ባሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች አሰላለፋቸው ወደፊት ሩቅ ዘመን ሳይውስድ ለጦረነትና
ለብዙ ግጭት ሊያስገባ በሚስያችል ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው። ይህ እውነታ አስቅድሞ ካልተመከረበትና መስመር ካልያዘ ውጤቱ ለማናቸውም ሳይሆን ኪሳራና አስከፊ ይሆናል። የውጭ ሃይሎችም ይህን ልዩነት
በመጠቀም የራሳቸውን ጥቅም ሊያራምዱበት ይችላሉ።
በፖለቲካ ሃይሎቹ መካከል ላለው ሲፊ የአመለካከት ልዩነት መንሴ ታሪካዊ እንዲሁም ውስጣዊና ከሃገር
ውጭ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች የራሳቸው ድርሻ አላቸው። እስካሁን ድርስ በሰላማዊ መንገድ ተቀምጠው
የተውያዩበት፣ የተከራከሩበት እንዲሁም የተግባቡበት መድርክ ባለመኖሩ ልይነቱ ይብልጥ እይሰፋ የቅራኔ
የጠላትነት ስሜት በተከታዮቻቸው መካከል ሊስፍን ችሏል።
ባሁኑ ወቅት ጎልቶ የሚታየው የፖለቲካ አሰላልፍንን በሁለት ዋነኛ አመልካከት ልንከፍለው የምንችለው
ነው።
1. የኢትዮጲያ የፖልቲካ ችግር የጎሳዎች መካክል ያለው የበታችና የበላይነት ታሪካዊና ወቅትዊ ክስተቶች
ዋነኝ መንሴ ነው ብሎ የሚያምነው ሲሁን ይህም አመለካክት እያንዳንዱ ጎሳ ወይም ቤሂርሰብ ወይም
ብሄር ራሱን በራሱ ያስተዳድር እንዲሁም እስከመገግነጠል የሚያሳችል መብት ይኑር ብሎ በዋናኝነት በጎሳ
ላይ የተመሰርተ የፊዴራል አስተዳድር በኢትዮጲያ እንዲመስርት የሚያቀነቅነው ሃይል ነው፡፤
2. የኢትዮጲያ የፖለቲካ ችግር ዋነኛው የዲሞክራሲ አስተዳድር አለምኖርና የግለስቦች ሰባአዊ መብት
አለመከብር ነው ብሎ በዋናኝነት የሚያምነው የፖለቲካ ሃይል ሲሆን ህዝብ የመረጠው አስትዳድር
ታሪካውና ወቅታዊ ችግሮችን ይፈታል ብሎ የሚያምን ሲሆን አገራችን በጎሳና ቋንቁዋ ላይ የተመሰርት
ፌዲራልዊ አስትዳደር አላስፈላጊ ነው የሚል ነው። የተወስነው የዚህ ክፍል በፌደርላዊ አስትዳደር
የሚያምን ሲሆን ግን በጎሳና ቁንቋ ላይ የተዋቀረ መሆን የለበትም ብሎ ያምናል። ሌላው የዚሁ
አስትሳስብ ክፍል ደግሞ አሃዳዊ አንድ ወጥ መንግስት ይዋቀር የሚል ሲሆን ቁጥራቸው ግን አንስተኛች
ናቸው።
እንዚህ ሁለት አመልካከቶች ባሁኑ ዘመን ራሱን የቻለ ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል። የጎሳ ፖለቲካ
የሚያጥነጥነው ክንፍ በብዛት ባልፉት 50 አመታት ገነው በተትርኩ ታሪክ ቀመስ ፖለቲካዊ
ፕሮፓጋንዳዎች ሰልባ የሆኑ፣ እንዲሁም ስልጣን ባቋራጭ በዚህ መንግድ ይግኛል ባሉ የፖለቲካ ሊሂቃን
እንዲሁም ባልፉት 50 አመታት የነበሩ በጎሳ መካከል ያሉ ልዪንቶችን የጭቆና ዋንኛ መግልጫዎች
ናቸው ብለው ያመኑ በብዛት ከከተማ አክባቢ ራቅ ያሉና በመለስትኛ ከተሞችና ከመሃል አገር ራቅ ባሉ
