በአክሱምና በአ/አ ከተሞች ሦስት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል በሚል ተጠረጠሩ

በአክሱምና በአ/አ ከተሞች ሦስት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል በሚል ተጠረጠሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ ሌሎች አዲስ አራት ሰዎች መገኘታቸውን ገለጸ።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተከናወነ በሚገኘው ሥራ በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና 27 የተለያዩ የድንበር መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነገረ። እስካሁን ለ47 ሺህ 162 ተጓዦች የሙቀት መለያ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

የጤና ኢንስቲትዩቱ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ሲሆን፤ በቫይረሱ የተጠረጠሩት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን አንዱ ደግሞ ቻይናዊ መሆናቸውን ጠቁሟል። ከዚህ ቀደም አራት ሰዎች በቫይረሱ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ መደረጉ ይታወቃል።

በበሽታው ከተጠረጠሩ አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ የተቀሩት ደግሞ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጸው ኢንስቲቲዩቱ ፤ የአራቱም ግለሰቦች ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቋል።

አክሱም ላይ በለይቶ ማቆያ እንዲቆይ የተደረገው ግለሰብ የበሽታው ምልክቶችን በራሱ ላይ በማየቱ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማደረጉን ተከትሎ ነው። በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር መንገድ እና እና ሃያ ሰባት የተለያዩ የድንበር መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ የማጣራት ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ይህ ምርመራ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያላቸውን ተጓዦችን የሚለይ ሲሆን ይሄም የቫይረሱ የበሽታ ምልክት የሚያሳዩትን ለመለየት እንደሚረዳም ኢንስቲትዩቱ አብራርቷል።

ከቻይና የሚመጡ ሁሉንም ተጓዦች  አገር ውሰጥ በሚቆዩበት ወቅት አድራሻቸውን የሚመዘገብ ሲሆን ለአስራ አራት ቀናትም የሚከታተል ቡድን መቋቋሙም ተገልጿል። በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ታካሚዎችንም ለመውሰድ አራት ተሽከርካሪዎችና ሁለት አምቡላንሶች ተመድበዋል:: የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ በቦሌ ጨፌ ያለ የህክምና ቦታ እና የየካ ኮተቤ ሆስፒታል ለህክምና መስጫነት የተመረጡ መሆናቸው ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY