ይድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ!! || ገብረመድህን አርአያ

ይድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ!! || ገብረመድህን አርአያ

|| የትግራይ ርእሰ መስተዳድር የህ.ወ.ሓ.ት. ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው? አጭሩ የሂወት ታሪክ ||

አውስትራሊያ ፐርዝ ጥር ወር 2020 ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህ.ወ.ሕ.ት.መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው።

ደብረፅዮን ወደ ህ.ወ.ሓ.ት. የተቀላቀለው በመጨሻው 1974 ዓ.ም አካባቢ ነው ። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል ። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታየ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!! የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋ መምራት ይችላል ወይ? ነው፤ የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲሊም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታልች 1 ሃልቃ ፀጋይ በርሄ 2 አባይ ወልዱ ተመርታለች 3ኛውና ክፉ አረሜነው የሃገርና የህዝብና ጠላት በሆነው “ደብረፅዮን ገ/ሚካኤ አሁንም ትግራይ እየተገዛች ነው። ትግራይ በራስዋ ልጆች ለምን አትመራም? የሚል ጥያቄ ከህዝቡ ቢነሳም በሕ.ወ.ሃ.ት. መሪዎች መልስ አያገኝም ፤ሾላ በድፍን;/ ከመቀሌ፤ ውቅሮ ‹ሁለት ዓውላዕሎ› ፤አጋሜ፤ ተምቤን፤ ዓድዋ፤ አክሱም፤ ሽሬm እንዳስላሴ፤ ማይጨው፤ የክልሉ ተውላጅ የመምራት ብቃት ያላቸው የሉምን? የሚል ጥያቄም ቢነሳም የሉም ሳይሆን የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊሲ በመሆኑ ብቻ ነው።

ፖሊሲው ት.ነ.ህ.ግ፣ (ህ.ወ.ሓ.ት) የትግሉን የጀመረበት ዋናው የትግሉ መነሻው ትግራይን ከጨቋኙ የአማራው መንግሥት(ኢትዮጵያ)ተገንጥላ ታላቅዋን የትግራይ ሪፓብሊክ መንግሥት ስለምትመሰረት ድሮም ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ፤ ወደ ውጭ ሃገር መውጫ በር፤ሰፊ የእርሻ መሬት ስለሚያስፈልጉ ከወሎ ከአለውሃ ምላሽ ራያ ድረስ ፤ከጎንደር ወልቃይት ጠለምት ጠገዴ ሁመር እስከ አርማጮህ መተማ ድረስ ጠቅልሎ የመውረር ወራሪው ድርጅት ህ.ወሓ.ት.ወደ ትግሉ ደደቢት በረሃ የወጣው ይህን ሁሉ በሚከተለው የትግሉ ፖሊሲ አዘጋጅቶ ነው ደደቢት የገባው።በዚህ ወቅትም በብዛት የተቀላቀሉት ትውልደ ኤርትራውያን ናቸው በአረጋዊ በርሄ የሚመራው ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. እነዚህ ኤርትራውያን ለከፍተኛ የስልጣን ኮረቻ ካደረሳቸው እንዲያውም ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን የበቁ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው፤ ትግራይ በነዚህ ጠላቶች እጅ የወደቀችም መነሻው ከዚህ ነው፤። ትግራይ ክ/ሃገር ብቻ ሳይሆን በሃገር ደረጃ ኢትዮጵያም አሁን እየደረሳት ያለው ምስቅልቅልና ለክፉ የመበታተን አደጋ ሌሎች ችግር የዳረጋት ከዚሁ ተያይዞ የመጣም ነው፤እነ መለስ ዜዊም ኢትዮጵያን ለ27 አመት ገዝተዋል መርተዋል በወያኔ የመጡ ኤርትራውያን የባንዳ ልጆች ከመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያን በመጥፎ ስሜትና ጥላቻን ኢትዮጵያን ያወግዛሉ አምርረው ይጠላሉ ።

ህ.ወ.ሕ.ቶች በትግራይ ብቻ አይደልም ይህን የአገዛዝ ስርአት ያሰማሩት አማራም በስመ ብ.አ.ዴ.ን. አማራ በራሱ ልጆች ሳይሆን በኤርትራውያንና በትግራይ መሪዎች በነ በረከት ስሞኦን ታደሰ ካሳ ህልዊ ዮሴፍ ካሳ ተ/ብርሃን ወ.ዘ፣ተ፣ እየተመራ ለብዙ ችግርና ሞት፤ ስደት ተዳርገዋል በእጅ አዙር ባንዳዎች በትግራይ በኤርትራውያን የአማራ ገዝተውታል ። ይህም የወያኔ ፖሊሲ ነው የአማራውን ህልውናው ለማጥፋት በህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች ከትግሉ መነሻ ጀምሮ የወጣና የታቀደ ፖሊሲም ነው ። የአማራው ኢትዮጵያዊ ባካሄደው ፀረ ህ.ወ፣ሕ፣ት፣ መራር ትግልና ከባድ መስዋእትነት ከ40 ዓመታት በላይ ከፍሎ ፤ ባሁኑ ጊዜ ነፃ ነው፤ ባንዳ የባንዳ ልጅ ጠራርጎ በማባረርና በማሰር ነፃ ሆኖ በራሱ ልጆች እየተመራ ነው ይህም ትልቅ ርምጃ ነው። በትግራይ ይህ የለም በኤርትራውያን አገዛዝ አሁንም እንደወደቀች ናት።

ለዚህም ተጠያቂውም ህ.ወ.ሓ.ት. ነው።ደብረፅዮን ገ/ሚክሰኢል በአስመራ ዩኒቨርሲት የኢጂነሪንግ ተማሪ ነበረ፤ትምህርቱን አቋርጦ ተ.ሓ.ኤ. (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ) ጀብሃ ተቀላቀለ በዚህ ድርጅት ሰልጥኖ በአስመራ ውስጥ ስዉር ፈዳያን ( ፈዳያን የአረብኛ ቃል ነው ትርጉሙ ሽብርተኛ፤ ገዳይ ፤ ነብስ አጥፊ ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛው TERRORIST ማለት ነው።

ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የጀብሃ ፈዳያን ሆኖ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሂወት የቀጠፈና ያጠፋ ሰው ነው፤ይህም ከፍተኛ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃይ መለስ ዜናዊ ወ.ዘ.ተ. በማያሻም ሁኔታ ያውቃሉ ፤ሌላ የደብረፅዮን ማንነት የሚያውቁ ብዙ ናቸው ፤የዛሬው “ሞኦ ወያኔ አይተ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ንጉሰ ዘትግራይ » ትግራይ እየገዛ ያለው ጀብሃ ታጋይ ነበር። ጀብሃም ሆነ ደብረፅዮን በጀመሩት የትግል መንገድ ብዙ አልሄዱበትም፤ ሻዕብያና ጀብሃ ከመነሻው የትግል ጉዛቸው የከረረ ጠብ ስለ ነበራቸው ጀብሃ በሻዕብያ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳና ጥቃት ያደርስበት ስለነበረ ለሻዕብያ አስቸጋሪ ጊዜ ነበ፤ ሻዕብያም በዚሁ ችግር ትግሉን ለማካሄድ የማይችል መሆኑን ስለተገነዘብ ችግሩን ወደ ሚያልቅበት ወሳኝ የሆነ የእስትራተጂ መፍትሄ ሃሳብ ገባ እስትራተጂካዊወታደራዊ ዝግጅቱም ነደፈ አጠናቀቀ።

ከሕዳር ወር 1972ዓ.ም. አንስቶ ሻዕብያ ሙሉ ወታደራዊ ዝግጅቱን አጠናክሮ ሠራዊቱን በማሰለፍ በጀብሃ ላይ በማያዳግም የጥቃት ዘመቻው ከፈተ ጀብሃ ተፈረካከሰ በየቦታው በየውግያው ሽንፈቱን ፅዋዉን ተከናነበ የጀብሃ ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ተበታተነ ወሳኝ ፍልምያ ጦርነቱ ታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም. በሁለት ወር ውስጥ ተገባደደ፤ ጀብሃ ከኤርትራ ምድር ድምጥማጡ ጠፍቶ የትግሉ ሂወት አበቃ Dead ። ብዙ የጀብሃ ታጋዮች ተማረኩ ከጥቂት ጊዜ በኋል ምርኮኞቹ ወደ ምትፈልጉት ሃገር ሂዱ በማለት ሻዕብያ በነፃ አሰናበታቸው፤ የደብረፅዮን ገብረሚካኤል ሓቀኛ ታሪኩ ከዚሁ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ኤርትራ ገብቶ ለመኖር ስለማችል መጠግያ ፍለጋ ወደ ህ.ወ.ሓ.ት.ሸራሮ መጣ እንዴት እንደተቀላቀለ ሚስጥሩን የሚያውቅ ተክሉ ሓዋዝ ብቻ ነው እሱም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየ ሚስጢሩ ማወቅ አይቻልም፤ለሌላ አስቸጋሪ ቢሆንም እነ ስብሓት ነጋ ግን የደብረፅዮን ማንነት ያውቃሉ ካለ እነዚህ የትግራይ መሳፍንቶች እውቅና ውጭ የሚድረግ የለም።

ተክሉ ሓዋዝ ወደ 02 ወታደራዊ ማሰልጠኛ ልኮት የአንድ ወር ስልጠና ወስዶ እንደጨረሰ በእንስሣት የጭነት ማጓጎዣ መደቡት ቦታው ግን የሚመጥነው አልነበረም የ02 አመራሮች አንስተዉት እንደነበርም ይናገሩ ነበር ሚስጢሩ ግን ስብሓት ነጋ ከህ.ወ.ሓ.ት. ታጋይ በተለይ በክፍሎች ተመድበው ከሚሰሩ ታጋዮች ጥሩ ግንኝነት ፈጥሮ ትውውቁ እንዲያጠናክር ሆን ብሎ ያደረገው ሲሆን ከማጓጓዣው አውጥተዉም በብዙ የተለያዩ ክፍሎች እየተመደበ መስራቱ ይታወሳል፤ ደብረፅዮን የካድሬ ትምህርት የተማረው መለስተኛ ካድሬ ነው ከዚም አልዘለለም ቢሆንም ግን የተማረ ሰው ነው በጊዜው በህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ታማኝነቱን አላረጋገጠም ነበር ማለቱ በቂ ነው።

በመጨረሻ በ1979 ዓ.ም. ግንቦት ወር ደጀና ላይ የህ.ወ.ሓ. ት ማሌሊት ኮንፈረንስ የ5ቀን የካድሬዎች ኮንፈረንስ ስብሰባ በሙሉ መሳተፉን አውቃለሁ አብረን ነበርን ትውውቃችን ቀደም ያለ የነበር ቢሆንም፤ በዚሁ በስብሰባ መሳተፍ ግን ለደብረፅዮን የመጀመሪያው ጊዜ ናት ጌታቸው አሰፋም ነበር ለሱም የመጀመሪያው ናት እነዚህ ሁለቱ በዚሁ ኮንፈረንስ መሳተፍ ማለት በስብሓት ነጋና በመለስ ዜናዊ ሙሉ እውቅና ማግኘታቸው ያረጋገጠም በቂ ማስረጃ ነው። በተረፈ ደብረፅዮን በዝቅተኛ ሰራ ተመድቦ መኖሩ ሁሉ ታጋዩ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፤ ደብረፅዮን እጅግ በጣም ተንኮለኛ መርዘኛ እባብ ነው፤ ደብረፅዮን ቁጡና ገልፍተኛ ባህሪ አለው ተሳዳቢም ነው ፤ ቂመኛ= ሰውን የማጥቃት ቂሙና በቀሉን ለመበቀል ፍላጎትና ምኞቱ እቅዱን በድብቅ የሚያከናውን በማር የተለወሰው መርዙ በአስመሳይ ባህሪው የማወናበድ ዘዴው የተካነ ነው።

ለምሳሌ አሁን እየተጠቀመበት ያለውን ማየት በቂ ነው፤ ለአብነት ፤የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል nፍላጎቱ አለው በግልፅ እየተናገረ ነው ፤ ብሎ በሬድዮና በተሌቭዥ ደብረፅዮን የተናገረውን እናስታውስ፤ ትግራዋይ በመሆናቸው ብቻ እየተለዩ እየታሰሩ ናቸው ፤ትግራዋይ በመሆናቸው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ቦታዎች እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፤ሃብት ንብረታቸው ወድመዋል ብዙ ትግሬዎችም ተገድለዋል ወ.ዘ.ተ ወ.ዘ.ተ’ በማለት አደገኛ የውሽት ፈጠራው ወደ ትግራይ ህዝብ በማሰራጨት ንፁሁን ህዝብ የሚያስጨንቅ ከወንድሙ በሰላም በፍቅር ከኖረበት ኢትዮጵያ ሃገሩ እየለየ አንተን ሊያጠፉህ ኤርትራና አማራው ተንኮል እያሴሩብህ ነው፤ እያለ የትግራይን ህዝብ እያስጨነቀ የሚገዛው ያለው በዚሁ ዘዴው በኢትዮጵያ ህዝብ ግጭት ለመፍጠርም ነው ይህም የወያኔ መርዎች እቅድም ነው።

የትግራይ በሰላም እንዳይኖር ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ለማለያይት ያልቻለው የትግራይ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት. ከተፈጠረባት እለት አንስቶ በባርነት በመያዣ የታሰረ ህዝብ ከኤርትራ የመጡ የባንዳ ልጆች በስመ ታጋይ ህ.ወ.ሓ.ት. የሚገዛና የሚመራ ለችግርና መከራ የተዳረገ ኢትዮጵያዊ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ነው። የሚመራው የትግራይ ሰው የለም ማለት ነው? ወይስ መሪ የመሆን ብቃትና ችሎታ በትግራይ ተፈልጎ ስለታጣ ነው? ይህን የሚመልሱት ሻንጣ ተሸካሚው የህ.ወ.ሓ.ት ማእከላይ/ኮሚቴውና፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ትርፍራፊ ለቃሚ ካድሬዎች፤ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ ብቻ ናቸው። የትግራይ ህዝብ ለሰቆቃና መከራ የዳረጉትም እነዚህ አጋሥስ ማ/ኮሚቴና ካድሬዎቹ ከተጠያቂነትም አያመልጡም ።የትግራይ ነፃ ህዝብ ከኤርትራ በመጡ የማፍያ ስብስብ ወንጀለኞች ተከቦ የተያዘ ነው።

አሁንም ለወደፊትም የትግራይ ህዝብም እንዲህ ሆኖ መኖርም ስለማይቻል ካሳለፍከው የ45 ዓመታት ስቃይና የሰቆቃ የወያኔ የባርነት አገዛዝ በስምህ እየነገዱ ባንተ ስም እየዘረፉ ኢትዮጵያን ያፈረሱ የስንቱን ኢትዮጵያዊ ህዝብ ሂወት የገደሉ ያጠፉ የህ.ወ.ሓ፣ት፣ወያኔ የወረበላ ወንጀለኞች ስብስብ ዛሬ ይብቃኝ ብልህ መነሳትና እነዚህ ማፍያዎች ማስወገድ በኢትዮጵያዊነት ሃላፊነትም የታሪክ ግዴታ አለብህ።

በአሁኑ ጊዜ ትግራይ ኢትዮጵያን ያደሙ ኢትዮጵያ በዝርፍያና በሙስና ሌብነት አጥንት ብቻ ያቀርዋት ህዝብዋን ጭምር የገደሉ ያጠፉ በህዝባዊ ሃይል ከስልጣናቸው የተወገዱ የወያኔ ማፍያ ስብስብ ምሽግ ሆናለች፤አሳዝኝ።ይህች የጀግኖች የአርበኞች የኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር ሰፈር ምን ጉድ ወረደባት።

