ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች መያዙን ገለጸ። የተያዙት እቃዎች ውስጥ የቴሌኮም ማጭበርበር ለማከናወን የሚያስችሉ 6 መሳሪያዎች (Sim box) ማግኘቱንም ይፋ አድርጓል።
በዚህም ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን በኤጀንሲው የሴኩሪቲ ክሊራንስ አገልግሎት ማዕከል ሓላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን አስታውቀዋል:: ባለፉት 6 ወራት ከቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች በተጨማሪ ለስለላ አገልግሎት የሚውሉ 60 ካሜራዎችን አገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት መያዛቸውንም ሓላፊው ተናግረዋል።
መንግሥት የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች ላይ የሚያደረገውን ቁጥጥር በተጠናከረ መልኩ ወደ ፊትም ከአጋር አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰራ የመረጃና የደህንነት ቢሮ አስታውቋል።