ገጠርማ ያገራችን ክፍሎች በሚኖሩ ወግኖች ተክታዮች ሲኖራቸው፡ እንዚህ ወገኖች ሌላኛውን የፖለቲካ
አመለካክት ሌሎችን ድፍጥጦ የሚገዛ አንድ ወጥ አሃዳዊ መንግስት አቀንቃኞች አድርገው ይከሷቸዋል።
የዲሞክራሲ አስትዳድርና የሰእባዊ መብት አለመከብር ያስከትለው ችግር ነው ብልው የሚያምኑት ደግሞ
ተከታዮቻቸው አብዛኛውን በዋና ከተማና ትላልቅ ከተሞች ያሉ፤ በብዛት ካንድ በላይ ጎሳ ተወላጅ በሆኑ
እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍ ያሉና በንግድ በመንግስት ስራ እንዲሁም በተለያዩ የሞያ ዘርፍ ያሉ ወግኖች
ናቸው። እንዚህ ወግኖች በጎሳ መካከል ያለው ልዩነት ዲሞክራሲያዊ ስራአት ሲመስርት ችግሩ ይፈታል
ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ አንዳንዶቹን የጎሳ ፖለቲካኞችን በጠባብነት እንዲሁም ዘርኝነት ወይም ለውጭ
ሃይል ተገዢዎችና ጸረ-ኢትይጵያዊነት የሚከሷቸው አሉባቸው።
ኢትዮጲያ የብዙ ጎሳዎች፣ ቋንቋ፣ እምነት ባህልና ትሁፊት ያሉባት አገር ናት። በዘመናት በነግስታቱ የሃይል
እርምጃና እንዲሁም በተለያዩ ጎሳዎችና እምነቶች መካከል በነበረ ድርድርና ስምምነት የቆየች፤ ግዛቱዋ
ሲስፋና ሲጥብ የኖርች ታሪካዊ አገር ናት። የክርስትና እምነት በተለይም የእስልምና እምንት መስፋፍትን
ተከትሎ ብዙ ታሪካዊ ፋይዳ የተካናውኑ ቢሆኑም ባለፉት 200 አመታት ደግሞ የአውሮፓውያንና
የኮሊያኒስቶች የአፍሪካን መቀራመት ሩጫ በኢትዮጲያና ባካባቢው ባሉ ግዛቶች ያስከትለው ተጽኖ አሁን
ለሚታየው ልዩንቶች ያሳደረው ተፅኖ ትልቅ ነው።
ዘመናዊ ኢትዮጲያን የመሰረቱት ዳግምዊ ሚኒሊክ አስትዋጾ ደግሞ በተለያዩ የህብረተሰባችን ክፍል
የተለያየ እንዲሁም የሚቃረን አመለካክትን ፈጥሯል። በጀግንነትና የዘመናዊነት ፋና ወጊ አድርጎ
የሚያይቸው ህብረትሰብ ክፍል እንዳለ ሁሉ ሌለው ደግሞ ባረመኔነትና በክፋት የሚመልከታቸው ወገን
አለ። ይህ አመልካክት ብቻ ሆኖ የቀር ሳይሆን ያንዳድን ፖለቲካ ሃይሎችን አሰላለፍ መስመር እስክማስያዝ
ድርስ ዘልቋል።
በኢትዮጲያ ያሉ ወገኖች ሁሉ የሚያግባብቸውና የሚያቅራርብችው ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ እምንታዊ
እንዲሁም በጋራ ጠላቶቻችውን መምክታቸው እውንታ እጅግ የሚያስተሳስርቸው ሲሆን ጎልቶ የሚነግርው
የተጋነን ልዩነትቸውን ካልተመክረበትና ካልተዋያዩበት የጋራ እሴታችውና በአንድ አገር መሆናቸውን
ሊንደው ይችላል።
የነበሩት አገዛዝ በሙሉ በህዝብ ፈቃድ የተመርጡ አስተዳድሮች ባለመሆናቸው ምክንያት ሁሉንም ዘዴ
ተጠቅመው አገዛዝቸውን ሲያራዝሙ ኑረዋል። አንዳንዶች እምነትን፣ ጎሳን፣ የዘር ሃርግን፣ እንድሂም
በዘምናት አግዛዞች በፈጠሩት የባህል፣የቋንቋ ና የግለስብ ከፍታና ዝቅታ አድርጎ የሚያይ አምለካክትን
ሁሉ እይተጠቀሙ ህዝቡን ሲገዙና ሲጨቁኑ ኖረዋል።
