|| በጋዜጣዉ ሪፓርተር ||
[የክቡር ሚኒስትሩን ቢሮ አንድ የክፍል ኃላፊ በርግዶ ገባ]
- ምን ሆነሃል?
- ምን እየተደረገ ነው ክቡር ሚኒስትር?
- መጀመሪያ ሥርዓት ይኑርህ እንጂ፡፡
- የምን ሥርዓት ነው?
- በሩን እንዴት በርግደህ ነው የገባኸው?
- ተናድጄ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምንድነው ያናደደህ?
- እዚህ መሥሪያ ቤት እየተደረገ ያለው ነገር ነዋ፡፡
- እኮ ምንድነው?
- ክቡር ሚኒስትር እኛ እኮ ለዚህች አገር ሕይወታችንን ሳይቀር የገበርን ሰዎች ነን፡፡
- ለመሆኑ እናንተ ማን ናችሁ?
- እሱን ልብዎት ያውቀዋል፡፡
- ምን ፈልገህ ነው አሁን?
- ይኸው የበረሃ ጓዶቻችንን ሥልጣን ነጥቃችሁ አባረራችኋቸው፡፡
- እኛ አላባረርናቸውም ሸሽተው ነው የሄዱት፡፡
- ትንሽ ግፍ አትፈሩም ግን?
- ጆሮዬ ነው ወይስ ግፍ ስትል ነው የሰማሁት?
- ምነው ክቡር ሚኒስትር?
- እናንተ ደግሞ ስለግፍ ለማውራት የሞራል ብቃቱ አላችሁ?
- ምን እያሉ ነው?
- ከእናንተ በላይ ግፈኛ ታይቶ ይታወቃል እንዴ?
- ተው ክቡር ሚኒስትር ቀን ጥሎን ነው እንጂ እንደ እኛ ሩህሩህ የለም፡፡
- ስማ አገሪቱን ለዚህ ያበቃችሁ ግፈኞች ናችሁ፡፡
- እ…
- ከራሳችሁ ውጪ ለማንም ግድ የማይሰጣችሁ አረመኔዎች መሆናችሁን አጥተኸው ነው?
- ለነገሩ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል ስለተባለ ምን እልዎታለሁ?
- አገሪቷን እንደ ግል ንብረታችሁ ቆጥራችሁ ስትፈነጩባት አልነበር እንዴ?
- ክቡር ሚኒስትር ውለታችን በአንዴ ተረሳ ማለት ነው?
- የምን ውለታ ነው?
- በድርቅ ትታወቅ የነበረችን አገር በልማት እንድትታወቅ ያደረጋት ማን ሆነና?
- ተወኝ እስቲ፡፡
- ምነው?
- ሙሉ አገሪቱ ትልቅ እስር ቤት አልነበረች እንዴ?
- ለማንኛውም ለእኛ እንዲህ አይገባንም ነበር፡፡
- ምን ተደረጋችሁ?
- እዚህ የቀረነውም ተጠቅልለን እንድንገባ ነው እንዴ የፈለጋችሁት?
- ምን እያልክ ነው?
- ይኸው ከኃላፊነታችን እንድንዘዋወር ደብዳቤ ደርሶናል እኮ?
- አላሠራ አላችኋ፡፡
- ምን ማለት ነው?
- ሁሉን ነገር እያደናቀፋችሁ ምን እናድርግ ታዲያ?
- ምን አድርገን ነው ያደናቀፍነው?
- በቢሮክራሲው ውስጥ ተሰግስጋችሁ ምንም ነገር መተግበር አልቻልንም፡፡
- ስለዚህ እኛን ከቦታ ማፈናቀል ጀመራችሁ?
- ያው በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም አይደል ተረቱ፡፡
- አሁን የተመደብንበት ቦታ ግን አይመጥነንም፡፡
- ምን እያልክ ነው?
- ከነበርንበት ቦታ የወረደ ነዋ፡፡
- የበፊቱን ቦታ በአቅማችሁ እኮ አይደለም የያዛችሁት፡፡
- ታዲያ በምንድነው?
- በጉልበት!
[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ባለሀብት ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]
- እንዴት ነህ?
- አለሁ ግራ እንደገባኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምንድነው ግራ የሚያጋባህ?
- ሁሉ ነገር ነዋ፡፡
- እንዴት?
- አገር ውስጥ አይደል እንዴ ያሉት ክቡር ሚኒስትር?
- ምንድነው የምትለው?
- ማለቴ ሁሉ ነገር መላ ቅጡ እንደጠፋው ያውቃሉ ብዬ ነዋ፡፡
- አልገባኝም?
- ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው ቢሉ ብቻ ሁሉ ነገር ግራ ያጋባል፡፡
- ስማ የኢትዮጵያ መፃኢ ዕድል እኮ ብልፅግና ነው፡፡
- የበፊቶቹም እንዲህ ነበር የሚሉን፡፡
- እ…
- ይኸው ባዷችንን አስቀርተውን እብስ አሉ እንጂ፡፡
- አሁን እኛና እነሱ የምንነፃፀር ነን?
- ያልጠረጠረ ተመነጠረ አይደል የሚባለው?
- እ…
- መጠርጠሩ አይከፋም ብዬ ነው፡፡
- ለስሰሰሰበበስማ እኛ እኮ የእነሱን ጥፋት ለማረም ነው እየሠራን ያለነው፡፡
- የእናንተንስ ጥፋት ማን ነው የሚያርመቡበየእናንተንስ ጥፋት ማን ነው የሚያርመው?
- ምን አበበምን አጠፋን?
- ምን አሉምን አሉኝ?
- አአአበበበበአናጠፋም እያልኩህ ሳይሆን ይኼን ያህል ምን የሚያስመርር ነገር አየህ ብዬ ነው፡፡
- ዓይዓይንዎን ከፍተው ካዩ እኮ ብዙ ነገር አለ፡፡
- ማማለት?
- ሕገሕገወጥነቱ፣ ዝርፊያው ኧረ ስንቱ?
- እእኛ እኮ የምንሠራው ሕገወጥነትንና ዝርፊያን ለማጥፋት ነው፡፡
- ክቡክቡር ሚኒስትር እንግዲያው እውነቱን ልንገርዎት?
- ነንንገረኝ፡፡
- እጭራሽ ብሶበታል፡፡
- ምምኑ?
- ሕገወሕገወጥነቱና ዝርፊያው ነዋ፡፡
- እእ…
- ይኸይኸው በየቦታው አይደል እንዴ መሬት የሚወረረው፡፡
- እሱ በቅርቡ መፍትሔ ያገኛል፡፡
- መሬቱ ተወሮ ካለቀ በኋላ መፍትሔ ምን ያደርጋል?
- እ…
- ዝርፊያውም ቢሆን ተባብሶበታል፡፡
- ማን ነው የሚዘርፈው?
- መንግሥት እኮ ሥራ መፍጠር ሲያቅተው ሌባ እየፈጠረ ያለ ነው የሚመስለው፡፡
- እ…
- ከተማዋ ውስጥ ያለ ዝርፊያ እኮ እየተባባሰ ነው፡፡
- ለማንኛውም ሥራችንን በሚገባ እንድንሠራ የአንተ ድጋፍ ያስፈልገናል፡፡
- የምን ድጋፍ ክቡር ሚኒስትር?
- የገንዘብ ድጋፍ ነዋ፡፡
- ማለት?
- ለአዲሱ ፓርቲያችን የገንዘብ ድጋፍ አድርግልና?
- በሉ ክቡር ሚኒስትር እንደ እኔ ሌላ ሰው እንዳይሰማዎት?
- ለምን?
- ባለፀጋ እኮ…
- እ…
- ይሰጣል እንጂ…
- እ…
- አይለምንም!
[ክቡር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር ተገናኙ]
- አሁን አመንኩ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምኑን?
- ዘመኑ የብልፅግና እንደሆነ ነዋ፡፡
- እንዴት?
- እናታችን ስታበድረን ነዋ፡፡
- እናቴ ሞተዋል አላልከኝም ነበር እንዴ?
- የሁላችንም እናት እኮ ነው ያልኩዎት?
- ኢትዮጵያን ማለትህ ነው?
- የለም! የለም!
- ማን ናት እናታችን ታዲያ?
- አይኤምኤፍ ናት፡፡
- እ…
- ሁሉ ነገር አለቀለት እኮ በቃ፡፡
- እንዴት?
- ቻው ቻው ነው ማለት ያለብን፡፡
- ማንን?
- ድህነትን ነዋ፡፡
- እንዲህ በቀላሉ?
- ቢያንስ እኔና እርስዎ ማለት እንችላለን፡፡
- ለምን?
- ከማንም በፊት የምንቋደሰው እኛ ነና፡፡
- ምኑን?
- ዶላሩን ነዋ፡፡
- እ…
- ክቡር ሚኒስትር መወሰን እኮ ነው ያቃተኝ፡፡
- ምኑን?
- የቱን ቢዝነስ እንጀምር የሚለውን ነዋ?
- እ…
- የኮንስትራክሽን ዕቃ እናስመጣ ወይስ መኪና የሚለውን መወሰን አልቻልኩም፡፡
- የደላህ ነህ እባክህ?
- እንዴት?
- ዶላሩ እኮ ለአገሪቱ እንጂ ለአንተ አይደለም የሚለቀቀው?
- ክቡር ሚኒስትር ከሰፈፏማ ካልበላን ሥልጣናችን ምን ሥልጣን ነው?
- እ…
- እንደዚህ ዓይነቱ ዕድል መቼም አይገኝም፡፡
- እንዴት?
- በዚህ ግርግር ወቅት የድርሻችንን አንስተን ዞር ማለት ነዋ፡፡
- ምን እያልክ ነው ሰውዬ?
- ምነው ክቡር ሚኒስትር?
- አዲሱ ፓርቲያችን እኮ እንዲህ ዓይነት ነገር አይፈቅድም፡፡
- የድርሻችንን እናግኝ እንጂ ለእሱ ችግር የለውም፡፡
- ምን እያልከኝ ነው?
- የድርሻችንን ካገኘን ክቡር ሚኒስትር…
- እ…
- ፓርቲ ብንቀይርስ ምን ችግር አለው?
- ከምን ወደ ምን ነው የምንቀይረው?
- ከብልፅግና…
- እ…
- ወደ ብልግና!
[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]
- ክቡር ማኒስትር ጆሯችንን አደማችሁት እኮ፡፡
- በምን?
- በዚህች ሳተላይት ዜና ነዋ፡፡
- የቀና ብዙ ያወራል፡፡
- ገና ከመላኳ አገሮች ዳታ ለመግዛት ጠየቁ ብላችሁ ዜና ትሠራላችሁ?
- ምን ችግር አለው?
- ለነገሩ ዜናው ላይ ዳታ መሸጥ ያልቻልነው ዋጋ ገና ስላልወጣለት ነው አለማለታችሁም ጥሩ ነው፡፡
- ቀልደህ ሞተሃል?
- ሳተላይቷ ከዚህ ብትመጥቅ ኖሮ ግን ምን ልታደርጉን ነበር?
- እናንተንም አብረን እንልካችሁ ነበራ፡፡
- ህዋ ላይ?
- እህሳ፡፡
- ይኼን ያህል ጠልታችሁናል እንዴ?
- ለማንኛውም የሳተላይቷ ነገር ምነው አንገበገባችሁ?
- ኧረ ምንም፡፡
- በቅርቡ ድሮን ልንሠራ ነው፡፡
- ምን አሉኝ?
- ሰምተሃል እባክህ?
- አለቀልን በሉኛ፡፡
- ስነግርህ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ የሁሉን ነገር ከፍታ ትረግጣለች፡፡
- ምን እኛንም ልትረግጡን አስባችኋል እንዴ?
- መቼ ይቀርላችኋል?
- እ…
- ሳተላይቷ እኮ ሁሉንም ነገር እየተከታተለች ትልክልናለች፡፡
- ምን?
- ከዚህ በኋላ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ሳይቀር እናውቃለን፡፡
- እንደዚያ ከሆነማ ልፈትንዎታ ክቡር ሚኒስትር?
- ምንድነው የምትፈትነኝ?
- አሁን ምን እየጠጣሁ ነው?
- እሱንማ ሳተላይትም ሳንልክ ልነግርህ እችላለሁ፡፡
- እኮ ምን እየጠጣሁ ነው?
- ውስኪ፡፡
- በምን?
- ደረቁን!