ደብረፅዮን በቀን 7 ጊዜ ይዋሻል አስመሳይ ውሸታም ነው ይህም የሚጠቀምበት ዘዴውም ህዝብ ለህዝብ ለማጋጨት ነው፤ በመቀሌ በህዝብ ፊት የዋሸው ሽሬ ሂዶ በህዝብ ፊት ቁሞ ይክዳል 7 ጊዜ ይዋሻል 7 ጊዜም ይክዳል፤ ከሃዲ ውሸታም ባህሪ የተጠናወተው በተለይ ህዝብ ለህዝብ የማጋጨት ድብቅ የተንኮሉ ሤራው ነው፤ ደብረፅዮን በህዝብ ላይ ይሳለቃል ህዝብን ይሳደባል በትግሉ ጊዜ ከገብሬዎች ለስራ አህዮች ለመሰብሰብ ወደ ገበሬዎቹ ሲሄድ ስዎቹን እየተሳደበ እየመታ በጉልበቱ የፈለገውን ይዞ ይሄዳል ገበሬዎቹም ያማረሩበት ጊዜ ነበር፤ ለሰው ልጅ ክብር አይሰጥም ከባለጌነቱ የተነሳ ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ቀናት በድምፅ ወይኔ የተናገረው አሳፋሪ ንግግር ለሰባዓ እንደርታ ለዓጋሜ ህዝብ ለተምቤን ህዝብ በአንድ ደምሮ ባንዳና ባንዳዎች ናችሁ ብሎ ህዝቡን መሳደቡን እናስታውሳለን በትግርኛ አንድ ተረት አለ “ ዘመን ያ ግርምቢጥስ ማይ ንዓቅብ”ይህ ማለት ዘመን ሲገላበጥ ውሃ ወድ ሽቅብ “ ይፈሳል የትግራይ ህዝብ ባንዳ አይደለም፤ በኢትዮጵያዊነቱ በጀግንነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ያስመሰከር ጀግና ህዝብ ነው፤ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነፃነት አንድነት ሲል ከጠላት ባእድን ወራሪዎች ለእናት ሃገሩ ኢትዮጵያ የሞተና አጥንቱ የከሰከሰ በኢትዮጵያ ታሪክ ያስመሰከረ ኩሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ነው።

የወያኔ መሪዎች የትግራይ ህዝብ ታሪክ አያውቁምና። ባንዳ ማለት እሱ ራሱና የወያኔ መሪዎች መቀሌ ውስጥ በምሽግ ተደብቀው ያሉት በራሱና በስብሓት ነጋ የሚመሩ ናቸው ዘር ከዘራቸው ባንዳዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ በዚሁ አይታማም ።ትግራይ ዛሬ በባንዳዎች እጅ ወድቃለች በአፈ ሹም ባንዳ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የምትመራ ከኢትዮጵያ አፈንግጣ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ ሁናለች ለማለት እንችላን ረእሰ መሪዋ የኢትዮጵያ ትእዛዝና መሪነት አይቀበልም ትግራይ የሌቦች፤ የወንጀለኞች፤ ሃገር ያፈረሱ ህዝብ የገደሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ንብረት የዘረፉ ሌቦች መኖሪያ ምሽግ ሆናለች። በመሳፍንቱ የወያኔ መሪዎች እጅ ወድቃለች።

በባድመ በተነሳው ግጭት ኤርትራና ኢትዮጵያ መሃከል የስንቱን ሂወት የቀጠፈው ስንት ሃብት ንብረት የወደመበት አስከፊ አሳዛኝ ጦርነት ወቅት በሁለቱ በደም በሥጋ በታሪካቸው የተሳሰሩ ህዝብ ይህን መከሰቱ ታሪክ ይቅር የማይለው የማይረሳው ነው።የህ.ወ.ሓ.ት.ወያኔው መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ የ27 አመት የጨለማ የሲኦልና ሶቆቃ ዘረኛ አገዛዙ በህዝባዊ ትግል ብርታትና መስዋእትነት ወያኔ ከሥልጣኑ ተወግዶ ሲጣል በወቅቱ የመጡ ዶ/ክ አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ተቀባይነትና ድጋፍ በማግኘት በኢትዮጵያ ሙሉ ባለሥልጣ ሆኖውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖው ተሾሙ ወያኔ እንደ ለመደው ሲሸነፍ መሸሽ ልማዱ ወደ መቀሌ ጓዙን ሸክፎ የፈረጠጠው እዚያውም ወደ ምሽጉ ገብቶ ተቸንክሮ ቀረ፤ አረሜናዊ ስርአቱም አብሮት በምሽግ ጉድጓዱ ተቸነከረ ።በዚህ ጊዜ ዶ/ክ አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስተር ሆነው እንደተሾሙ የወያኔው የ27 ከፉ የጨለማ ዘመን አገዛዝ አከተመ ።

ዶ/ር አብይ አህመድ ሥልጣኑ እንደተረከቡም የመጀመሪያ የሰላም እጃቸው የዘረጉት ወደ ኤርትራ ነው እቅዳቸውም ወደ መተግበር ገቡ፤ ብዙ ችግር የነበረበት ባድመ በተፈጠረው ግጭት በሁለቱ ወንድማዊ ህዝብ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሊከሰት የማገባው ደም አፋሳሽ የተካሄደው ጦርነት የስንቱን ሂወት የቀጠፈ ስንት ሃብትና ንብረት ያወደመ ለ20 ዓመታት ሙሉ በህዝቡ መሃከል ስጋትና ፍርሃት የነገስበት አስቸጋሪ ውጥረት ለማጥፋት የኢትዮጵያው መሪ ዶ/ክ አብይ ከኤርትራ መሪ ፕረዚዳንት ኢሳያሳ አፈወርቅ የሰላም የፍቅር የወንድሟሞች ውይይት ተካሂዶ የእግዚአቢሄር መልካም ፈቃድ ተጨምሮበት በሁለቱ ሃገራትና በህዝብ ዘላቂ ሠላም ወረደ። ኤርትራም የኢትዮጵያዊያን ቤት ማረፊያ ሆነች ኢትዮጵያም የኤርትራውያን ማረፊያ ቤት ሆነች ሁለቱ ወንድማዊ ህዝብ በሰላምና በፍቅር ተቃቅፈው ዛሬ ይገኛሉ። ለወያኔ ግን ይህ የሰላም የፍቅር መንገድ አልተዋጠለትም:: የኤርትራ ህዝብ የኢትዮጵያ በተለይ ኩታ ገጠም ድንበር ያላቸው አማራና ትግራይ በእልልታና ደስታ ሲያከብሩት።

መቀሌ የመሸገው የወያኔ ፀረ ህዝብ ቡድን አእምሯቸው የዛለ በድን መሳፍንት
እነ ስብሓት ነጋ የእነዚህም አፈ ሹም ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለተፈጠረውና ለመጣው እርቀ ሰላም አደባባይ ወጥተው አወገዙት በሁለት አምባገነን መሪዎች የሚፈጠር ስላም አይገኝም አሉት ። ከነዚሁ ያልተለየ ውግዘት የሰነዘረው የTAND (ታንድ)ም/ሊቀ መንበር ግደይ ዘርአፅዮን በLTV ቴሌቭዥ ጣብያ የተገኘው ሰላም አውግዞ በሁለት አምባገነን መሪዎች ሰላምና ስምምነት አይፈጠርም ሰላም አይገኝም በማለት አወገዘው ።ኮተታሙ ግደይ ዘራፅዮን ውግዘት ለወያኔ መሳፍንቱ ለነ ስብሓት ነጋ አስደስቶ ርፍራፊው ለመልቀም ያቋመጠ ነው።ቂመኛው ደብረፅዮን ግን የራሱ ቂም በቀሉን መወጣጫ አደርገዋለሁ ለሚለውን የትግራይ ህዝብ ሰላም እንዳያገኝ ሻዕብያ መጣብህ ሊያጠፋህ ነው እያለ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ኡፈይታ አግኝቶ አርሶ ሰርቶ ሰላማዊው ኑሮው እንዳይኖር በትግራይ ህዝብ ከባድ ጫና በመፍጠር ማለቅያ የሌለበት ጦርነት ሊማግደው ስለሚፈልግ ሻዕብያ በጀብሃ ያደረሰው ጥቃት በትግራይ ህዝብ ደም ብቀላውን ሊወጣ ፍላጎቱ ግልፅ እየሆነ ነው።

በዚህ ብቻ ደብረፅዮን አልተወሰነም በትግራይ ክልል ድንበር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ወንድሞቹ በደምና በሥጋ ዝምድና የተሳሰሩ ህዝብ አካሉ የሆኑት የአማራ ክልል በጎንደርና በወሎ በአፋር ክልል ወ.ዘ.ተ. የመሬት ወረራ በትግራይ ስም እየፈፀመ፤ ህዝብ ለህዝብ እያጋጨ ያለው ይህ ከኤርትራ የመጣ የህ.ወ.ሓ.ት. ጉዳይ አስፈፃሚ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ነው።የትግራይ ህዝብ ከወንድሞቹ እያጋጩ ችግር እየፈጠረ፤ችግሩን እየሎኮስ የእሳት ጭድ የሚያቀጣጥለው ያለ የትግራይ መሪ ተብየው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዋና ተጠያቂም ነው።

ከኤርትራ ከጎንደር ከወሎ ከአፋር ከሸዋ ከጎጃም ወ.ዘ.ተ.የትግራይን ህዝብ እያጣላ ጥላቻም እየፈጠረ እያራራቀ የህዝብ እልቂት እንዲከሰት የውሸት ዲስኩሩ እያስፋፋ ይገኛል፤ ይህም ዋናው የወያኔ የእለት ሥራና ተግባር ሆነ በየቀኑ የሚታይ ሓቅ ነው።የትግራይ ህዝብ ሰላምና እፎይታ ካጣ እንሆ ዛሬ 45 አመቱን ሞልቶታል፤ በወያኔ የባርነት ሰንሰለት ከወደቀ የአንድ ትውልድ ዘመን ሆኖታል። የትግራይ ህዝብ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የሃገሩን ዳር ድንበር አስከባሪ ኢትዮጵያዊ ጀግና በዚህ የወያኔ አሰቃቂ ኑሮ ነፃነቱ የተቀማ ህዝብ በወያኔ ተገድሎ ተረሽኖ ያለቀ የትግራይ ህዝብ ነው።

