አይፎን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ ማክስ ሊያመርት ነው

አይፎን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ ማክስ ሊያመርት ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግዙፉ ኤሌክትሮኒክስ አምራቹ ፎክስኮን ኮሮና ቫይረሰን ለመከላከል ወይም በቀዶ ህክምና ወቅት ሊደረግ የሚችል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ (ጭምብል) ሊያመርት መሆኑ ተሰማ።

የአይፎን ስልክ አምራች ጭምር የሆነው ኩባንያው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቻይና ለመዝጋት የተገደደውን ማምረቻ ጣቢያዎቹን ለመክፍት ጥረት እያደረግኹ ነውም ብሏል።

የኮሮናቫይረስ መከሰት በመላው ዓለም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እጥረት እንዲያጋጥም አድርጓል።የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሀብት ላይም ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩ ተሰምቷል::

ፎክስኮን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በቀን ሁለት ሚሊዮን የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን ለማምረት ማቀዱን አስታውቋል። “ይህን ወረርሽኝ ስንዋጋ እያንዳንዷ ሰከንድ ትርጉም አላት” ሲል ኩባንያው ‘ዊቻት’ በተሰኘው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስፍሯል። “የመከላከል እርምጃ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ያስችላል። የሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻል ማለት በፍጥነት ቫይረሱን ማሸነፍ ማለት ነው” ብሏል።

ይህ ኩባንያ የዓለማችን ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ሲሆን፤ ከአይፎን በተጨማሪ፣ አይፓድ፣ የአማዞን ኪንድል እና ፕለይስቴሽኖችን ያመርታል።

ኩባንያው በቅድሚያ የሚያመርታቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ምርቶች ለሠራተኞቹ እንደ ሚያድል ከዚያ በኋላ ምርቶቹን ለገበያ እንደሚያቀርብ ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY