስራዉን ጀምሯል። ህዝቡ ይህን በሁለት መልኩ ሊያግዝ ይገባል።
በአንድ በኩል ተጠርጣሪዎችን ይዞ ለህግ ለማቅረብ ይተባበራል። በሌላ በኩል ደግሞ ተጨማሪ ችግር እንዳይፈጠር ቤተ-እምነቱን እና አከባቢዉን በንቃት ይጠብቃል። ይህን ማድረግ የጠላትን ሴራ በማክሸፍ ሀገርን ያሻግራል! ደግሞም እዉነት ሁሌም ያሸንፋል!
ምንድ ነዉ የሆነዉ?
ማን አደረገዉ?
ለምን አደረገዉ?
ብለን ካልጠየቅን በተሳሳተ መንገድ እንሄዳለን። የሚጠቅመንን ትተን የሚጎዳንን እንሰራለን!
የቤተ-እምነቶች ጉዳይ
በጥንቃቄ ይታይ!