ይህ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ጀግና ትግራዋይ ዛሬ በወያኔ የባርነት ሸንሸል ታስሮ አንገቱን ቀና አርጎ መሄድ የማይችል ቀናም ካለ አንተ ባንዳ እየተባለ እየተሰደበ ስቃይና መከራ በወያኔዎች እየደረሰበት ይገኛል ።ደብረፅዮን የግሉ ቂም በሻዕብያ የቋጠረው በትግራይ ህዝብ ስም ኤርትራውያን ሊበቀል ሊበቀል ይፈልጋል፤ የትግራ ህዝብ በሻዕብያና በጀብሃ የተከሰተው ነገር ምንም አያውቀም፤ የተከሰተው በኤርትራ ውስጥ በሁለት ኤርትራውያን ወንድማሞች መሃከል ነው ፤ለምን ደብረፅዮን የትግራይ ህዝብ ወደ ማያውቀው የማይመለከተው የጦርነት እሳት ትግራይን ሊማግድ ፈለገ? ህዝብ ፍርድህን ስጥ!! ከትግራይ አጎራባች ክልሎች ከጎንደር፤ ከወሎ፤ ከአፋር ወንድማዊ ህዝብ ደም እያቃባው ይገኛል።

ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለምን ትውልድ ሃገሩ ኤርትራ ሂዶ ሜዳው ፈረሱ ካገኘ አይበጠብጥም (ዓዲያ ዘይብሉስ ዓደይ ዓድዋ ይብል) “ትውልድ ቦታውን የደብቀ ተውልዴ ዓድዋ ነው ይላል” ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዓድዋ የምትባላው አውራጃ አያውቃትም የትግራይ አውራጅዎች ጨምሮ ምክንያቱም አላደገበትም ሽሬ ሸራሮ ያወቃትም ያያትም በ1974 ዓ.ም. ነው። በወያኔ የተሰጠው ምርቃት ነው የትግራይ መሪ የሆነው ኤርትራዊ በመሆኑም ። እሱ ብቻ አይደለም ብዙ ናቸው፤ ለምሳሌ እንውሰድ መለስ ዜናዊ ፤ ሙሉ ሓጎስ፤ተክሌ መሓሪ “ሙሴ” ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፤ ግደይ ዘራርአፅዮን፤ ቴድሮስ ሓጎስ፤ ስብሓት ነጋ፤ ሥዩም መስፍን፤ ፃድቃን ገብረተንሳይ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ፤ ቴድሮስ አድሓኖም ኣረ ስንቱን የትግራይ ትውልድ የሌላቸው ከወያኔተቀላቅለው ከ1967ዓ፣ም፣ እስከ አሁንዋ ስአት ትግራይን እየመርዋ ያሉት።

ከሚያሳዝነው ነገር ዋናውና ም የትግራይ ክልል ብሎ ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔ ከጠራት ከ1985ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የግል ንብረታቸው በመያዝ የምትመራውም፤ የትግራይ ፕረዚዳንት አንድ ኢትዮጵያዊ የትግራይ የእንደርታው መቀሌ ተወላጅ አቶ ገብሩ አስራት በርእሰ መሪነት ነበር፤ በ1993 ዓ.ም. እሱን ከድርጅቱ አባርረው የሚፈልጉትና ሲመኙት የነበሩቱን ትግራይ በራስዋ ልጆች መመራት የለባትም በሚለው በወያኔው በፖሊሳቸው መሰረት ከኤርትራ በተሰባሰቡ ባንዳ የባንዳ ልጆች እንድትመራ በመለስ ዜናዊና በስብሓት ነጋ ተወሰነ። በዚሁ መሰረት ተከታትለው የመጡ ትውልደ ኤርትራውያን የትግራይ ክልል ርእሰ መሪዎች ሆኑ።

ለአብነት እንመልከት! … 1ኛው ሃለቃ ፀጋይ በርሄ ፤ 2ኛው ዓባይ ወልዱ 3ኛው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሾመ።ትግራይና ህዝብዋን እንደፈለገው እያሸማቀቁ ወያኒያዊ የባርነት አገዛዙን በማጠናከር ህዝብ ለስደትና ርሃብ በሽታ እየዳረጉት የመጡትም ከሃለቃ ፀጋይ በርሄ ንግሥና ጀምሮ ሲሆን። በፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት የሚታወቀው ባንዳው መሪው ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለከፋ ደረጃ የትግራይ ህዝብ ተዳርጎ ይገኛል። የደብረፅዮን ገ/ሚካአኤል እውነተኛ የሂወት ታሪኩ ይህ ነው። ህ.ወ.ሓ.ትና የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት// ዘረኛውና ጠባቡ ህ፣ወ.ሓ.ት ፀረ ኢትዮጵያ ሏሉአላዊነት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት መሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አጠናቅቆ የሚያውቀው ሓቅ ነው። በሃገርና በህዝብ የሚነግድ ወረበላ ማፍያ ነጋዴ ሓፍረት ቢስ ፀረ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ህ.ወ.ሓ.ት.ወያኔ መሆኑ መላው የኢትዮጵያ በሚገባ ያውቃል ስለ ሆነመም ህዝብ እናት ሃገሩ ኢትዮጵያና የራሱን አንድነት
ይጠብቅ።

ወያኔ ደደቢት በረሃ የገባው 1ኛ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለማፍረስ፤የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ለመናድና ለመበታተ 2ኛ የኢትዮጵያን ታሪክ መሉ አሻራው አጥፍቶ የራሱን ዝና ለመፍጠር የወያኔን ታሪክ ለመፍጠር እና ለመፃፍ 3ኛ አማራ ህዝብ የአማራው ጨቋኝ ገዢ ስርአት እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከርስትና እምነት ጨምረህ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት መደምሰስ አለብኝ ብሎ እቅድና ፖሊሲ አዘጋጅቶ ይህ ተግባራዊ በማድረግ “ታላቅዋ የትግራይ ዲሞክራያሳዊት ሪባብሊክ ስርአት መፍጠርና ትግራይን ከኢትዮጵያ ተገንጥለው ነፃ ሃገር ትግራይ መመስረት ነው በማለት የወያኔ የትግል መርሆ ከዋና አላማው
አንዱ ይህ ነው።

ህ.ወ.ሓ.ት.እና የ2010 ዓ.ም. ለውጥ!! የህ.ወ.ሓ.ት፣መሪዎች ደርግን አሸንፈን ኢትዮጵያና ህዝብዋ ተቆጣጥረን እጃችን ውስጥ አስገብተን እንገዛለን የሚል ሃሳብ ፍፁም አልነበራቸውም ፤የነሱ ትልቁና ዋነኛው ዓላማቸው ትግራይ ከድርግ ተዋግተን ትግራይ ነፃ እናወጣለን ትግራያም ከኢትዮጵያ ገንጥለን የራስዋ የሆነ ነፃ መንግሥትም ትመሰርታለች ነበር የህ.ወ.ሓ.ት. ዋናው ዓላማ። የትግላቸው ፖሊሲም አላማው ይህ ነው።ይህን ፖሊሲና የትግል አቋማቸው ተከትለው የካቲት 11 ቀን 1967ዓ.ም “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት” (ት.ህ.ነ.አ.ድ.)ተብሎ በይፋ ተመሰረተ።

በየካቲት ወር 1968 ዓ.ም. በዲማ ጉባኤ በድርጅቱ ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ የትግሉ ማኒፈስቶ‹መትከል›በእነሱ አጠራር ይህ ማለትም የትግሉ ፖሊሲ አቋም፤ ድርጅቱም አዲስ ስም እንዲሰጠው በነበሩት ጥቂት ታጋዮች ውይይት ከተደረገ ማኒፈስቶው ፀደቀ የድርጁቱ ስምም “ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ” (ተ.ሓ.ህ.ት.) ተባለ፤ ይህ ማለትም ህ.ወ.ሓ.ት.ቀጥሎም ማ.ሌ.ሊ.ት ተመልሶም ህ.ወሓ.ት.ስሙን እየለዋወጠ “የመጣ አጭበርባሪው ድርጅት ህ.ወ.ሓ.ት. ነው። ይህ ድርጅት ሲፈጠር ከመነሻው ፋሽሽት ድርጅትም ነው፤ መሪዎቹ ከኛ በላይ አዋቂ በዚች ዓለም አልተፈጠረም አይገኝም የሚሉ የዕውቀት ድሆች ናቸው፤ ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጥና በውይይት ነገር መፍታተ እደሚቻል ፍፁም አያውቁም አእሙራቸው የአለት ድንጋይ፤ፍፁም በዚች ምድር የድንጋይ ዘመን ቅሪቶች ይፈለጉ ቢባል የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎችና አባሎቻቸው ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም. የተፈጠረው ለውጥ ህ.ወ.ሓ፣ት፣ ወያኔው ግንቦት ወር 1983 ኢትዮጵያን በመውረር ሃገርና ህዝብ ከተቆጣጠረ ለ27 አመታት በፋሽሽታዊ ስርአቱ ሃገርና ህዝብ ያጠፋ ፀር ድርጀት የኢትዮጵያ ህዝብ ህፃን ወጣት ሽማግሌ ሴት ወንድ ሳይለይ ለ27 አመታት በምሬት ታግሎ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ ከመንበር ሥልጣኑ ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት ወያኔን ንቅሎ ያባረረው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው፤ ወያኔ በ27 ዓመቱ የስልጣን ዘመኑ የፈፀማቸው ወንጀሎች ዘግናኝ አሰቃቂ ድርጊቶች የፈፀመ መንግሥት አረሜኔ ስርአት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ያፈረሰ ኢትዮጵያን ያዳከመ በዘር በቋንቋ ኢትዮጵያን የሸነሸነ በአንድነት የቆየ ህዝብዋን አንድነቱ ያወደመ ህ፣ወ.ሓ.ት.ነው፤ መሬት የመንግሥት ብሎ መሬቱን ከኢትዮጵያ ህዝብ በመንጠቅ የድርጅቱ አባላትና ካድሬዎቹ ሰፋፊ መሬት በመስጠት ለውጭ ሃገር ባለ ሃብት ሰዎች በመሸጥ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለችግርና ረሃብ የዳረገ ወያኔ ነው፤ የኢትዮጵያ የኢኮነሚ ተቋማት በወያኔ ተወርሰው የመንግሥት ነው በሚል ሽፋን እንደ ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንክ ሌሎች ባንኮች የመድን ኢንሹራንቶች መብራት ሃይል ማአድኖች ሆስፒታሎች ትልልቅ ሆቴሎች ፓርኮች ወ.ዘ.ተ.በመንግሥት ሽፋን በህ.ወ.ሓ.ት.ወያኔ ተወርሰው 27 ዓመታት ሙሉ በጥቂት የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎቸና ካድሬዎቻቸው ሙሉ በሙሉን ተዘርፈዋል፤ ሃገር ደህይታ ህዝብ ለችጋር ለመከራ ድህነት ለበሽታ ርሃብ ስለተጋለጠ ከዚህ ባገኝ ብሎ ለስደት የተዳረገው ኢትዮጵያዊ በዛም የውሃ ሽታ ሆኖ የቀረው የኢትዮጵያ አምላክ ይቁጠረው፤ በወያኔ የ27 ዓመት ስርአት ኢትዮጵያና ህዝብዋ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት፣ የአገዛዝ ዘመን ወድመዋል ጠፍተዋል ኢትዮጵያ ወደ ግላጭ ድህነት ወደቀች ህዝብዋም እንኳንስ የሚበላ እህል የሚጠጣ ውሃ ያጣበት በዚሁ የወያኔ የ27 ዓመት አገዛዝ ዘመን ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት ተዘርፋለች።ዝርፍያው ብዝህ የተወሰነ አልነበረም ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ወያኔ ባስቀመጠው በትግል ፖሊሲው ማኒፈስቶው ታላቅዋን የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ለመመስረት ከወሎ ጠ/ግዛት ከአለውሃ ምላሽ እስከ ራያ ድረስ ከጎንደር ጠ/ግዛት ሰሜን ጎንደር በሙሉ እንዳለ ወደ ትግራይ መጠቅለል አለበት በማለት በማኒፈስተው በማስገባት በጉልበትና በጠመንጃ ሃይል መሬቱን ወረው ተቆጣጠሩት የሰሜን ጎንደር ህዝብ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር በክፉ መልኩ ታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም ወያኔ ሃይሉ ሰብስቦ 1ኛ ታጋዩ 2ኛ ወየንቲ(ምልሻው) 3ኛ ክርቢት(ክራቢት) ክርቢት ወያኔ በልዩ ታክቲክ አሰልጥኖ ሽብርና ግድያ የሚፈፅሙ ናቸው ፤ሰሜን ጎንደር በተለያዩ አቅጣጫ በማሰማራት በንፁህ ህዝብ የሲኦል ነበልባል ወረደ ህዝብ ሞተ ተገደለ ሂወት በመሬቱ እንደቅጠል አረገፉት ሃብቱ ንብረቱ ሁሉ በህ.ወ.ሓ.ት.ውርስ እየተባለ ተዘረፈ፤ ሂወቱን ይዞ ያመለጠ ደግሞ ለስደትና ለእንግልት ተዳረገ።

