ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አገር ዐቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012 የትምህርት ዘመን አገር ዐቀፍ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ ተረጋግጧል። በተያያዘ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል ዐቀፍ ፈተና ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ኤጀንሲው አስታውቋል።
ህወሓት መራሹ መንግሥት ከ19 94 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገው ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ መሠረት በርካታ ታዳጊ ወጣቶች በ15 እና 16 ዓመታቸው ማትሪክ ከ10ኛ ክፍል እየወሰዱ ከዕውቀት ማዕድ እንዲስተጓጎሉ በማድረግ እንድ ትውልድ እንዲመክን ማድረጉን ምሁራንና የዘርፉ ባለሙያዎች ሲከሱ መቆየታቸው ይታወሳል።