እንዳልነበሩበት – ተናዳፊ ንቦች ፤
ሇህዝባቸው ጥቃት – ዘብ ቆሞ አዳሪዎች ፤
የዕውቀትን ጥበብ – ትምህርት ቀስመውበት፤
ሇሇውጥ ሃዋሪያነት – ሃሳብ ላመኑበት፤
በአንድላይ ተነስተው – እንዳልተመሙበት፤
ዘመን አሳልፎ – ዘመንን ዯርቶ ፤
ሳየው ይገርመኛል ግቢው አንቀላፍቶ ፤
ግቢው አንኮራፍቶ።
” ፋኖ ተሰማራ – ፋኖ ተሰማራ ፤ “
” እንዯነ ሆ ቺ ሚን – እንዯ ቼ ጉቬራ ፤ “
“መሬት ላራሽ ይሁን – ገባርነት ይጥፋ ፤“
” የድሃ ልጅ ይማር – ትምህርት ይስፋፋ ፤ ”
ሃሳብን በሃሳብ – እያሞሻሇቅን፤
ትምህርት እንማር – እንቅሰም እውቀትን።
ማሇቱ ቀረና !
የአይምሮ ባዶነት – የሃሳብ ድህነት፤
የህሊና ዝገት – ሃሞተ ቢስነት ፤
ተዯማምረውበት – ጎሣ_ ዘረኝነት ፤
ይታያል ተኝቶ – ግቢው አንቀላፍቶ ፤
ግቢው አንኮራፍቶ።
የባዶነት ስሜት – ኳኳታ _ ኳኳታ ፤
የውስጣዊ ቁሸት – ክርፋት _ ክርፋት ሽታ፤
ቂም በቀል ጥላቻ – ተዯማምረውበት፤
ይታያል ተኝቶ – ግቢው አንቀላፍቶ፤
ግቢው አንኮራፍቶ።