36ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬመካሄድ ጀመረ

36ኛው የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬመካሄድ ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ መካሄድ በጀመረው ጉባዔ ላይ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማትን ጨምሮ፣ የ55 የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ እና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የሆነችው ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ ፈቻ ንግየመክግር አድርገዋል። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ በንግግራቸው፤ በርካታ ችግሮች በተደቀኑባት አህጉር፣ የጦር መሳሪያ ድምፅ የማይሰማበት አፍሪካን የመፍጠር ፕሮጀክት ይሳካ ዘንድ ሁሉም አባል አገራት ትብብር እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከግጭቶች ጋር ተያይዘው ለሚፈጠሩ  የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች አስፈላጊ መፍትሄ እንዲሰጥ እና ለስደተኞች አስፈላጊው ጥበቃ እና እንክብካቤ ሊደረግ እንደሚገባም ያሳሰቡት ፤ የአፍሪካ ኅብረት የማሻሸሻያ ሥራዎች እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንጌ በበኩላቸው ማቆሚያ ያጡ ግጭቶች የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት እየጎዱት ነው ብለዋል።

በዛሬው እለት የተጀመረው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ እስከ ነገ የሚዘልቅ መሆኑ ተነግሯል። ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው በአፍሪካ ኅብረት ቋሚ መልዕክተኞች ባረቀቁት የመሪዎች ጉባዔ አጀንዳ ላይ ከተወያዩ በኋላ ለመሪዎቹ ጉባዔ እንዲቀርብ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች 33ኛ መደበኛ ጉባኤ የካቲት 1 እና 2 2012 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ፤ የመሪዎቹ ጉባዔ “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት”በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

በጉባዔው ላይ የ31 የአፍሪካ አገራት ፕሬዚዳንቶች፣ 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የ7 አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የ3 አገራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ 14 ቀዳማዊት እመቤቶችን ጨምሮ 45 አገራት በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ ነው የሚጠበቀው። ከአባል አገራቱ ውጪየካናዳ እና የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የፍልስጤም መሪ፣ የሦስት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የሰባት አገራት አምባሳደሮች ተሳታፊ ይሆናሉ

LEAVE A REPLY