በጁነዲን ሳዶ የተቋቋመው ሸገር ባንክ አክሲዮኖችን (ድርሻ) መሸጥ ጀመረ

በጁነዲን ሳዶ የተቋቋመው ሸገር ባንክ አክሲዮኖችን (ድርሻ) መሸጥ ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በወያኔ የተገፉት የቀድምው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ “ሸገር” የተሰኘ አዲስ ባንክ ከአጋሮቻቸው ጋር በማቋቋም ላይ መሆናቸው ታወቀ::

ድርሻ (አክሲዮን) የመሸጥ ፈቃድ አግኝተው ከየካቲት ሰባት ጀምሮ በይፋ አክሲዮን መሸጥ መጀመራቸውን የገለፁት የሸገር ባንክ መሥራች እና የቦርዱ ሰብሳቢ ጁነዲን ሳዶ የባንኩ የምሥረታ አስተባባሪ ኮሚቴ በአጠቃላይ 150 ግለሰቦች እንዳሉት፣ ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከዳያስፖራው ሀብት በማሰባሰብ ባንኩ  ካፒታሉን እንደሚያሟላ ተናግረዋል።

ጁነዲን ሳዶ የቀድሞ የኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት ወቅት የመገናኛ እና ትራንስፖርት ሚኒስቴር የሳይበር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሆነው በመንግሥት የሥራ ሓላፊነቶች ላይ ማገልገላቸው ይታወሳል::

LEAVE A REPLY