ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በድሬዳዋ ከተማ የገንዳ ሮቃ አካባቢ ኗሪዎች የጅብ መንጋ ጥቃትእያደረሰባቸው በመሆኑ የሚመለከተው አካልመፍትሔእንዲፈለግላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የጅብ ጥቃት ተከትሎ በድሬዳዋከተማ ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ከቀኑዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ልዩስሙ ገንዳ ሮቃ ከሚባለው ገዳላማ ስፍራ የወጣ የጅብ መንጋ፤ በሰፈሩ በመጫወት ላይከነበሩ ሕጻናት መካከል አንድ የሦስትዓመት ሕፃን አንጠልጥሎ ወስዷል፡፡
በክስተቱ የተደናገጡት ሕጻናት ባሰሙት ጩኸት የሰፈሩ ሰውነቅሎ ቢወጣም፣ የተጣቂው ሕጻን አባትን ጨምሮየተወሰኑሰዎች የጅብ መንጋው ጎሬ ድረስ ሮጠው በመሄድ ፤ የአንዱን ጅብጭራ በመያዝ የልጁን ሕይወትለማትረፍ ያደረገው ሙከራሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ሕጻኑን በነዋሪው ከፍተኛርብርብ ከጅብመንጋው ማስጣል ቢቻልም ጭንቅላቱ ላይ በጅብንክሻ የከፋ ጉዳት ስለደረሰበት ሕይወቱ አልፏል፡፡
ከቀድሞ ምድር ባቡር ድርጅት፣ ከጉምሩክና ከምስራቅ አየር ኃይል፣በተለምዶ ሰባተኛ ከሚባለው የጦር ካምፕየሚዋሰነው ገንዳ ሮቃየሚባለው መንደር ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥሻ እየተዋጠ በመምጣቱየጅብ መንጋየሚርመሰመስበት ስፍራ ሆኗል፡፡
የጅብ መንጋው በአካባቢው እንዲርመሰመስ ካደረጉት ምክንያቶችመካከል ከምድር ባቡር ድርጅት የፍሳሽቱቦዎች ከሰባተኛ ጦርካምፕና ከጉምሩክ የሚጣሉ ተረፈ ምርቶች የሚለቃቀመው ምግብፍለጋ እንደሆነተረጋግጧል፡፡