ወያኔ በጉልበቱ ሥልጣን ከጨበጠም ኢትዮጵያን ክልል ብሎ በመከፋፈል ለዕድሜው ማራዘሚያ የተጠቀመብት ዘዴ በሌላም በኩል የትግራይን ግዛት በበለጠ ለማስፋፋት ይጠቅመኛል በሚል እሳቤ የተቀናጀ ነው ለምሳሌ ላይ አርማጮህና፤ ታች አርማጮህ፤ መተከል፤ የትግራይ ግዛት ናቸው ተብለው ወያኔ እንደልማዱ ለመቀማት በትግራይ ካርታ አካቶ ካርታውን እያሰራጨ እንደነበር ሁላችን ያየነው እውነት ነው። ህ.ወ.ሓ.ት ከልደተ ጥምቀቱ ሲፈጠር ፀረ ኢትዮጵያ ነው፤ህ.ወ.ሓ.ት ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ነው።ህ.ወ.ሓ.ት ከወራሪው የመቃድሾ መንግሥት ሳይድ ባሬ በ1969ዓ.ም. በመተባበር ኢትዮጵያን የወጋና ያቆሰለ የለየልት ከሃዲ ድርጂ ነው፤ ህ፣ ወ.ሓ.ት.የኢትዮጵያን ግዛት አሳልፎ ለሱዳን መንግሥት የሸጠ ከሃዲ ድርጅት የጠላት መሳሪያ ነው፤ ህ.ወ.ሓ፣ት፣በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ በአማራው ላይ የፈፀመው እየፈፀመው ያለውን ፤ ህ.ወ.ሓ.ት ወራሪና ተስፋፊ ድርጅት ነው ፤ ህ.ወ.ሓ.ት በትግራይ ህዝብ ኢስባዊ በሆነው መንገድ የትግራይ ህዝብ አጥፍቶታል ገድሎታ ታርደዋል በፈፀመው ውንጀል ተጠያቂ ነው ፤ህ.ወ.ሓ.ት.ተጠያቂ ወንጀለኛ ስለሆነ በሕግ መጠየቅ አለበት።

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ በዚሁ ወንጀለኛ ድርጅት ህ.ወ.ሓ.ት የስቃይ መክራ ሲኦል ከወረደብህ ከየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. እስከ ዛሬዋ እለት 2012 ዓ.ም 45 አመታት ሙሉ በባርነት ተይዘህ ወያኔ በስምህ ነግዶብሃ ባንተ ስም ያልፈፀመው ወንጀል የለም ፤አሁንም እየተጠቀመብት፤ ተነስ ከዚሁ የወያኔ የባርነት አገዛዝ ራስህን ነፃ አውጣ ወያኔ የነጠቀህን ክብርህን መልሰው በቃኝ በል የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ካንተ ጋር ነው ያለው። ለተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ መለእክቴን ማተላልፍ የምፈልገው በህ.ወ.ሓ.ት.ወሳኝ እርምጃ ካልወሰድክ ወያኔ ካለ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላምና ተባብሮ መኖር እፎይታም ማግኘት በፍፁም አይቻልም አይታሰም።
ይቀጥላል

LEAVE A REPLY