ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ “የኢትዮጵያን ጉዳይ እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከተው አይደለም” በማለት መረር ባለ ቃል መናገራቸውን ያልወደዱትየህወሓት ነባር ታጋዮችና የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ኢሳያስ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተዋል የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ተቃወሙ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን እና የቀድሞ የትግራይ ፕሬዝዳንት አቶ ፀጋይ በርኸ ለየካቲት 11 ክብረ በዓል በተዘጋጁ መድረኮች ላይ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስን በግልፅ ከመተቸታቸው ባሻገር የኤርትራን መንግሥት በአደባባይ አብጠሌጥለዋል።
አቶ ፀጋይ በርኸ ባለፈው በማይ ፀብሪ ከተማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ በኢትዮጵያ ጉዳይ እጁን ካስገባ እጁ ይሰበራል እንጂ የሚያመጣው አንዳች ነገር የለም ሲሉ ተደምጠዋል::
“ይህ የኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስን አያገባቸውም” ያሉት አቶ ፀጋይ የኢሳይያስን ጣልቃ ገብነት “ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ መንግሥት ሊቃወሙት ይገባል ከማለታቸው በተጨማሪ “ኢሳያስ አገራችንን ለማፍረስ ነው ይህን እያደረገ ያለው ፣ሁለት ሶስቴ ያስቡበት” ሲሉም የኤርትራውን ፕሬዚዳንት አስጠንቅቀዋል።
በትናንትናው ዕለት የካቲት 8፣2012 ዓ.ም አክሱም ሲከበር በነበረው የህወሓት 45ኛ ዓመት ምስረታ በዓል የተገኙት አቶ ስዩም መስፍንም በንግግራቸው በሞት መቃብር አፋፍ ላይ ያለው ድርጅታቸው ህወሓት በቀደመ ጠንካራ ቅርጽና አቋሙ ላይ ያለ አስመስለው የተጠቀሙበትን ተራ ጉራናትችት አሰምተዋል።
”ኢሳይያስ አፈወርቂ ወያኔን እና ወያኔ የገነባውን ሕገ-መንግሥት አፈርሳለሁ ማለታቸው ነውር” በማለት ከእውነታው ያፈነገጠ የሐሰት ፕሮፐጋንዳ ያለሀፍረት የነዙት የገዳዮ ቡድን ነባር ታጋይ ስዮም መስፍን “ይሄንን ሕገ-መንግሥት ለማፍረስ የሚመጣ ካለ እሱ ሞሶሎኒ ነው። ሂትለር ነው” በማለት የትግራይን ሕዝብ በኤርትራ ሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ መልእክት አስተላፈዋል።
“ኢሳይያስ ግማሹን የኤርትራ ህዝብ በትኖ ሲያበቃ፤ የኤርትራን ህዝብ ማስተዳደር ሳይችል ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት ሊያመጣ አይቻልም” የሚሉት የኃጢአት መአት የተሸከመው የወያኔ ቡድን ዋነኛ ተዋናይ ፤ የኤርትራ ህዝብም፤ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት እንዳሉት ሁሉ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስን “መጀመርያ የውስጥ ችግራችንን እንፍታ ሊሏቸው ይገባል ሲሉ በኤርትራ ብጥብጥ እንዲነሳ ያላቸውን ፍላጎት ያሰበቀ ንግግር አድርገዋል:: “ከዚያም እንደ ህዝብ፣ እንደ አገራት እንደ መንግሥታት አንዱ ሌላኛው ላይ ጣልቃ ሳይገባ መሥራት እንችላለን” ነው ያሉት በመቀሌ የመሸጉት ስዩም መስፍን።