የመኢጠማ አባላት ጉድ ፈላብን! በብርጭቆ ድራፍት ከ40 በመቶ በላይ ዋጋ ጨመረ!

የመኢጠማ አባላት ጉድ ፈላብን! በብርጭቆ ድራፍት ከ40 በመቶ በላይ ዋጋ ጨመረ!

  1. || ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ||

ሀገር እየታመሰች አንተ ስለድራፍት ዋጋ መጨመር ታወራለህየደላህ ነህ!” እንዳትሉኝ እንጂ የአቢ መንግሥት ድል በድልእየተምበሸበሸ  መጥቶ አሁን ደግሞ ባለችን አንዲት ናኛ ላይ ውኃእማያሰኝ ዱላውን አንስቷል፡፡ የፕሮቴስታንቶቹ መንግሥት አልቻልብሏል፡፡ አብዛኞቹ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከመጠጥ ጋርያላቸው ፍቅር እስከዚህ መሆኑ ገራልቢያንስ ሲጠጡ በአደባባይአይታዩም፡፡ እዚህ ላይውስጡን ለቄስየሚሉ ወገኖች እንዳሉ ግንአይካድም፡፡ ታላላቅ ፓስተሮች ሳይቀሩ በቤታውና በሥውር ዝጉብኞችውስኪና ቢራ እንደሚራጩ  የሚወራ መሆኑን መደበቅተሸኮርማሚነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ሰው በወደደው ይቆርባልና በዋጋጭማሪ የሰውን ፍላጎት ለመግታት መሞከር ነውር ነው፡፡

ትናንት ማታ እንደወትሮየ ከሥራ ወጥቼ ሱክ ሱክ እያል ኞቼወደሚገኙበት የማታ ትምህርት ማዘውተሪያ ሥፍራየ እሄድላችኋለሁለእናንተ ስል መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ እንደደረስኩ የቀደሙኝ ኞቼዳጊየምሥራች!” ይሉኛል፡፡ ምን ተገኝቶ እንደዚያ እንዳ ሳልጠይምሥር ብሉ!” እላለሁ፡፡ አንዱ ለጠቀናያን የተለጠፈ ወረቀትአንብበውኛል፡፡ ሳነበው በዚያ የሕዝብ መዝናኛ የቀበሌ ክበብ 13 ብር የነበረው ድራፍት አምስት ብር ጨምሮ 18፣ 15 ብር የነበረው ትንሹጠርሙስ ቢራ 20 ብር መሆኑን እረዳለሁ፡፡

እውነቴን ነው የምችሁጠላታችሁ ክው ይበልና እንደሎጥ ሚስት ክው ብዬ ቁሜ  ቀረሁ፡፡ ቁጭ እንድል ቢወተውቱኝም የሀዘኑ ብዛት ወደ ተረጋጋ ሰውነቴሊመልሰኝ አልቻለም፡፡ ሌላ ብሶታችንን የምንተነፍስ ነገር የለንም፡፡ ከየትም ተሰባስበን ካለችን አነስተኛ ገቢ ቆንጥረን ቤተሰባችንንበመበደል የሆድ የሆዳችንን ተንፍሰን ወደየጎጇችን የምንገባው በዚሁድራፍትና ቢራ ነበር፡፡ በዚህም መጡብን፡፡ አምባገነኖችየማይመጡብህ አቅጣጫ የለም፡፡ አሁን የቀራቸው ባል ከሚስቱሚስትም ከባሏ ለምታገኘው ተፈጥሯዊ እርካታ ግብር ማስከፈል ብቻነው፡፡ እንደዚያ ቢሉኝ ሲፈልጉ ያስመርምሩኝ እንጂየሜተር አርቲስትአፈወርቅ ተክሌ ወንድም ከሆንኩ ሰነበትኩ!” ነው የምላቸው፡፡ ሆ! ሰውበገዛ መንግሥቱእንደባብ እየተቀጠቀጠ ተሳቅቆ ይኖራል? ምንዓይነት ውርጅብኝ ነው! በሣዳም ሁሴንና በጋዳፊ የወረደው መቅሰፍትበነዚህም ላይ ይውረድአሜን! የተባረኩ መንግሥታት ቀጭን ሰበብእየፈለጉ ሕዝባቸውን ይጠቅማሉ፡፡ ከድህነት ሠፈር የመጡ የኢትዮጵያመሪዎች ደግሞ ድህነት አንጎላቸው ውስጥ ቤቱን ስለሠራባቸውበህልማቸውም በእውናቸውም የሚያስቡት ስለማደህየት እንጂስለማክበር አይደለም፡፡ እናም ዕረፍት አጥተው የሚጨነቁት ሕዝብንስለማቆርቆዝና አቆርቁዞም ስለነሱ እንዳያስብ ማድረግ ሆነ፡፡ በነሱ ተራየፖለቲካ አስተሳሰብ ሕዝብ ከተመቸው ለመንግሥት አይመችም ነው፡፡ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን፡፡

እርግጥ ነው መጠጥ ለማንም አይመከርም፡፡ መጠጥ ገዳይ ነው፡፡ ገዳይ ግን በአወሳሰድ ይወሰናል፡፡ በልክ ከሆነ ደግሞ ያጫውታልሀዘን ትካዜን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያስረሳል፡፡ በዚያም ላይ ኝነትንያጠናክራልሰውን ያቀራርባልያወያያልየዚህ ጭማሪ ዓላማም ይህንለማስቀረት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ጉዳት ብቻ ሳይ ጥቅምምአለውና በዚህ ማኅራዊ ገመድ ላይ ይህን ያህል መጨከን አይመስልም፡፡

አንድ ጭማሪ ሲደረግ ጥንቃቄን ይሻ፡፡ የዱሮ ጭማሬዎችንስናስታውስ የሚገር ነበሩ፡፡ ሥንትና ሥንት ዓመት ቆይቶ የሚደረግጭማሪ ቢበዛ አሥር ሣንቲምና አሥራ አምስት ሣንቲም ነው፡፡ አሁንግን የዛሬ 30 ዓመት ገደማ 1.70 ሣንቲም የነበረ ድራፍት አሁን በሕዝብመዝናኛ ክበብ ብቻ ብር 18 ሲገባ ጭማሪ ዘግናኝ ነው፡፡ በመቶኛብትመቱት እጅግ ብዙ ነው፡፡ በአንድ ቢራ አምስት ብር መጨመርማሪውን የቁጥር ችሎታ ገደል የሚከት ነው፡፡ ሃምሣ ሣንቲምመጨመር ወግ ነውአንድ ብር መጨመርም ወግ ነውአምስት ብር?! በግል ቡና ቤቶች ደግሞ እንኳ ዘምቦብሽ እንዲያውም ነሽእንዲሉ ናቸውና ይሄኔ ሰማይ ሰቅለውታል፡፡ ሌባው በዛደህናው አነሰበኑሮ እየተገረፈ ያለው ደህናውና የወር ገቢው ለሁለት ቀናትምየማይበቃው ዜጋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ወዴት አለህ?! እባክህንሕዝብ አስብርስትህንም ባርክ፡፡

ለነገሩ ከፕሮቴስታንት ምን ይጠበቃል? ባለሥልጣ ሁሉ ከላይእስታች ጴንጤ ወይም ሙስሊም ነው፡፡ እነዚህ ባለሥልጣናት ደግሞከኛ ጋር ወርደው ድራፍትና ቢራ አይሻሙም፡፡ ከፈለጉ ምን የመሰለምርጥ ፓኝና ዊስኪ ከሎንዶን ቤታቸው ድረስ በቀጥታይመጣላቸዋ፡፡ ይህ ጨለማ የማይነጋ እየመሰላቸው ግና በኛ በድሆችላይ ጢባጢቤ ይጫወታሉ፡፡ ለማየት ያብቃችሁአያያዛቸው ሁሉሌሊቱን የሚያሳጥር ነውና ተስፋችንን በአንድዬ ጥለን ከኃጢኣትናከክፋ ተቆጥበን የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፡፡ ወሮበሎች ጋርአንተባበር፡፡ ደግሞም በርትተን እንጸልይ፡፡

ቭየት ኅብረት ዘመን ራሽዎች ድንች ቮድካ ርካሽይደረግላቸው ነበር፡፡ ያን ካገኙ ወደ መንግሥት አያስቡም፡፡ መጽሐፉምእኮ ድሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ስጡት ይላል፡፡ ጴንዎቹመሪዎቻችን ግን ይቺን ጥቅስ አላነበቧም መሰለኝ፡፡ እንዲህ በአራቱምማዕዘን አክረው አክረው የተበጠሰ እንደሆነ (መበጠሱም አይቀርም) እነሱን አያድርገኝ፡፡ አቢይ ከመጣ ወዲህ ኑሮው ከቀን ወደ ቀንእንደመንኮራኩር እየተወነጨፈ ነው፡፡ እርሱ ግን ምንምአልመሰለውም፡፡ የአንድ ሽህ ምናም ብር ኩንታል ጤፍ አራት ሽህሲገባ አቢይን ማይርበው ቅንጣት አላሳሰበውም፡፡ የሃያ ብሩ የምግብዘይት 80 እና 90 ሲገባ የርሱ ምግብ በሕዝብ ቅቤና ዘይት ስለሚሠራጉዳዩ አይደለም፡፡ ወይ መንግሥት መሆን! በኢትዮጵያ መንግሥትመሆን እንዲህ ልበ-ድፍን ያደርጋል ነው? የነሱ ከርስ አይጉደልእንጂ ስለሕዝቡ የዕለት ከዕለት ኑሮ እኮ ቅንጣት አያስ፡፡ እነዚህንየአጋንንት ልጆች ከየትኛው የሲዖል መንደር አፍሶ እዚህች ኢትዮጵያውስጥ እንደዘረገፈብን እሱ ራሱ ይወቅ፡፡ ይሄ ሁሌ ይገርመኛል፡፡

ሀገር ቁና ሆናለች፡፡ ኑሮ ወደሰማየ ሰማያት በብርሃን ፍጥነትተተኮሰ፡፡ በዚህ የመጠጥ ዋጋ ጭማሪ ደግ ለማየት ያብቃችሁሕይወት እንደኳስ ሽቅብ ትጉናለች፡፡ እያንዳንዱ የግል ተዳዳሪ ይህንየመጠጥ ውድነት ለመጋፈጥ ሲል በሚሸጠው ዕቃና በሚሰጠውአገልግሎት ላይ ዋጋውን ዕጥፍ ድርብ ሲያደርገው ነገሩ ሁሉ ቡሃ ላይቆረቆር ይሆናል፡፡ ይህን የሚፈልጉ አምስተኛ ረድፈኞች ሳይሆኑአይቀሩም በዚህ የቀውስ ሰዓት በአላስፈላጊ ሁኔታ ይህን የዋጋ ጭማሪእውን ያደረጉት፡፡ አለበለዚያማ ሀገር በብዙ ችግሮች እየተናጠችየኑሮውድነቱ በተለይ ቅጥር ሠራተኛውን ከመኖር ወዳመኖር እየለወጠውበሚገኝበት በዚህ አስጨናቂ ወቅት ይህን ያህል እጅግ የተጋነነ ጭማሪአይደረግም ነበር፡፡ በአንዲት ብርጭቆ አምስት ብር መጨመር ማለትበራሱ እስካ በፍጹ ኪሣራ ነበር የሚሠሩት ማለት ነው፡፡ እንዲያእንዳልሆነ ደግሞ እናውቃለን፡፡

ለማንኛውም በዱሮ አጠራር የመላው ኢትዮጵያ ጠጭዎችማኅ አባላትን በዚህ አጋጣሚእግዜር ያጥናችሁየጌሾ ጌታችግራችሁን ይስማችሁ በማለት ላጽናናችሁ እፈልለሁ፡፡ ዕድለቁንድፍት ደታችኛውና ወደሚያዋጣኝ መንደር ጎራ እላለሁእሷየወቅቱን ፋሽ ተከትላ አሁን ችበት በመለኪያ አራትና አምስት ብርወደ ስምንትና ዐሥር ብር ልወርወር ካላለች፡፡ ተለያየን!

LEAVE A REPLY