አውስትራሊያ አምስት ሺህ ግመሎችን በጥይት ገደለች || ታምሩ ገዳ

አውስትራሊያ አምስት ሺህ ግመሎችን በጥይት ገደለች || ታምሩ ገዳ

በተፈጥሮ አየር መዛባት ለከፍተኛ ድርቅ እና የዱር ሰደድ እሳት የተጋለጠችው አውስትራሊያ ሰሞኑን ከአምስት ሺህ በላይ የዱር ግመሎችን መጨፍጨፏን ይፋ አደረገች፣ እርምጃው ከመብት ትልሟጋቾች ባንድ ቁጣን አስከትሏል።

ከደቡባዊው የአውስትራሊያ፣ አብሮጂኒ ግዛት የተከሰተው ድርቅ ያስከተለው የምግብ እና የውሃ እጥረትን ለመቋቋም ያቃታቸው በርካታ ግመሎች ወደ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ቢማስኑም የጠበቃቸው ከሂሊኮፕተር ላይ የተርከፈከፈ የአልሞ ተኳሾች የጥይት እሩምት ነበር። አውስትራሊያ አንድ ሚሊዮን የሚገመት የዱር ግመል ያላት ሲሆን ለአምስት ቀናት በዘለቀው የጸረ ግመል ዘመቻ ከአምስት ሺህ በላይ ግመሎች ከእያሉበት ታድነው ተገለዋል።

በድርቅ የተነሳ ከዜጎቹ ጸረ ግመሎች አቤቱታ የቀረበበት የአውስትራሊያ መንግስት በአጠቃላይ አስር ሺህ ግመሎችን ለመግደል እቅድ ይዟል። ግመሎች ከሌሎች እንስሳት ጋር ሱነጻጸሩ ድርቅን እና የበረሃ እሳትን የመቋቋም ልዩ ችሎታ እንዳላቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ ።

የአውስትራሊያ ባለስልጣናት ለዜና ሰዎች እንደገለጹት ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ለምግብ እና ለመጠጥ ፍለጋ ተግተልትለው የመጡት ” የዱር ግመሎች” ለደህንነት ጠንቆች ናቸው” ብለዋቸዋል። ግመሎች በአውስትራሊያኖች ዘንድ “መጤ እንስሳት /non native animals” ተደርገው የሚቄጠሩ ሲሆን በአውስትራሊያ መሬት የረገጡት እንደዛሬው ባቡር እና መኪና ብብዛት ባልነበረበት እኤአ 1840 የቀኝ ገዢዎቻቸው በነበሩት፣ እንግሊዞች፣ አማካኝነት ለሰዎች እና ለሸቀጦች ማጓጓዣነት ታስበው እንደነበር የተለያዩ ዘገባዎች ይገልጻሉ። የግመሎቹ በጅምላ መጨፍጨፍ በእንሰሳት መብት ተሟጋቾች ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ እና ትችት የገጠመው ሲሆን የአውስትራሊያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ተቃውሞውን ያስተባብላሉ።

ካለፈው አምስት ወራት ጀምሮ በአውስትራሊያ የተለያዩ ግዛት ውስጥ የተከሰተው የዱር እሳት ከአስር ሚሊዬን ሄክታር በላይ ደን እና ከሁለት ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ወደ አመድነት ሲቀይር፣ አውስትራሊያን በአለም ማህበርፕሰብ የምትታወቅበት ካንጋሮን፣ ኮአላ ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንስሳት የቃጠሎው ሰለባ ሆነዋል።

ለአንዱ ወርቅ፣ ለሌላኛው ጠጠር….?

ከሁለት መቶ አመት በላይ በአውስትራሊያ ውስጥ መኖር የጀመሩት ግመሎች በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ተቀባይነት ባይኖራቸውም በተቃራኒው በመካከለኛው ምስራቅ እና መሰል አገራት ውስጥ “የበረሀው መርከብ” የሚል ስያሜ ያለው ግመል ከ መደበኛ እድከቅንጦት የትራንስፓርት መጓጓዠነቱ ባሻገር ሙሽሮች ሲጋቡ በጥሎሽ መልክ ይቀርባል፣ ስጋው በልዩ በዓላት ቀን ለምግብነት፣ ወተቷም እንዲሁ ለቸኮሌት እና ልብስኩት መስሪያነት ይውላል። የግመል ጸጉርም እንዲሁ ከልብስ ምፕድሪያ አንስቶ ለተለያዩ ማስዋቢያነት ይውላል።

ከዚህም በተጨማሪ እንደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬት ባሉት አገራት ውስጥ የግመሎች እሩጫ እና የግመሎች የቁንጅና ውድድሮች ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል። አውስትራሊያ ውስጥ ብዙም ትኩረት ያላገኙት ግመሎች በኢትዬጵያ ሆነ በአረቡ አለም ዋጋቸው ቀላል አይደለም።ለምሳሌ ያህል እኤአ 2008 በ አል ዳፍራ ፌስቲቫል (አረብ ኤሜሬት) ላይ አንድ ግመል ሁለት ሚሊዬን የእንግሊዝ ፓውንድ(ከሰማኒያ ሁለት ሚሊዮን ብር) በላይ ለማውጣት ችሏል።

LEAVE A REPLY