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ቦኋላ ባአለማችን ውስጥ የዚህን አይነት አገዛዝ እይጣሉ ዘመናዊ እና የህዝብ
ምርጫ ያለው አስትዳድር የመሰርቱ አገራት እጅግ ተበራክተዋል። ያለመታዳል ሆኖ በኢትዮጲያ ዙፋን ላይ
የተቀመጡ ወገኖች ግን ያንኑ የድሮውን ዘዴ ዘመናዊ ካባ አስለብሰው የጭቆና አገዛዝ ሲገዙ ቆይተዋል።
ባልፍት 50 አመታት በተለይም በቀደሙት 27 አምታት በትህነግ (ወያኔ) መራሹ መንግስት በኩል በ
ኢትዮጲያዋያን ላይ የተሰራ ግፍ በወንድማምቾች መካከል ልዮነትን በማጉላትና በማናከስ ላይ የተመሰርተ
አገዛዝ ስለነበር ቀድሞ የነበረው ችግር ላይ ሌላ እሳት በመጨመሩ በትግል ያሉ የፖለቲካ አመላካከቶች
ልዩንታቸው እንዲስፋና በጠላትነት እንዲታያዩ ትልቅ ድርሻ ተጫውቷል።
ከ ሚያዚያ 2018 (EC) ጀምሮ በተፈጠርው የለውጥ ሂደት በዶ/ር አብይ የሚመራው መንግስት
በወሰደው እርምጃ ለመጀምርያ ግዜ በታሪካችን ሁሉም አይነት አመለካክት ያላቸው ነፍጥ ያነሱትንም
የፖለቲካ ሃይሎች ጨምሮ በአገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ በመፈቀዱ ህዝቡ ሁሉንም አይነት የፖለቲካ
ፕሮፓጋንዳና መዘዙን ለመካፈል በቅቷል።
ምንም እንኳ በ ዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመራው መንግስት ስልጣን በያዘ መጀመርያ ወራቶች የወሰዱት
እርምጃዎች አብዛኛውን ወገኖቻችን ያስደሰተና የአለም አገራትን ያስደነቀ ቢሆንም ለውጡን ተከትሎ
ሊከትሉ የሚችሉትን ውጢቶች ያልተጠኑና ዝግጅት ያልተደርግባቸው በመሆኑ ያስከተለው ጣጣ ብዙ ነው።
የለውጡን መንግስት ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ክፍሎችን ያላካተተ በመሆኑ የተፈለገው ለውጥ ግማሽ
መንግድ ላይ የቆመና እንዲንገዳግድ አድርጎታል። በይብልጥ በዋናኝነት ሊሰራ የሚገባውን ወዲፊት ሊፈጠሩ
የሚችሉ ችግሮችን የሚቀንስና ህዝቡን ለሰልማዊ ለውጥ እንዲሁም ትልቅ የመንፈስ ልእልና ያድርስ
የነበረውን የቤሄራዊ የእርቅ፣ የመግባብት፣ የመነጋገር ና የአገር ምስርታ ጉባኤ ወይም ስራዎች
ባለመሰራቱ አሁን ለተከሰተው ችግርና ለወዲፊትም ሊከስቱ የሚችሉ ልዩንቶችን እንዳይቀርፍ አስችሏል።
ይህ ተድርጎ ቢሆን ኖሮ በዳይና ተበዳይ ይቀር ተባብሎ ፤ የተጓደለ ፍትህና ካሳ ተስተካክሎ በታሪክ ላይ
የነበርውን ልዩንት ትቶ በወድፊቱ ላይ የሚያተኩር ስምምነት ላይ የደረሰ ንቁ ማህብረሰብ ይፈጠር ነበር።
በግንቦት ወር 2020 ይደረጋል የተባለው ምርጫ በህዝቦችና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካክል መልካም
ውይይትና መስማምት ሳይድርግ በቶሎ ሊድርስብን ነው። ይህ ንግግርና ስምምነት ሳይደርግ የሚከናወን
