ባል ሚስቱን በልጆቹ ፊት ገድሎ ራሱን አጠፋ

ባል ሚስቱን በልጆቹ ፊት ገድሎ ራሱን አጠፋ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከካርል አደባባይ ወረድ ብሎ፣ በተለምዶ ብስራተ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ “ታሪክ ስጋ ቤት” ፊት ለፊትበሚገኘው አንድ መኖርያ ቤት ውስጥ ጠዋት የአንድ ቤተሰብሕይወት በአባወራው አማካይነት መጥፋቱ ተረጋግጧል፡፡

ጥር 26 ቀን 2012 ዓ።ም ከጠዋቱ 8፡30 አካባቢ ነበር የተኩስ ድምፅ የተሰማው፡፡አደጋው ደርሶበታል በተባለው ቤት ውስጥ የሚኖሩትባልና ሚስቶች የ14 እና 12 ዓመት ታዳጊ ልጆች ያላቸው ከመሆኑ ባሻገር፤ ከሁለት ወር በፊት በመሀላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ በሽምግልና ከሳምንት በፊት እርቅ በመፈጠሩ እንደቀድሞውመኖር ጀምረው ነበር፡፡

ሆኖም የውዝግቡ መንስዔበይፋ ባይረጋገጥም፤ ዛሬ ማለዳ ባል በሁለት ልጆቹ ፊት ሚስቱንበጥይት ተኩሶ መትቷታል፡፡ እናት በደረሰባት አደጋ ስታቃስት ያዩልጆች እናታቸውን በመጥራት አቅፈዋት ማልቀስ ሲጀምሩ የደረሰው የቤቱ ጥበቃ ላይም ጥይት ተኩሶበት እንዳቆሰለው ተሰምቷል፡፡

በስተመጨረሻ ባል ወደ ሳሎን በማምራት ራሱ ላይ በመተኮስ ሕይወቱን ከማጥፋቱ ባሻገር ሚስቱንም በተኮሰው ጥይት መግደሉተረጋግጧል፡፡

LEAVE A REPLY