የትግራይ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ህወሓትን በማውገዝ መግለጫ አወጡ

የትግራይ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ህወሓትን በማውገዝ መግለጫ አወጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የካቲት 11 ቀን የተከበረውን 45ኛ ዓመት የትጥቅ ትግል የተጀመረበትን ክብረ በዓልን በተመለከተ በትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራሮች መግለጫ አወጡ፡፡

አኩሪው የትግራይ ሕዝብ የፀረ ጭቆና ተጋድሎና መስዋዕትነት ከከሰሩ ኃይሎች አይራከሱም ቡድናዊ ፍላጎት መጠቀሚያ ምአይሆንም በሚል ርዕስ የፓርቲው አመራሮች አባላት ባወጡትመግለጫ፤ 45 ዓመታት በፊት ይደርስብህ የነበረው የዘመናትጭቆና እና አፈና ይልቁንም ወታደራዊው መንግስት ደርግ የተወሰዱትን መጠነ ሰፊ የግድያ የአፈናና የጭቆና እርምጃዎች ቢቃወሙም ለጥቂት ልጆች በተጀመረው ሕዝባዊ መነሳሳትና የትጥቅ ትግል በሰፊው ተቀጣጥሎ መላ ገሪቱ በማደረሱ 29 ዓመት በፊት ተጠናቆ ለአገራችን ኢትዮጵያ አዲስ የጉዞ ምዕራፍ እንዲከፈት መሰረት እንዲጣል ማድረጉ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

ሆኖም ይህንን አኩሪ የሕይወት መስዋዕትነትን የጠየቀው ተጋድሎን በአንድ በኩል የትግ አላማን በማጠልሸት መስዋዕትነቱን ለማራከስ በሚዳክሩ የከሰሩ ኃይሎች በሌላ በኩል ደግሞ የተከፈለውን ሕዝባዊ መስዋዕትነት ለራስ ጠባብ ቡድናዊ ዓላማ  ለማዋል በሚፈልጉ ኃይሎች መካከል በሚደረግ የገመድጉተታና እንቶ ፈንቶ ጨዋታ ባለቤት የሆነውን የትግራይ ሕዝብን የሚጋፋ መሆኑን እንገነዘባለንብለዋል የብልፅግና አባላቱ በመግለጫቸው፡፡

መግለጫው የብልፅግና ፓርቲ አመራ አካል እና የትግራይ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር አብርሃም በላይ ስም የወጣ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ከብልፅግና ፓርቲ ጋራ በመሰለፍ እነዚህን የከሰ ያሏቸውን ፖለቲከኞች እንዲታገል ጥሪ አድርጓል፡፡

LEAVE A REPLY