ምርጫ መፍቴ ከመሆን ይልቅ ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህም ይህ ስጋት በሁሉም
ዘንድ አጽኖት ተሰጦት ወደ ውይይትና ድርድር ቶሎ ተድርጎ ስምምነት መደርስ አለብት ወይም ምርጫው
መራዘም አለብት።
ምንም እንኳ ቤሂራዊ አገር አቀፍ እርቅና የይቀርታው ጉባኤ የረፈደበት ቢሆንም (የ በፊቱ በድልና ጥፋት
ላይ የዶ/ር አብይ መንግስት ከመጣ ጅምሮ እጅግ ብዙ ወገኖች በ ሞት እርዛት ስድት ደርሶባቸዋል)
በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ግን በመካከላቸው ያለውን ልዮነት ለማጥበብና ሊከትል የሚችለውን ደም
አፍሳሽ ቅርሾዎችን መቀንስ ይቻላል።
የዲሞክራትክ ችግር ነው ዋንው መንሲኤ የሚለው ከፍል የሌሎቹን የወንድሞቹን በጎሳ ፖለቲካ
የሚያምኑትን ተቀምጦ ብሶታቸውን መስማት፣ በታሪክ ሂደት ላይ ያሉ አተራርኮችን በመስማማታ ወይም
በጨዋነት በልዩንት መስማምት ነገር ግን ታሪክን አሁኑኑ በመኖር ሳይሆን የአሁኑንና የወደፊቱን እጣ
ፈንታችን ላይ አተኩሮ መነጋገርና መስማምት። በቋንቋ፣ ባህል፣እምነት በእኩልነት የሚታይበትን መንግድ
መምልክት። የቡድን መብቶችን ለመንጋገርና ለመስማማት መዘጋጀት አለበት።
የጎሳ ፖለቲካ ዋነኛ ነው ብሎ የሚያምነው ክፍል ሌሎች ወንድሞቹን የሚያቀርቡትን የዲሞክራሲ ስርአትና
የግለስቦች መብት ሊያስከትል የሚችለውን ውጤትና ተባብሮ መስራት ሊያመጣስ የሚችለውን አገራዊ፣
ዜጋዊ እንዲሁም የቡድን መብትን ለመነጋገር፤ ከሌሎች አገር ልምድ ለመውስድ፤ የአገራችን ጠላቶች
ልዩንታችንን ለራስቸው ጥቅም እንዳይጠቀሙብን ለመተማመንን መዘጋጀት አለበት። በተጋነን ታሪክ ላይ
የሚነገር ፕሮፓጋንዳን መተውና በእውነትኛ ታሪክዊ ሂደቶች ላይ ለመስማማት እንድሁም ልዩነትም ካለ
ለመቀበል ነገር ግን ወደፊት የበላይነትና የበታችነት እንዳይፈጠር የሚያስችል መንግስታዊ ስራአትን
ለመምስርትን ለመምልክት መዘጋጀት ያስፈልጋል።
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጲያን ራሳቸውን ባንድ ጎሳ አጥር ውስጥ መሆን የማይፈልጉ ወግኖች
መኖርቸውን በማወቅ የነሱን መብት የሚከበርበትና እኩል ለሁሉም የሚሆን ድርሻ ያለው ስራአትን
መመልክት ያስፈልጋል። ይሄ ቦታ ለኔ ይግባኛል በሚለው ከመጣልት ይልቅ ያን ቦታ በጋራ እንዴት ለሁሉም
ተጠቃሚ ማደርግ እንደሚቻል መሰራትዊ ስምምነት ለማድረግ መዘጋጀት ያስፍልጋል።
በነዚ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ከተደርሰ ምርጫውን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በእጅጉ የሚቀርፍ
ስልሆነ ሁሉም የፖለቲካ ሓይሎች በተለይም መንግስትና የምርጫ ቦርድ ይህን ዋና ነገር ቅድሚያ ሰጠተው
ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አደርጋለው።
(1st January 2020)